Get Mystery Box with random crypto!

የህወያትን እኩይ ዓላማ ለማስፈፀም በተለያየ ምክንያት ወደ ከተማዋ ገብተው እየተንቀሳቀሱ የመረጃ ማ | ግዮን-ፎረም

የህወያትን እኩይ ዓላማ ለማስፈፀም በተለያየ ምክንያት ወደ ከተማዋ ገብተው እየተንቀሳቀሱ የመረጃ ማቀበል ስራ የሚሰሩ 16 ተጠርጣሪ ሰርጎ ገቦችን እና ሶስት ህገ-ወጥ መሳሪያ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የደባርቅ ከተማ ከንቲባ እና የፀጥታ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ብርሀን ፀጋየ ገልፀዋል።
የህወሀትን ዳግም ወረራ ለመከላከል በሚደረግ ዘመቻ የመጀመሪያው ተግባር የከተማችን ከሰርጎገብ መጠበቅ እና የደጀንነት ሚና መወጣት ዋነኛና ቁልፍ ተግባር መሆኑ ታውቆ በአደረጃጀት ስምሪት ተሰጥቶ ወደ ስራ ከተገባ ሰነባብቷል ስለሆነም ደባርቅ ከተማ ውስጥ በጠንካራ የመረጃ መዋቅር እና የኬላ ጥበቃ እና በሌሎች ስምሪቶች የህወሀት ተላላኪ ሰርጎገብ ዓላማውን እንዳያሳካ የሚያስችል እንቅስቃሴ እየተደረገ ይገኛል ተብሏል።
የደባርቅ ከተማ ባለገጀራ ወጣቶች ፣ የሰሜን ጎንደር ጥቁር አንበሳ የቀድሞ ሰራዊት የበጎ አድራጎትና ልማት ማህበር አባላት ፣ አጠቃላይ የፀጥታ መዋቅሩ ፣ ወጣቶችና ማህበረሰቡ የአካባቢውን ሰላም እያስጠበቀና የደጀንነት ተግባር እየፈፀመ ይገኛል።
#የደባርቅ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮምንኬሽን።