Get Mystery Box with random crypto!

🌴Ãlwan .... ⭐️ الون ⭐️

የቴሌግራም ቻናል አርማ alwane_colors — 🌴Ãlwan .... ⭐️ الون ⭐️ Ã
የቴሌግራም ቻናል አርማ alwane_colors — 🌴Ãlwan .... ⭐️ الون ⭐️
የሰርጥ አድራሻ: @alwane_colors
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 842
የሰርጥ መግለጫ

👋የረበና ሰላም በናንተ ላይ ይሁን👋
« በብዕርህ መጣራት ባትችል በሰዎች ብዕር ተጣራ »
ለአስተያየት 👉 @Alwan_colors_bot

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-05-20 09:20:29 ትብብራችሁን እፈልጋለሁ።

ወንድማችን ሪያድ አብዱልጀባር
.
.

ላፕቶፕ ኮምፒውተሬ ለአቅሜ በላይ ለሆነ ችግር ተጋልጧል።
ድንገት ሁሉም የሥራና ተያያዥ ፋይሎቼ KXDE እና WDLO በሚሉ ቫይረሶች ተቆልፈውብኝ፣ ሥራ ካስፈቱኝ ከወር በላይ ሆነ። ስለሆነም ተያያዥ የ ransomware ወይም የ malware ችግሮችን የመፍታት ተሞክሮ ወይም እውቀት ያላችሁ ተሞክሯችሁን ብታጋሩኝ፣ የመፍትሔ ሐሳብ ብትጠይቁኝ እላለሁ።
ሌላኛው ደሞ permanently delete አድርጊያቸው የነበሩ አስፈላጊ የቪዲዮ ፋይሎች ነበሩኝ። በዳታ ሪከቨሪ ሶፍትዌር አማካይነት ሪከቨር ማድረግ የቻልኩ ቢሆንም፣ ቪዲዮዎቹ bad ፋይል ሆነው አልሰራ አሉኝ። የተለያዩ የቪዲዮ ሪፔር ማድረጊያ ሶፍትዌሮችን ብጠቀምም ውጤት ማግኘት አልቻልኩም። ውጤታማ የቪዲዮ ሪፔር ማድረጊያ ሶፍትዌር ካላችሁም እንዲሁ አለሁ ብትሉኝ፣ ወይም ጥቆማ ብትሰጡኝ ከብዙ ጭንቀት ትታደጉኛላችሁ።
ለትብብራችሁ ከወዲሁ ምስጋናዬን እንኩ

#ቢያንስ_ሼር_በማድረግ_ለሌሎች_እናስተላልፍ

ጥቆማ ያላችሁ ቤተሰቦቻችን @Jemseidbot ላይ ፃፉልን እናገናኛችኋለን
224 views06:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-10 06:20:32
Alwan..

<< የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ ወደ ጀነት ተመለከትኩኝ እና ብዙ#ሰዎችም_ድሆች መሆናቸውን አየሁ። >>

Alwane_colors
Alwane_colors
Alwane_colors
651 views03:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-03 21:16:23
Alwan.

وَكُلُّهُمْ ءَاتِيهِ يَوْمَ ٱلْقِيَٰمَةِ فَرْدًا
''ሁሉም በትንሣኤ ቀን ለየብቻ ኾነው ወደርሱ መጪዎች ናቸው፡፡''

(መርየም : 95 )

@Alwane_colors
@Alwane_colors
@Alwane_colors
1.0K views18:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-03 21:15:51 አላህ (ሱወ) ሰባት ነገሮችን ይወዳል

ተውበት ☆ “አላህ (ከኃጢኣት) ተመላሾችን ይወዳል” አል በቀራህ [2:222]

ጦሀራ ☆ “አላህ ተጥራሪዎችንም ይወዳል በላቸው፡፡”አል በቀራህ [2:222]

ተቅዋ ☆ “አላህ ጥንቁቆችን ይወዳልና፡፡” አተ ተውባ[9:4]

ኢህሳን ☆ “አላህም በጎ ሠሪዎችን ይወዳል፡፡” አል ኢምራን[3:134]

ተወኩል ☆ “አላህ በርሱ ላይ ተመኪዎችን ይወዳልና” አል ኢምራን[3:159]

ዐድል ☆ “አላህ በትክክል ፈራጆችን ይወዳልና፡፡”አል ማዒዳህ{5:42]

ሶብር ☆ “ ..”አላህም ትዕግስተኞችን ይወዳል፡፡”አል ኢምራን[3:146]


@Alwane_colors
@Alwane_colors
@Alwane_colors
843 views18:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-01 18:16:37
Alwan.

وَمِنَ ٱلَّيْلِ فَتَهَجَّدْ بِهِۦ نَافِلَةًۭ لَّكَ عَسَىٰٓ أَن يَبْعَثَكَ رَبُّكَ مَقَامًۭا مَّحْمُودًۭا
ከሌሊትም ላንተ ተጨማሪ የኾነችን ሶላት በእርሱ (በቁርኣን) ስገድ፡፡ ጌታህ ምስጉን በኾነ ስፍራ በእርግጥ ያቆምሃል፡፡

(Quran17:79)

@Alwane_colors
@Alwane_colors
@Alwane_colors
699 viewsedited  15:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-01 18:14:57 ጣፍጭ የሆኑ የሳሀቦች ታሪክ

ክፍል 6

(ሑዘይፋ ረዲየላሁ አንሁ)

*የሑዘይፋ ረ.ዐ የስለላ ተልዕኮ

~ ሑዘይፋ ረ.ዐ እንደገለፀው :- ''በኸንደቅ ጦርነት ግዙፍ የጠላት ጦር ጋር መጋፈጥ ነበረብን። የመካና የአጎራባች ጎሳዎች ስብስብ ኃይል ወሮናል። የመዲና አይሁዳውያን በኒ ቁረይዟ ከጀርባችን ሊወጉን በዝግጅት ላይ ነበሩ። ሁላችንም መዲናን ከጥቃት ለመከላከል በመውጣታችን ቤታችንን እና ቤተሰባችንን እንደሚዘርፉና እንደሚያስቸግሩ ተሰምቶናል። መናፍቃን ወደ መዲና ለመመለስ ነብዩን ﷺ ፈቃድ መጠየቅ ጀመሩ። ቤቶቻቸው ያለ ጠባቂ የቀሩ መሆናቸውን ና በአይሁዳውያንም ሊጠቁ ስለሚችሉ ጥበቃ እናድርግ የሚል የሀሰት ምክንያት አቀረቡ።


~ ለሁሉም ፈቃድ ሰጡ። በእነኛ የፈተና ቀናት አንድ ምሽት ከሌላው ጊዜ የተለየ የጨለማና ንፋስ ነበር። ከጨለማው ከፍተኝነት የተነሳ አንድ ሰው የገዛ እጁን እንኳን ማየት አይችልም ነበር። ንፋሱም እጅግ አደገኛ ነበር። መናፍቃን ወደ መዲና በመመለስ ላይ ናቸው። ሦስት መቶ ሰዎች ብቻ በተጠንቀቅ ለመወጋት ተዘጋጅተናል። ነብዩ ﷺ ወደ እያንዳንዳችን በመጠጋት ይጠይቁናል ። እኔ ራሴን የምከላከልበት የጦር መሣሪያ አልነበረኝም። ከብርድ የሚያድነኝ ልብስም አልነበረኝም። አንድ ትንሽ ፎጣ ቢጤ ብቻ ነበረኝ ከሚስቴ የተዋስኩት። ከጉልበቴ ሎሚ ላይ ጠመጠምኩት። ከዚያም በጉልበቴ ተንበረከኩ። የአላህ መልዕክተኛ ﷺ በአጠገቤ ሲያልፉ ' ማንነህ?' አሉኝ:- 'ሑዘይፋ ነኝ ' አልኳቸው።


~ ከብርዱ የተነሳ መቆም አልቻልኩም። ሀፍረት እየተሰማኝ ጉልበቴን ከመሬቱ ጋር ቸክዬ ቀረሁ። እርሳቸው ግን :- ''ሑዘይፋ ተነስ! ወደ ጠላት ካምፕ በመሄድም መረጃ ሰብስበህ ተመለስ ' አሉኝ። ከሁሉም ሶሓባ ለጠላት መመከቻ መሣሪያ የሌለኝ ፤ ራሴን ከብርድ ለመከላከልም ልብስ የሌለኝ እኔ ነበርኩ። ቢሆንም በፍጥነት በመነሳት ወደ ጠላት ካምፕ አመራሁ። የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ በማለት ጸለዩልኝ:- '' አላህ ሆይ! ከሁሉም አቅጣጫ አንተ ጠብቀው።' በቅጽበትም ፍርሃቴና ቅዝቃዜው ልቀቀኝ ።በሞቃታማ ና ሰላማዊ ክልል የምጓዝ መሰለኝ። ነብዩም ﷺ 'እነርሱም የሚሠሩትን ካጤንክ በኋላ በቶሎ ተመለስ። ሌላ እርምጃ እንዳትወስድ።' አሉኝ።

~ በጠላት ካምፕ ስደርስ የሚቀጣጠል እሳት ተመለከትኩ። ሰዎችም በዙሪያው ተቀምጠዋል። እያንዳንዱ ሰው እጁን በእሳቱ እያሞቀ ሆዱን ያሻል። የማፈግፈግ ድምጽ በሁሉም አቅጣጫ ይሰማል። ሁሉም ለጎሣ አባላት ዕቃቸውን እንዲጭኑና እንዲሸሹ በማሳሰብ ላይ ነው።


~ ድንኳናቸው በነፋስ ኃይል በሚገፉ ድንኳኞች ተነረተ። የድንኳኖቹ ገመድም ተበጣጠሱ። እንስሳዎች ቅዝቃዜውን መቋቋም ተስኗቸው መሞት ጀመሩ ። የጠላት ጦር አዛዥን አቡ ሱፍያንን ተመለከትኩት። ከእሳት አጠገብ እጁን በማሞቅ ላይ ነበር። ልገድለው አሰብኩ። ቀስቴን አነጣጠርኩ ። በቅጽበት ግን የነብዩን ﷺ ትዕዛዝ አስታወስኩ ። ቀስቴን ወደ ቦታው መለስኩ። በመካከላቸው ባለሁበት ወቅት ባዕድ ኃይል ሊኖር እንደሚችል የጠረጠሩ ይመስለኛል ። አቡሱፍያን ' በመካከላቸው ሰላይ እንዳይገባ። እያንዳንዳችሁ ከአጠገባችሁ ያለውን ሰው እጅ ያዙ።' በማለት ለፈለፈ ። በአጠገቤ ያለውን ሰው እጅ በቅፅበት በመጨበጥ ' አንተ ማን ነህ!' አልኩት።' እንዴ አታውቀኝም እገሌ እኮ ነኝ' አለኝ።


~ ከዚያም ወደ ነብዩ ﷺ ተመለስኩ ። የአላህ መልዕክተኛ ﷺ ሶላት ላይ ነበሩ። ከባድ ሁኔታ ሲያጋጥማቸው ምን ጊዜም የሚያቀኑት ወደ ሶላት ነው። ሶላት ሰግደው እንደጨረሱ በጠላት ካምፕ ያየሁትን በዝርዝር አቀረብኩላቸው ።

~ ሰላይ በመካከላችሁ ገብቷል በማለት ሰላዩን ለመያዝ ያደረጉትን ጥረት እንዴት እንዳከሸፍኩ ስነግራቸው የሚያምር ጥርሳቸውን መመልከት ችያለሁ...''። ፊዳከ አቢ ወ ኡሚ ያረሱለላህ !!

እኛም በጀነት ፊታቸውን ከነ ፈገግታቸው ከሚያዩት ያድርገን አሚን

#Bint_nassir

@Alwane_colors
@Alwane_colors
@Alwane_colors
826 views15:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-11 15:38:39
Alwan....

<< ትክክለኛ አማኝ ማለት እሱ ጥሩ ባህሪ ያለውና ለሚስቱ መልካም የሆነው ነው >>
{ ረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም}

@Alwane_colors
@Alwane_colors
@Alwane_colors
967 views12:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-08 06:39:59
Alwan...

በፎቶው የምትመለከቱት ወጣት ፍልስጤማዊው የነፃነት ታጋይ ዘከሪያ አዝ-
ዘቢዲ ይባላል።ዘከሪያ ከእስር ካመለጡት ስድስቶቹ መሃል አንዱ ነው።
ከሁለት አመት በፊት በወራሪው ፍርድ ቤት በቀረበበት ወቅት ነበር፤ልብ በሚስብ
የጀግና ፈገግታ ተሞልቶ ለዳኛው:-"ነፃ ሆኜ የምንገናኝበት ቀን ቅርብ ነው።"
ያለው።ሽብር የተፈጠረበት ዳኛውም በጥብቁ የጀልቡዕ እስር ቤት በእስር
እንዲማቅቅ ፈረደበት።
ታዲያ በእስር ቤቱ ለሁለት አመታት ያክል በተለየ ክፍል ውስጥ አሳለፈ።አለምን
ጉድ ያሰኘው ክስተት ከመከሰቱ ከአንድ ቀን በፊት ግን አሏህ የውህኒ ክፍሉን
እንዲቀይሩለት የእስር ቤት አዛዦችን አገራለት።በአዲሱ የእስር ክፍልም የምድር
ጉድጓዱን ቁፋሮ ሚሽን ከመጀመሪያው ጀምሮ ካስተባበረውና ከሃያ አመት በላይ
በእስር ቤቱ ከታሰረው ሙጃሂድ መህሙድ አል-አሪዳና አራት ጓደኞቹ ጋር አንድ
ክፍል ውስጥ ታሰረ።ከአንድ ቀን በኋላም እሱ ስድስተኛቸው ሆኖ ከእስር ቤቱ
አመለጡ።

Ibrahim Taj Ali

@Alwane_colors
@Alwane_colors
@Alwane_colors
957 views03:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-07 15:45:55
@Alwane_colors
@Alwane_colors
@Alwane_colors
772 views12:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-06 17:15:06 ፈጣሪ እውነት ነው!!

በጥንት ዘመን በአንድ አገር ውስጥ የሚኖር ንጉሥ ነበር። ይህ ንጉሥ ታዲያ በፈጣሪ መኖር አያምንም። ንጉሡ "ፈጣሪ በእውነት ያለ ሳይሆን ሰውች በሕልማቸው ወይም በሃሳባቸው የፈጠሩት ነው" ብሎ ነበር የሚምነው። በዚህም የተነሳ ፈጣሪ የሚለው ቃል በአገሪቱም ሆነ በቤተሰቡ ውስጥ እንዳይነገር የተቻለውን ጥረት ሁሉ ያደርግ ነበር።
ከዕለታት አንድ ቀን የንጉሡ ሚስት ወንድ ልጅ ትወልዳለች። ነገር ግን እናትየው በወሊድ ወቅት በተፈጠረባት የጤና ችግር ምክንያት ትታመምና ትሞታለች።
ንጉሡም የተወለደው ልጅ ስለ ፈጣሪ መስማትና ማስብ የለበትም በሚል ዓላማ ከሰዎች ተነጥሎ የሚያድግበትን ሁኔታ ማመቻቸት ይጀምራል። ለሕፃኑ የሚሆን ቤት በጣም ከፍታ ካለው ማማ ላይ ያሠራል። ሕፃኑን ልዑል የሚንከባከቡና የሚያስተምሩ አገልጋዮችን ይመድብለታል። አገልጋዮቹንና መምህሩን ለሕፃኑ የፈጣሪን ስም በምንም መልኩ እንዳይገልጹ መመሪያ ይሰጣቸዋል። ሁሉንም ነገር ባሰበው መንገድ አከናውኖ አጠናቀቀ። እንዲህ በማድረጉም ሕፃኑ በምንም መንገድ ስለፈጣሪ መስማትም ሆነ ማሰብ አይችልም ብሎ እርግጠኛ ሆነ።
ሕፃኑ ልዑል በዚህ መልኩ እየኖረ ሳለ ከዕለታት አንድ ቀን ንጉሡ ሕፃኑን ሊጎበኝ ማማው ቤት ላይ ይወጣል። በዚህን ጌዜ ሕፃኑ የሚመለከተው የሚያምሩ አበቦችንና የአካባቢውን የተፈጥሮ ሁኔታዎች ነበር። ሕፃኑ እርግቦች ሲበሩና ወራጅ ወንዞች አካባቢውን አቋርጠው ሲያልፉ የሚመለከተው ትእይንት እንደሚያስደስተው ከገጽታው ያስታውቅ ነበር። ወደ ውጭ እየተመለከተም ጭንቅላቱን ወደ መሬት ዝቅ ያደርጋል።
ንጉሡም በሕፃኑ ሁኔታ ተገርሞ ምን እያደረገ እንደሆነ ይጠይቀዋል። ሕፃኑም "ለፈጣሪዬ ምስጋና እያቀረብኩ ነው!" በማለት አስደንጋጭ መልስ ለአባቱ ይሰጠዋል።
በሕፃን መልስ በጣም የደነገጠው ንጉሡም "የቱን ፈጣሪ ነው የምታመሰግነው? ለመሆኑ ስለፈጣሪ ማን ነው የነገረህ?" ሲል በቁጣ ይጠይቀዋል።
ሕፃኑም "ማንም ስለፈጣሪ አልነገረኝም፤ በዚህ ተፈጥሮ ውስጥም የፈጣሪዬን ውበት እና እውነት በግልጽ እመለከታለሁ። ምክንያቱም እነዚህን የሚማርኩ ነገሮች የፈጠራቸው አለ ብዬ አምናለሁ፤ ይህንን ታላቅነቱን ሳስብ ደግሞ ጭንቅላቴን ዝቅ በማድረግ ለክብሩ ስል እሰግድለታለሁ" በማለት ለአባቱ ጥያቄ መልስ ስጠ።
ንጉሡ በሕፃኑ ንግግር ሁኔታ በጣም ደነገጠ። የሽንፈት ስሜት ውስጥ ሆኖም ወደ ኋላው አፈገፈገ። ትንሹ ልዑል አባቱ ፈጽሞ እንዳይሰማውና እንዳይስበው ይፈልገው የነበረውን ነገር ተፈጥሮን በማየትና በማድነቅ ብቻ ደረሰበት። ማንም ሳይነግረውና ሳያስተምረው የፈጣሪን መኖር አወቀ። ፈጣሪያችን እሱ በእርግጥም እውነት ነው!

@Alwane_colors
@Alwane_colors
@Alwane_colors
832 views14:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ