Get Mystery Box with random crypto!

ከዓሳ ጋር በተያያዘ ኢየሱስ በመጽሐፍ ቅዱስ 4 ተዓምራቶችን አድርጓል። - በሁለት ዓሳ 5ሺህ ህዝ | Amazing Bible Facts



ከዓሳ ጋር በተያያዘ ኢየሱስ በመጽሐፍ ቅዱስ 4 ተዓምራቶችን አድርጓል።
- በሁለት ዓሳ 5ሺህ ህዝብ መግቧል [ማቴ 14: 15-25]።
ሕዝቡም በሣር ላይ እንዲቀመጡ አዘዘ፥ አምስቱንም እንጀራና ሁለቱን ዓሣ ይዞ ወደ ሰማይ አሻቅቦ አየና ባረከ፥ እንጀራውንም ቆርሶ ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠ፥ ደቀ መዛሙርቱም ለሕዝቡ።
ሁሉም በልተው ጠገቡ፥ የተረፈውንም ቁርስራሽ አሥራ ሁለት መሶብ ሙሉ አነሡ።
ከሴቶችና ከልጆችም በቀር የበሉት አምስት ሺህ ወንዶች ያህሉ ነበር። (ቁ. 19-21)

- ግብር ለመክፈል ሳንቲም ከዓሳ አፍ አውጥቷል [ማቴ 17: 24-27]።
" ነገር ግን እንዳናሰናክላቸው፥ ወደ ባሕር ሂድና መቃጥን ጣል፥ መጀመሪያም የሚወጣውን ዓሣ ውሰድና አፉን ስትከፍት እስታቴር*ፍ2* ታገኛለህ፤ ያን ወስደህ ስለ እኔና ስለ አንተ ስጣቸው አለው።" (ቁ.27)

- መረቡ እስኪቀደድ ዓሳ አስወጥቷል [ሉቃ 5: 4-11]
ስምዖንም መልሶ። አቤቱ፥ ሌሊቱን ሁሉ አድረን ስንደክም ምንም አልያዝንም፤ ነገር ግን በቃልህ መረቦቹን እጥላለሁ አለው።
ይህንም ባደረጉ ጊዜ እጅግ ብዙ ዓሣ ያዙ፤ መረቦቻቸውም ተቀደዱ። (ቁ. 5-6)

- መረባቸውን በስተቀኝ እንዲጥሉ ባዘዛቸው ጊዜ [ዩሐ 21:4-11]
" እርሱም። መረቡን በታንኳይቱ በስተ ቀኝ ጣሉት ታገኙማላችሁ አላቸው። ስለዚህ ጣሉት፤ በዚህም ጊዜ ከዓሣው ብዛት የተነሣ ሊጐትቱት አቃታቸው።" (ቁ.6)

አስደናቂ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነታዎች
@amazing_bible_facts
@amazing_bible_facts
@amazing_bible_facts