Get Mystery Box with random crypto!

ውድ የአማራ ባንክ አክሲዮን ማህበር ባለአክሲዮኖች በሙሉ አማራ ባንክ አ.ማ እንኳን ለ2014 ዓ.ም | Amhara Bank S.c

ውድ የአማራ ባንክ አክሲዮን ማህበር ባለአክሲዮኖች በሙሉ
አማራ ባንክ አ.ማ እንኳን ለ2014 ዓ.ም አዲስ አመት እና የመስቀል በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!

አማራ ባንክ ምሥረታውን በማጠናቀቅ ስራ ለመጀመር ከሚያስፈልጉት ቅድመ ሁኔታዎች መካከል የባንኩ ዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት እና ዋና ስራ አስፈፃሚ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መስከረም 14/2014 ዓ.ም የፀደቀ ሲሆን፤ በቀጣይ ባንኩ ከብሔራዊ ባንክ ፍቃድ ለማግኘት እንዲያስችለው ባለአክሲዮኖች በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ ፊት ቀርባችሁ በባንኩ መመስረቻና መተዳደሪያ ደንብ ላይ ፊርማችሁን እንድታኖሩ ይጠበቃል።
ከዚህ ቀደም ውክልና የሰጣችሁ ባለአክሲዮኖች በወኪሎቻችሁ አማካኝነት የሚፈርምላችሁ ሲሆን፤ ውክልና ያልሰጣችሁ ባለአክሲዮኖች ግን በቅርብ ቀን በምናስታውቀው ቀንና ቦታ በመቅረብ ባንኩን ስራ ለማስጀመርና የባንኩ ባለአክሲዮኖች መሆናቸሁን ለማረጋገጥ መፈረም የሚጠበቅባችሁ መሆኑን እናስታውቃለን።

ለበለጣ መረጃ
0921943382
0921607902 ይደውሉ።

የአማራ ባንክ አክሲዮን ማህበር የዳይሬክተሮች ቦርድ