Get Mystery Box with random crypto!

ይህን ያውቁ ኖረዋል?... በኢትዮጵያ የቴምር እርሻ የሚገኘው አፋር ውስጥ ነው። በአፋር በየ | Ahmed Habib Alzarkawi

ይህን ያውቁ ኖረዋል?...

በኢትዮጵያ የቴምር እርሻ የሚገኘው አፋር ውስጥ ነው። በአፋር በየአመቱ ከረምት ላይ ከፍተኛ የቴምር ምርት ለገበያ ይቀርባል። የትም የማይገኝ አፋር ብቻ የሚገኝ የቴምር ዝርያ አለ እነሱም የአውሳ ቴምር እና የሃሪሳ ቴምር ይባላል። በተለይ ሃሪሳ ቴምር በጣም ተወዳጅ ሲሆን እንደሌላው ቴምር እርጥም ሳይሆን ደረቅ ቴምር ነው በጣም ጣፋጭም ነው። እና የአፋር የቴምር ኢንቨስት ቢደረግ ለሀገራችንም ከዛም አልፎ ለውጭ ገበያ ማቅረብ ይቻላል።

የግብዣ ጥሪ---የአፋር ምድር ለየትኛውም የእርሻ አይነት ለማረስ ምቹና ተስማሚ መሆኑ የማያቋርጥ የአዋሽ ወንዝ በመኖሩ ያለ ምንም ስጋት ኢንቨስት ማድረግ የምትችሉ በመሆኑ ማንኛውም ኢንቨስት ማድረግ ለሚፈልግ የክልሉ መንግስት የእርሻ መሬት አዘጋጅቷልና ወደ አፋር መጥተው ኢንቨስት እንድታደርጉ ተጋብዛችኋል። Ahmed Habib Alzarkawi

የተፈጥሮ ሃብታችን እና መሬታችንን በአግባቡ ከተጠቀምን እንኳን ለሀገራችን ለአፍሪካ እንበቃለን።