2022-08-05 00:32:54
► #ቁርአንን_ለመሀፈዝ_የሚጠቅሙ_6_ምክሮች
① ►ኢኽላስ የሁሉም ነገር ቁልፍ ነው
ስራ ላይ ኢማን እና ኢኽላስን ማጣት ትልቅ ክስረት ውስጥ ያስገባል ። የለፋህበትን የደከምክበት ሁሉ በአንዴ ያወድምብሃል ። ስለዚህ ልብህን ተጫንና በውስጥህ ኢኽላስ‥ ኢኽላስ‥ ኢኽላስ እያልክ ወደ 2ተኛው ምክር‥
②► አላማ
አንድን ነገር ለመስራት አላማዬ ብለህ ከያዝክ ምንም ነገር አላማህን ከማሳካት አያግድህም ። ብቻ አንተ ውስጥህ ላይ ያለውን ፍላጎት ፣ ቆራጥነት ፣ ሀይልን እና ምኞትህን ቀስቅሰህ እችላለሁ በልና ወደ 3ተኛው ምክር‥
③ ►ትኩረት
ዛሬ ላይ መለኩል መውት መጥቶ በእርግጠኝነት ከ2 ወር በኋላ ትሞታለህ ቢልህ ምን ታደርጋለህ??
- አንዱ በ2 ወር ቁርአን ሀፍዜ እጨርሳለሁ ይላል ። ሌላው ደግሞ በ1 ወር ሀፍዤ እጨርስና ቀሪውን ኢባዳ ብቻ አደርጋለሁ ይላል‥
ይህ ሁሉ ችሎታ እና ሀይል አሁን የት አለ?
๏ ሰው በተሰጥኦ ምናምን ይለያል ብለህ አታስብ ። በተወሰነ % ቢኖርም ግን ሁላችንም ውስጥ ምኞት ፣ ፍላጎትና ጉጉት አለ ። እያንዳንዳችንም ፍላጎታችን ላይ መድረስ እንችላለን ብለህ እራስህን አሳምነህ ወደ 4ተኛው ምክር‥
④ ►የምትሀፍዝበትን ጊዜ ወስነህ ለየው
አብዛኛውን ጊዜ ቁርአን ለመሀፈዝ የተሻለ ጊዜ ነው የሚባለው ሱሁር የሚበላበት ጊዜ ነው ። ከዛ ቀጥሎ ከፈጅር ሰላት በኋላ ነው ።
ሱሁር ላይ የተሻለበት ምክኒያት : የሰው ልጅ በዛ ሰአት ከእንቅልፉ ሲነቃ አእምሮው ለመቀበል ክፍትና ዝግጁ ስለሚሆን ነው ።
⑤ ►አንድ አይነት ሙስሀፍ/ቁርአን ብቻ መጠቀም
የአንድ አንድ ሙስሀፎች ገፅ አቀማመጥ ይለያያል ። እዚህኛው ሙስሀፍ ገፅ ላይ ያየኸው አንቀፅ በዛኛው ሙስሀፍ ገፅ ለይ ደግሞ ሌላ አንቀፅ ሊኖር ይችላል እና ሁሌም የምትቀራበትን ሙስሀፍ አዘጋጅ ።
⑥ ►ወንጀሎችን መራቅ
የወንጀል ፅልመት እና የእውቀት ብርሃን በአንድ ቦታ ላይ ሊሰበሰቡ አይችሉም ።
- የሰው ልጅ ወንጀል ሲሰራ ወንጀሉ ሀዘን ፣ ጭንቀት እና የመሰሰሉ ነገሮች ስለሚያመጣበት ሀሳቡ ሁሉ ይቀየርና ከበጎ ነገራቶች ያርቁታል ። ስለዚህም በተቻለን አቅም ወንጀል ከሚባሉ ነገሮች መራቅ ይኖርብናል ።
2.0K views21:32