Get Mystery Box with random crypto!

ይህን ያውቁ ኖረዋል..! አሚሽ (Amish) ፦ በአሜሪካ ምድር ከዘመናዊ ቴክኖሎጂ ርቀው የሚኖሩ | Ahmed Habib Alzarkawi

ይህን ያውቁ ኖረዋል..!

አሚሽ (Amish) ፦ በአሜሪካ ምድር ከዘመናዊ ቴክኖሎጂ ርቀው የሚኖሩ ማህበረሰቦች!!!

መኪና አይወዱም፣መብራትም ግድ አይሰጣቸውም፣ትምህርትም ቢሆን ከስምንተኛ ክፍል በላይ ምን ያደርጋል ብለው “ትምህርት እስከ ስምንት” በሚል መርኽ ነው የሚኖሩት። ፎቶ? ኸረ ነውር ነው! አሚሾች ፎቶ መነሳት አንድን ሰው እራሱን አምላኪ እንዲሆን ይገፋፋዋል ብለው ስለሚያምኑ አይነሱም። ህይወታቸው በዋነኛነት በእርሻ ላይ የተመሰረተ ሲሆን ጠንካራ ማህበራዊ ስረአት ያላቸው ማህበረሰቦች ናቸው።

አሚሾች መነሻቸው አውሮፓ (ጀርመን፣ስዊዘርላንድ፣ሆላንድ) ቢሆንም በእምነታቸው ምክንያት ይደርስባቸው የነበረውን ጫና በመሸሽ ነበር ወድ ሰሜን አሜሪካ በተለይም ወደ ፔንስልቫኒያ የተሰደዱት። የዚህ ማህበረሰብ መስራች Jakob Ammann የተባለ ሰው ሲሆን የማህበረሰቡ መጠሪያ ስምም ከዚሁ ሰው ስም የተነሳ እንደሆነ ይነገራል።