Get Mystery Box with random crypto!

ወንድሜ ሴትን ለሀራም ፍቅር ጠይቀህ እንቢ ስላለችህ አትናደድ ከጓደኞችህም ያነስክ ወይም ፋራ የሆን | አል ሙስሊም 🌴🌴🌴

ወንድሜ ሴትን ለሀራም ፍቅር ጠይቀህ እንቢ ስላለችህ አትናደድ ከጓደኞችህም ያነስክ ወይም ፋራ የሆን እዳይመስልህ ይልቁንስ አላህ የሀርምን መንገድ ዘግቶ ለሀላል መንገድ እያዘጋጀህ ስለሆነ ልትደሰት ይገባህ።

ስለዚህ ላንተ ያዘነልህ ጌታ ለጓደኞችህም እንዲያዝንላቸው ዱዐ አድርግላቸው የተሰጠህን ኒዕማ አስተንትን አስተውል ጌታህንም አመስግን በኸይር ስራ ላይም ፅና።


እህቴ አንቺም የወንድ ጓደኛ የለኝም እኔን ማንም አይወደኝም ቆንጆ አይደለውም እያልሽ አላህ የሰጠሽን ትልቅ ኒዕማ ጥለሽ ለሀራም እራስሽን አትጋብዢ።

ምናልባት የሴት ጓደኞችሽ ብዙ ለሀራም ፍቅር ይጠየቁ ይሆናል አንቺ ግን በዚህ ሊሰማሽ አይገባም አላህ ከዚህ የትርምስ አለም ስላወጣሽ አመስግኚ።