Get Mystery Box with random crypto!

ሕዝቡ እያደረገ ያለው የምግብ ድጋፍ ጊዜያዊ ሳይሆን፤ ቋሚ የአእምሮ ስንቅና ትጥቅ ነው ሲሉ ግንባር | ግዮን-ፎረም

ሕዝቡ እያደረገ ያለው የምግብ ድጋፍ ጊዜያዊ ሳይሆን፤ ቋሚ የአእምሮ ስንቅና ትጥቅ ነው ሲሉ ግንባር ላይ ያሉ የኢትዮጵያ ጥምር ጦር አባላት ተናገሩ።

የወልድያ ከተማና አካባቢዋ ነዋሪ ግንባር ላይ ላለው የኢትዮጵያ ጥምር ጦር ሕዝባዊ ደጀንነቱን አጠናክሮ ቀጥሏል። እኛ ከሞቀ ቤት ነው ያለነው ለዛሬው ጥሬ ቆልተን፥ ቂጣ ጋግረን እንበላለን። ለነገም አቡከተን እንጋግራለን በማለት በርካታ እናቶች የጋገሩትን እንጀራ ሳይሰስቱ ለግሰውታል።

እናቶች አክለውም የኢትዮጵያ ጥምር ጦር ልጆቻችን እኛን ብቻ በመጠበቅ እና ነጻ በማውጣት እንዳይወሰኑ፤ ተረግጠው ያሉ የትግራይ አካባቢ ምስኪኖችንም ነጻ እንዲታወጧቸው ሲሉ አሳስበዋል።

ግንባር ላይ በመፋለም የሚገኙት የኢትዮጵያ ጥምር ጦር አባላት በበኩላቸው ምሽግ ድረስ ምግብ አጥቅሶ እየላከ ያለ ሕዝብ የላከው ጊዜያዊ ምግብ ብቻ አይደለም ቋሚ የአእምሮ ስንቅና ትጥቅ ነው። የሕዝብ ድጋፍ ለእኛ ኩራትም፣ ደጀንም፣ ክብርም ነው ብለዋል አስተያዬት የሰጡን በራያ ግንባር የሚገኙ የኢትዮጵያ ጥምር ጦር አባላት።

እንዲህ ዓይነት ሕዝብ ባለቤቷ ኢትዮጵያ አትፈርስም። የፀረ-ኢትዮጵያውያን እና የባንዳዎች መፍረስ ግን አይቀርም። ጠላት ሲቅበዘበዙ በራሱ የማይነካውን ሁሉ እየነካ እየፈረሰ ነው። ምሱን እየቀመሰ ነው ብለዋል የኢትዮጵያ ጥምር ጦር አባላት።

ነሐሴ 25 ቀን 2014 ዓ.ም

ወልድያ ከተማ ኮሙኒኬሽን።