Get Mystery Box with random crypto!

ዋሪዳ ነብያችንﷺ እና ሰሓባዎቻቸው በእስልምና የመጀመሪያው የሆነውን ሒጅራ ከመካ ወደ መዲና ባደረ | ያሙፍረደል ዓለም ሙሀመድﷺ ቻናል

ዋሪዳ

ነብያችንﷺ እና ሰሓባዎቻቸው በእስልምና የመጀመሪያው የሆነውን ሒጅራ ከመካ ወደ መዲና ባደረጉ ግዜ ሠይደል ውጁድﷺ እና ረፊቃቸው ሠይዲና አቡበከር(ረ.ዐ) በቀናት ወደሁዋላ ዘግይተው ነበር::

ቀድመው መዲና የገቡት ሙሓጂሮች እና አንሳሮች በነብዩﷺ ናፍቆት ልባቸው ተንጠልጥሎ ህፃን አዋቂው፣ሴት ወንዱ ከቤቱ ወጥቶ መጠባበቅ ሆነ ስራው:: የካኢናቱ ሁሉ ኢማምﷺ በደረሱ ግዜ በዛ ሁሉ ኸልቅ ልብ ላይ ዋሪዳው ወረደ ሁሉም በአንድነት:-(ከሠይዲ እንደሰማሁት ከዛ በፊት ተብሎ የማያውቅ የሆነ አዲስ መድህ)
"ጠለዓል በድሩ ዓለይና ሚን ሠኒየቲል ወዳዕ
ወጀበ ሹክሩ ዓለይና ማዳዓ ሊላሂ ዳዕ" እያሉ ነብዬንﷺ እየመደሁ ድቤ እየደለቁ እያጨበጨቡ ሐቢቢን ተቀበሏቸው:: አሊይሂ አፍደሉ ሰላት ወልሰላም
በሀገራችን እንዲሁም ከሀበሻ ውጪ ያሉ አካቢር አውሊያዎች ነቢንﷺ የመደሁት ልመድህ ብለው አስበው ግጥም ገጥመው ሳይሆን ግጥሙ እራሱ መጥቶ በሉኝ ነው የሚላቸው:: ለምሳሌ ያክል ሸምሰዲነል አብሬትይ ክብሪተል አሕመር የሰለዋት ኪታባቸው መግቢያ ላይ እንዲህ ብለዋል:-በሸዋል ወር ከዙሁር ሶላት ተርቲብ አዝካሬ(ኢባዳ)ዬ በሁዋላ ምንም አይነት ሌላ ንግግር ሳላስከትል ተኛሁ...የዚህ ሰለዋት ዋሪዳ በመናሜ ሐርፈን ሐርፍ ተከትቦ መጣ...እኔ አፍደል (የተሻልኩ) (ምርጥ) የሆንኩ ሶለዋት ነኝ, ክብሪተል አሕመር እባላለው ቅራኝ አለኝ እኔም ቀራሁት... ብዙ እንግዳ እና ግሩም የሆኑ ብዙ አስራሮችን አየሁባት ይላሉ ጌቱዋ:: ለእኛ አይነቱ የሚገባ ጉድ አይሁን እንጂ እያንዳንዱ ሐርፍ በዋንጫ ሆኖ በልዩ ልዩ መጠጥ ተመስሎ መጣ ይላሉ... ኧረ እንደው ከለሩንም ይናገራሉ::
ሌሎችንም እጅግ ብዙ ብዙ አብሬትይ ከመድሆቻቸ እና የሰለዋት ኪታቦቻቸው መግቢያ ወይንም መጨረሻ ላይ የፃፉዋቸውን መጥቀስ ይቻላል::

@mahbubil