Get Mystery Box with random crypto!

አማራ ባንክ ሰኔ 11 2014 ስራዉን በይፋ እንደሚጀምር አስታወቀ። አዲስ አበባ፡ ሰኔ 06/2 | Amhara Bank S.c

አማራ ባንክ ሰኔ 11 2014 ስራዉን በይፋ እንደሚጀምር አስታወቀ።

አዲስ አበባ፡ ሰኔ 06/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በባንኩ የምረቃ እለትም 70 የተሟሉ ቅርጫፎች የባንክ አገልግሎት የሚሰጡ ይሆናል ተብሏል።

እሰከ ሰኔ 30 ባሉት ቀናቶች ባንኩ ቅርጫፎቹን ወደ ከ100 በላይ የሚያሳድግ መሆኑንም ገልጿል።

የባንኩ ቦርድ ሊቀመንበር አቶ መላኩ ፋንታ ሀገራዊ ለዉጡን ተከትሎ ሀገራዊ ኢኮኖሚዉን ለማሳደግ የተከፈተ ባንኩ ሲሆን በሀገሪቱ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ላይ አስተዋጽዎ ለማድረግ የተጀመረ ባንክ ነዉ ብለዋል።

የሕዝብ ባንክ መሆኑን አንስተዉ እሰካሁን በብሄራዊ ባንክ ደንብ መሰረት የአክሲዮን ሸያጭ የማድረግ ስራዎች መከናወናቸውን አንስተዉ በሁሉም የኢትዮጵያ አካባቢዎች አክሲዮኖች ተሽጠዋል ብለዋል።

የካቲት 2/2014 ዓ.ም ዋና እና ምክትለረ ስራ አስፈጻሚዎችን ማስመረጡን አንስተዋል።

የባንኩ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሄኖክ ከበደ በበኩላቸዉ እስከ ሰኔ 30 አጠቃላይ መቶ ቅርጫፎች ስራ እንደሚጀምሩ ጠቅሰዉ ሰኔ 11 ላይ በመክፈቻዉ 70 ቅርጫፎች ስራ ይጀምራሉ ብለዋል።

የሰራተኛ እና የስራ ቁሳቁስ ግብዓት የማሟላት ስራዎች ተሰርተዋል ሲሉ ገልጸዋል ዋና መሪ ቃሉን "ከባንክ ባሻገር "ብሎ የጀመረዉ አማራ ባንክ ማህበራዊ ሀላፊነቱን በስራዎቹ እንደሚወጣ አስታዉቋል።

እስከ ሰኔ 11 ባሉት ቀኖችም ባንኩ የፓናል ዉይይት፣ የደም ልገሳ እና ሌሎችም መርሀ ግብሮች እንደሚኖሩት አስታዉቋል።

ባንኩ የማህበራዊ አገልግሎቱን ለመወጣት እንዲያስችለዉ ሰኔ 11 ቀን ከጠዋቱ 12 ሰአት እስከ ምሽት 3 ሰአት ድረስ የአምበሳ ባስ ተጠቃሚዎችን ወጭ መሸፈኑን አስታዉቀዋል።

ተጠቃሚዎችም በእለቱም ያለምንም ክፍያ ተጠቃሚ መሆን እንደሚችሉም አስታዉቋል።

ባንኩ ከስድስት ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ስራዉን የጀመረ ሲሆን እስካሁንም ከ4 ቢሊየን ብር በላይ በስራ ላይ ማዋሉን ባንኩ አስታዉቋል።