Get Mystery Box with random crypto!

በአፋር ክልል ሰላምና ልማትን ከማረጋገጥ አኳያ የተገኙ ስኬቶች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ መንግሥት ትኩ | Ahmed Habib Alzarkawi

በአፋር ክልል ሰላምና ልማትን ከማረጋገጥ አኳያ የተገኙ ስኬቶች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ መንግሥት ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል - አቶ አወል አርባ
********************

6ኛው የአፋር ክልል ምክር ቤት 2ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባኤ ዛሬ በሠመራ ከተማ ተጀምሯል።

የአፋር ክልል ርዕሰ-መስተዳድር አቶ አወል አርባ በክልሉ ባለፉት 6 ወራት በመልካም አስተዳደር፣ በማህበራዊና ኢኮኖሚ ልማት መስኮች የተከናወኑ ዐበይት ስራዎችን ለምክር ቤቱ በዝርዝር አቅርበዋል።

በሪፖርታቸው ባለፉት 6 ወራት ክልሉን ከአጎራባች አማራና ኦሮሚያ ክልሎች ጋር በሚያዋስኑ አካባቢዎች አልፎ አልፎ ያጋጥሙ የነበሩ ግጭትችን በማስቀረት የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን ለማጠናከር የሚስችሉ ስኬታማ ስራዎች ተከናውነዋል ብለዋል።

በተጨማሪም በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል የነበረው ግጭት በውይይት እንዲቋጭ መደረጉን አንስተው፤ ይህም አፋርን ጨምሮ የሁሉም ኢትዮጵያዊውያን ድል መሆኑን ለምክር ቤቱ አብራርተዋል።

የተገኘው ሰላም የበለጠ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የክልሉ መንግሥት የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል ያሉት ርዕሰ-መስተዳድሩ፤ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎችና የማህበረሰብ መሪዎችም የበኩላቸውን ገንቢ ሚና እንዲጫወቱ ጥሪ አቅርበዋል።

ከዚህም በጨማሪ በበጀት ዓመቱ በኢኮኖሚ ልማት መስክም ስኬታማ ስራዎች መከናወናቸውን ገልጸዋል።

ከነዚህም መካከል የሌማት ትሩፋት ስራዎችን ከማሳለጥ በተጨማሪ በስንዴ ልማት እንዲሁም የእንስሳትና የግብርና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የተሰሩ ስራዎች ጥሩ የሚባሉ መሆናቸውን አብራርተዋል።

በክልሉ በሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋዎች ለተጎዱ የህብረተሰብ ክፍሎች የዕለት ደራሽ እርዳታ በአግባቡ ተደራሽ እየተደረገ መሆኑንም ርዕሰ-መስተዳድሩ በሪፖርታቸው ገልጸዋል።