Get Mystery Box with random crypto!

በሰለፎች መንገድ

የቴሌግራም ቻናል አርማ alselfiy — በሰለፎች መንገድ
የቴሌግራም ቻናል አርማ alselfiy — በሰለፎች መንገድ
የሰርጥ አድራሻ: @alselfiy
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 254
የሰርጥ መግለጫ

💎«رَبَّنَا آتِنَا مِن لَّدُنكَ رَحْمَةً وَهَيِّئْ لَنَا مِنْ أَمْرِنَا رَشَدًا

♻️« ጌታችን ሆይ! ከአንተ ዘንድ እዝነትን ስጠን፤ ለእኛም ከነገራችን ቅንን አዘጋጅልን‼️
ወደ ቻናላችን ይቀላቀሉ
https://t.me/Alselefiy
ለአስተያየትዎ https://t.me/Alselefiygoldenislamicgroup

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-23 07:26:18 #ያአሏህ.....

በድቅድቅ ጨለማ ከአሏህ ጋር

ልትተኛ መብራቱን አጥፍተህ ሳለ
ወደ መኝታ ቦታህ እንደመጣህ


ከዚያ የአሏህን ታላቅነት አስተነተንክ
አሏህን ለማግኘት ሌላ መንገድ የለም
አሏህ ለባሪያው የፃፈለት መንገድ ቢሆንጅ!

መብራትን አጥፍተህ የነበረው ተነስተህ
ከዚያም ዑዱ ወደ ሚደረግበት ቦታ
ሂደህ ዑዱ አደረክ

ከዚያም (ከብረህ) ቆመህ ቁርዓን
መቅራት ጀመርክ ከዛ ሱጁድ ወረድክ


#መሀላን_ሀላል_ባደረገው_አሏህ_እምላለሁ!

ከዚህ ሱጁድ የበለጠ ዱኒያ ላይ
ምንም ነገር ደስታ ሚሰጥ ነገር የለም


አሏህ ለነብያችን እንድህ ይላቸዋል፦

(አሸናፊ አዛኝ በኾነው(ጌታህ) ላይም ተጠጋ።

በዚያ ለሶላት በቆምክም ጊዜ
በሚያይህ። በሰጋጆች ውስጥ
መዘዋወርህንም (በሚያየው ጌታህ
ላይ ተጠጋ)።

ጌታችን እንዲህ ይላል፦
ባት የሚገለጥበትን (ከሓዲዎች)
ወደ መስገድም የሚጠሩበትንና
የማይችሉበት (ቀን) አስታውስ።


➴ዓይኖቻቸው የፈሩ ውርደት
የምትሸፍናቸው ሲኾኑ፤ (ወደ ስግደት
የሚጠሩበትን)እነርሱም(በምድረ ዓለም)
ደህና ሆነው ሳሉ ወደ ስግደት
በእርግጥ ይጠሩ ነበሩ።

አንተ አሁን ሰላም እያለህ ወደ
ሱጁድ ትጠራለህ ነገ የውመል
ቂያማህ መስገድን እስክትችል


እዚህ ዱኒያ ላይ ሳለህ
የአሏህን ፊት ፈልገህበት ስገድ


(ጡባ) ለዚያ ቀብሩን ከመግባቱ
በፊት ብርሀንን ለሞላው (በሶላት)።

يارب.......
#ቀልባችንን_የተገራች_አድርግልን!
↷⇣ ⇣↷
https://t.me/Alselfiy
23 viewsedited  04:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-22 08:09:48
37 views05:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-22 03:59:05 #አትፍራ

የሚሆነው ላይቀር ለምን ትፈራለህ?

➴አንዳንዱ ሰው...
እራሱን በራሱ ይገድላል

በጭንቀት ነፍሱ የማትችለውን
ይጭንባታል

የጭንቀት የፍርሃት ኑሮ ይኖራል

ከበሽታ ይፈራል.....የሆነ የሚፈልገውን
ስራ እንደማይወፈቅ አስቦ ይፈራል

#በቃ_ሁሌ_ይፈራል...........

የዚህ መፍሔው...
ፍረሃት ከሞት አይከላከልም

ነገር ግን በሕይወትህ ተጣቅመህ
እንዳትኖር ያደርግሃል

ወንድሜ ሆይ አትፍራ!!
↷⇣ ⇣↷
➣https://t.me/Alselfiy
277 views00:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-20 07:05:27
.
የቁርኣን ግብዣ

••┈┉┅━❀ ❀━┅

የጌታቹን ቃል ተሰምቶ አይጠገብም ተጋበዙልኝ
61 views04:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-19 17:14:10
« #ያኡኽቲ_ፊሏህ ! »
ኸይር ሲመጣ አመስጋኝ ሸር ሲመጣ ሶብርን
ትዕግስትን ተላበሺ! ምንም እንኳን ነገራቶች እንዳሰብሻቸው ባይሆኑም ታጋሽና አመስጋኝ እንስት ሁኚ።

#ይሉናል_መካሪዎቻችን!
408 viewsedited  14:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-19 13:38:45وَٱلَّذِينَ إِذَآ أَنفَقُوا۟ لَمْ يُسْرِفُوا۟ وَلَمْ
يَقْتُرُوا۟ وَكَانَ بَيْنَ ذَٰلِكَ قَوَامًۭا ❝


❝ እነዚያም በለገሱ ጊዜ የማያባክኑ የማይቆጥቡትም ናቸው፡፡ በዚህም መካከል ( ልግስናቸው ) ትክክለኛ የኾነ ነው ፡፡ ❞

سورة الفرقان - 67

ከዚህ የቁርዐን አንቀፅ ከምንወስዳቸው
አስተምህሮዎች መካከል


1 ) ለጋስነት
2 ) አባካኝ አለመሆን
3 ) ቋጣሪ አለመሆን
4 ) ሚዛናዊ መሆን

የሙዕሚን ባህሪያቶች መሆናቸውን ነው፡፡

አሏህ ከተግባሪዎች ያድርገን!
↷⇣ ⇣↷
https://t.me/Alselfiy
https://t.me/Alselfiy
401 views10:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-18 22:42:00 إشراقة صباحية
‏لا تعلق سعادتك بغير الله ، فإن الحبيب
يجفو ، والقريب يبعد ، والحي يموت ،
والمال يفنى ، والصحة تزول ، ولا يبقى
إلا الحي القيوم

ደስታህን ከአሏህ ውጭ ሌላ ነገር
ላይ አታንጠልጥል ምክንያቱም ወዳጅ
ዞር ይላል፤ የቅርቡም ይርቃል፤ ህያው
ይሞታል፤ ገንዘብ ያልቃል፤ ጤንነትም
ይወገዳል፤ አል ሀይ አል ቀዩም እንጂ
ማንም አይቀርም

https://t.me/Alselfiy
362 views19:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-18 07:13:19 በመጀመሪያው ቀን ትውውቅ እንዴት ልገመግመው?

#ተንቢሀት_ካውንስሊንግ (001)

ጥያቄዬ የሚከተለው ነው ፤
በመጀመሪያ ትውውቅ የምርጫዬን ዓይነት
እንደሆነ እንዴት ልገመግመው እችላለሁ?

ስብዕናውን ለመረዳት እና አስተሳሰቡን
ለማወቅስ ምን መጠየቅ ወይም መናገር
አለብኝ?

የተሳሳተ ምርጫ ላይ ወድቄ የስሜት ጉዳት
እንዳይደርስብኝ መጠንቀቅ እፈልጋለውና
እባካችሁ ምክር ለግሱኝ።

::::::::::::::

➴#ምላሽ:– ከሁሉም በፊት ከአላህ ጋር ያለሽ
ትስስር በጣም ጠንካራ ይሁን፤ ከአላህጋር
ያለሽ ትስስር ጠንካራ ከሆነ እና ዘወትር ዱዓ
ካልተለየሽ የጉዳዬችሽ ፍጻሜ ሁሉ ያማረ
እንደሚሆን አያጠራጥርም። አላህ እርሱን
ታዛዦችን ወደ መልካም መንገዶች ይመራል፡፡

ﻭَﻣَﻦ ﻳَﺘَّﻖِ اﻟﻠَّﻪَ ﻳَﺠْﻌَﻞ ﻟَّﻪُ ﻣِﻦْ ﺃَﻣْﺮِﻩِ ﻳُﺴْﺮًا
«አላህንም የሚፈራ ሰው ከነገሩ ሁሉ ለርሱ
መግራትን ያደርግለታል» ጦላቅ 4

ውዷ እህታችን!
በጥያቄሽ ላይ እንደቀረበው አይነት የህይወት
መንገድን የሚያስቀይሩ መንታ መንገዶች
ሲገጥሙን ምርጫን ወደ አላህ ማስጠጋት
መልካም መሸሸጊያ ነው፡፡ ፍርሃትና ስጋትን
ሁሉ ያጠፋል፡፡ አላህ ትክክለኛውን ምርጫ
እንዲያሳይሽ ከብዙ እና ብርቱ ዱዓ ጋር
ደጋግመሽ [እስቲኻራ] አድርጊ፡፡

ትዳር ላሠቡ ሁለት ጥንዶች የመጀመሪያ
ትውውቅ እና መተያየት በመሀላቸው
መፈቃቀድ እና ተቀራራቢ የነፍስ ፍሰት መኖሩን
ለመፈተሽ ወይም ለማወቅ የሚጠቅም ነው፡፡
በዚህ ሂደት ዐይን በሚያየው አካላዊ ገፅታ
አሊያም በንግግርና በውይይት መጣጣምና
መፈቃቀድ ሊፈጠር ይችላል።

ስታይው የምችደሰችበትና የምትወጅው
አይነት መሆኑንም ማስተዋል ያስፈልጋል ፡፡

በዚህ የመጀመሪያ ትውውቅ ወቅት አላህ
ከአንቺ ጋር ሁሌም እንደሆነ አስቢ፤ ራስሽን ብቻ
ሁኚ፤ ምን መናገር ወይም መጠየቅ እንዳለብሽ
በማሰብ ስሜትሽን አትረብሺ፡፡ እነዚህ ነጥቦች
ወደ ለትክክለኛው ምርጫ ያግዙሻል፡፡

ነገር ግን ይህ ሰው ትክክለኛ ምርጫ መሆኑን
ለማረጋገጥ ቀጥተኛ እና ቀጥተኛ ባልሆኑ
መንገዶች መሠረታዊ የሆኑ በርካታ ወሳኝ
ነጥቦችን መመርመር እና ማጣራት ያስፈልግሻል፡፡

1) ለእምነቱ ያለው ትኩረት ምን ያህል ነው? ሰላት በህይወቱ ውስጥ ምን ቦታ አለው?ከሰዓት ከመዘውተር እና ከሁኔታ አንፃር በትክክል ሰላቱን ይጠብቃል?

ትክክለኛውን የትዳር አጋር ለማግኘት እነዚህ ጥያቄዎች ትክክለኛውን መልስ ማግኘት አለባቸው፡፡ ሰላቱን የሚጠብቅ ሰው ከአላህ ጋር ዘወትር የተሳሰረ ነው ፤ ከአላህገር የተሣሠረ ሰው አብሮ ከሚኖረው ሰው ጋር መልካም ግንኙነት እንደሚኖረው ይታመናል፡፡

2) ለወላጆቹ ምን ያህል መልካም ነው? ለወላጆቹስ በጎ ነውን? ይህን ጥያቄ ቀጥሎ ማቅረብ ያስፈልጋል፡፡
ለወላጆቹ መልካም ከሆነ አላህን የሚፈራ እና የአላህን ውዴታ የሚፈልግ ሰው ለመሆኑ አንድ ማስረጃ ነው፡፡

፨ ከነዚህ ምላሾች በመነሣት ከዚህ ሰው ጋር የህይወት ጥምረት መፍጠር እምነት የሚጣልበት መሆኑን እና አለመሆኑን መገምገም ይቻላል፡፡

3) ከወንድሞቹ ፣ ከእህቶቹ ፣ ከጓደኞቹ፣ ከስራ ባልደረቦቹ አንዲሁም በዙሪያው ከሚገኙ ሰዎች ጋር ያለው ግንኙነት ምን ይመስላል? ተወዳጅ ሰው ነው? ከሰዎች ጋር ያለው ግንኙነት ጤናማ እና ያልተረበሸ ነው? ለሰዎች ያለው አቀራረብ ለዛ አለው?

፨ የእነዚህ ጥያቄዎች ምላሾች ደግሞ የማህበራዊ ግንኙነቱን ስኬታማነት ያሳያሉ፡፡

4) የህይወት ታሪኩ ምን ይመስላል? ቢያንስ ስለዚህ አጭር ነገር ማወቅ የኀላ ማንነቱን ለማወቅ ጠቃሚ ነው። ዕውቀት በመፈለግ ባሳለፈባቸው ትምህርት ቤቶች ፣ ሪዝቅ በመፈለግ ባሳለፈባቸው የስራ ቦታዎች እንዲሁም ኑሮውን ባሳለፈበት መንደር ትቶት ያለፈውን የህይወት ጠረን ጥሩ ይሁን መጥፎ ማሽተት ያስፈልጋል፡፡

፨ መልካም ሽታ የመልካም ስነምግባር ውጤት ሲሆን መጥፎ ሽታ የመጥፎ ስነምግባር ውጤት ነው፡፡

5) ተቀዳሚ ምልከታሽ ዲን ይሁን ፤ ገንዘብን ወይንም ማህበራዊ ክብርን ከዲን አታስቀድሚ፤ የነብዩ /የአላህ ሠላም እና ሰላት በእርሳቸው ላይ ይሁን/ የምክር ቃል ይህን ይላል፦

قال النبي صلى الله عليه وسلم: «إذا أتاكم من ترضون دينه وخلقه فانكحوه» الحديث

«እምነቱን እና ስነምግባሩን የወደዳችሁት ሰው የትዳር ጥያቄ ሲያቀርብ ተቀበሉት»

አደራ የምንልሽ ቤተሰቦችሽ የትዳር ጥያቄ ያቀረበውን ሰው አስመልክቶ የሚሰጡትን አስተያየት ቦታ እንዳትነፍጊው ነው። አስተያየታቸው በህይወት ተሞክሮዎች የተፈተሸ በመሆኑ ጠቃሚነቱ አያጠራጥርም፡፡
የምታማክሪዉን ሰው ልታውቂ ይገባል። በእድሜ ላንቺ እኩያ ወይም ካንቺ ያነሱ ያልበሰሉ ወጣቶችን ካማከርሽ፤ ቁሳዊ መመዘኛን ተጠቅመው ወይም ከቅናት ስሜት በመነሳት የማይበጅሽን ሀሳብ ሊለግሱሽ ስለሚችሉ ተጠንቀቂ።

ሁልጊዜም ለአላህ ትእዛዛትና ገደቦች ጥንቁቅ ሁኝ፡፡ አላህን መፍራት ያማረ ፍፃሜ የሚገኝበት ብቸኛ መንገድ ነው።

ﻭَاﻟْﻌَﺎﻗِﺒَﺔُ ﻟِﻠﺘَّﻘْﻮَﻯٰ

«መልካም መጨረሻም ለጥንቁቆቹ ናት!» ጣሀ 132

ተንቢሐት
↷⇣ ⇣↷
https://t.me/Alselfiy
445 views04:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-18 07:12:19
አንብበነውም ከሆነ ደግመን
ማንበባችን ማስተዋልን ይጨምርልን
ቢሆንጅ አይቀንስብንም...እናምብባት
84 views04:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-18 00:57:06 أَلَمْ يَجِدْكَ يَتِيمًا فَآوَىٰ (6) وَوَجَدَكَ ضَالًّا فَهَدَىٰ (7) وَوَجَدَكَ عَائِلًا فَأَغْنَىٰ (8) فَأَمَّا الْيَتِيمَ فَلَا تَقْهَرْ (9) وَأَمَّا السَّائِلَ فَلَا تَنْهَرْ (10) وَأَمَّا بِنِعْمَةِ رَبِّكَ فَحَدِّثْ (11)

محمد الغزالي

ጣፍጭ ቲላዋ ግብዣ ⓵


https://t.me/Alselfiy
89 viewsedited  21:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ