Get Mystery Box with random crypto!

መውሊድ ይቻላል ለሚልህ ይህንን አቅርብለት ጥያቄ አንድ መውሊድ ማክበር አላህን መታዘ | 📚ሀዲሦችና አጫጭር የቁርአን አንቀፆች መልቀቂያ ቻነል 📚

መውሊድ ይቻላል ለሚልህ ይህንን አቅርብለት


ጥያቄ አንድ
መውሊድ ማክበር አላህን መታዘዝ ነው ወይስ አላህን ማመፅ በለው?

①) መውሊድ አላህን ማመፅ ነው ካለ አላህን ለማመፅ መውሊድ ማክበር አይቻልም በማለት ፋይሉ መዝጋት ይቻላል። ነገር ግን በፍፁም ይህንን አይሉም።

②) አላህን መታዘዝ ነው ካለ (የሚሉትም ይህ ነው) ወደ ሁለተኛው ጥያቄ ትሸጋገራለህ

ጥያቄ ሁለት
ይህንን አላህ መታዘዝ ነው ኢባዳ ነው የምትለው መውሊድ የአላህ መልእክተኛ ያውቁት ነበር ወይስ አያውቁትም ዘንግተውታል በለው።

①) መልእክተኛው አያውቁትም ዘንግተውታል ካለ ይህ ግልፅ የሆነ ኩፍር ነው። ነገር ግን ይህንን በፍፁም አይሉም።

②) የአላህ መልእክተኛ አውቀውታል ካለ (የሚሉትም ይህ ነው) ወደ ቀጣዩ ጥያቄ ትሻገራለህ።

ጥያቄ ሶስት
መውሊድ የአላህ መልእክተኛ አውቀውት ከሆነ ለህዝባቸው አድርሰውታል ወይስ አላደረሱትም በለው።

①) ለህዝባቸው አላደረሱትም ካለ አላህ ታማኝነታቸውን የገለፀውን ነብይ በመጥፎ መጠርጠር ስለሆነ ግልፅ የሆነ ኩፍር ነው። ነገር ግን ይህንን አይሉም።

②) ለህባቸው አድርሰውታል ካለ፦ በሙግትህ ላይ እውነተኛ ከሆንክ መረጃ አምጣ በለው? ነገሩ እዚህ ላይ ያበቃል። መረጃ ደሞ ከየትም ሊያመጣ አይችልም።

ምክንያቱም መውሊድን በተመለከተ አንድም የቁርአን ወይም የሀዲስ መረጃ የለምና። ይህም ማረጋገጫው እነሱ ራሳቸው መውሊድ ቢድአ ሀሰና ነው ማለታቸው ነው። መረጃ ያለው ነገር ደሞ ቢድአ ሀሰና ሊሆን አይችልምና።

ነገር ግን አላዋቂዎችን ለማታለል ከቁርአን ከሀዲስ መረጃ አለ ብለው ሊያጣቅሱ ይችላሉ። እውነታው ግን ለመውሊድ ብለው የሚያመጧቸው የቁርአንና የሀዲስ መረጃዎች በነሱ ላይ መረጃ የሚሆኑ እንጂ ለነሱ መረጃ የሚሆኑ አይደሉም።

http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru