Get Mystery Box with random crypto!

#WachemoUniversity የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለመስጠት | ALL STUDENTS EXAMS AND INFO

#WachemoUniversity

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለመስጠት የሚያስችላቸውን ዝግጅት እንዲያደርጉ የትምህርት ሚኒስቴር ማሳሰቡ ይታወሳል፡፡

የ2014 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በሁለት ዙር ከመስከረም 30/2015 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚሰጥ ይታወቃል።

ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በተቋሙ የሚሰጠውን ፈተና አስመልክቶ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ሀብታሙ አበበ (ዶ/ር) ከሁሉም ምክትል ፕሬዝዳንቶች እንዲሁም ከኮሌጅ እና የትምህርት ቤት ዲኖች ጋር ውይይት አድርገዋል።

በዩኒቨርሲቲው ዋና ግቢ፣ በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የዱራሜ ካምፓስ እና በንግስት እሌኒ መሀመድ መታሰቢያ ኮምፕሬንስቪ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከ20 ሺህ በላይ ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ ተገልጿል።

ሁሉም የኮሌጅ እና የትምህርት ቤት ዲኖች የትምህርት ሚኒስቴር ባወጣው የፈተና አስፈፃሚዎች ምልመላ መነሻ መስፈርት መሰረት የፈታኝ መምህራን ምልመላ እንዲያደርጉ ፕሬዝዳንቱ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

ሚኒስቴሩ ከመስከረም 28 እስከ ጥቅምት 17/2015 ዓ.ም በሁሉም የዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ምንም አይነት መደበኛ ተማሪ እንዳይገኝ ማለቱ ይታወሳል።

╔════════════╗
JOIN:
@alluexams
JOIN:
@alluexams
╚════════════╝