Get Mystery Box with random crypto!

የ 2022/2023 የክረምት የዝውውር መስኮት (መርካቶ) በሊቨርፑል ፡ እሄ የክረምት የዝውውር መ | All Sport

የ 2022/2023 የክረምት የዝውውር መስኮት (መርካቶ) በሊቨርፑል

እሄ የክረምት የዝውውር መስኮት (መርካቶ) ለሊቨርፑል ትልቅ ኪሳራ የሆነ እና ጠንካራ የሆነ ነበር!

የሊቨርፑል የክረምት የዝውውር መስኮት (መረካቶ) የጀመረው በትልቅ ሽንፈት ሳይሆን በትልቅ ኪሳራ ነው

ሊቨርፑል ከነገነ ሌላ ኮከብ ተጫዋች ማጣት አይፈልግም ፤ አንድ ጊዜ ኮከቡን አጥቷል ከነገነ ሌላ ኮከብ ማጣት አይፈልግም ፤ በሜዳ ላይ ብዙ ጊዜ በደንብ የሚጫወት ፤ በሚፈልገው ጊዜ እንደጦር መሪ የሚጫወት ፤ ከቡድኑ ጋር በደንብ የሚከለከል እና ኳስን በደንብ የሚቆጣጠር ተጫዋች ፤ ጨዋታ የሚያሟሙቅ እና ብዙ ጎሎች የሚያስቆጥር ፤ ኳስ እንዴት መቆጣጠር/መያዝ የሚችል እና የቡድኑ ግብ አግቢ ነው ያጣል ሊቨርፑል እሱም ሳዲዮ ማኔ ነው ፤ እሄም የክረምት ዝውውር ትልቁ የሊቨርፑል ኪሳራ ያደርገዋል

የሳዲዮ ማኔ ቦታ የሚሸፍን ተጫዋች ማግኘት በጣም ከባድ ነው ፤ እና ሉዊስ ዲያዝ የሳዲዮ ማኔ ቦታ ለመሸፈን ገና ብዙ ይቀረዋል። ሊቨርፑል በክረምቱ ዝውውር መስኮት (መርካቶ) ብዙ ተጫዋች ቢያስፈርሙም ያው አሉታዊ ነው የሚሆነው

የዳርዊን ኑኔዝ አጀማመር አሪፍ ነው በቀይ ባይወጣ ኑሮ ዳግሞ በጣም አስደናቂ ይሆን ነበር። ኑኔዝ ቢያንስ ለሊቨርፑል እድል/የራስ መተማመን አስገኝቷል። ቢያንስ አዲሱ ሰዋሬዝ ይሆናል ብዬ አምናለሁ። ኑኔዝ በሳላህ ጎን ከሆነ በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ጠንካራ መሆን ይችላል።

ወጣቱ ፋቢዮ ካርፈልሆ ከፉልሃም ነው የመጣው ፤ በየጨዋታው በተሳተፈ ቁጥር ጎበዝ (በጣም ችሎታ ያለው) እንደሆነ ይሰማሃል። ትንሽ ተጫዋች ቢሆንም ለቡድኑ ማገዝ (ማደገፍ) ይፈልጋል። በአሰልጣኝ ዩርገን ክሎፕ በማሰልጠኑ ልዩ ( ጎበዝ ፣ ጠንከራ) ተጫዋች ያደርገዋል።

በውድድር አመቱ መጀመሪያ ላይ ይፋ የሆነው የቡድኑ ችግር የመሀል ሜዳው ክፍል ሲሆን ቡድኑ በቀላሉ ኳሱን ከቡድኑ ሜዳ ወደ ተጋጣሚ ሜዳ የሚያንቀሳቅስ አማካኝ እንደሚያስፈልገው ግልፅ እንደሆነ ታውቋል። የፊት መስመርን የሚረዳ ተጫዋች እንዳሚያስፈጋውም ግልፅ ነው።

በመጨረሻው የክረምቱ ዝውውር መስኮት (መርካቶ) ሰዓት አርተር ሚሎን አስፈረሙ። እሄ ብራዚላዊ በጣም ችሎታ ያለው ተጫዋች ነው። በባርሴሎና ድንቅ ነበር። በባርሴሎና ይቆያል ተብሎ ይጠበቅ ነበር ነገር ግን ጁቬ ችሎታውን አይተው አስፈረሙት ነገር ግን እንዳተጠበቀው አልነበረም እሄም ባልተጠበቀ ሁኔታ ሊቨርፑል በመጨረሻ ሰዓት አርተር ሚሎን እንዲያስፈርሙቴ ቻሉት። ከዮርገን ክሎፕ ጋር ሲሰራ ችሎታው እንዳሚያገኝ እርግጠኛ ነኝ።

ነገ ከ TOP 6 ክለቦች ውስጥ የማን ሊቀርብ ትፈጋለችሁ?

ማንችስተር ዩናይትድ
ሊቨርፑል
ማንችስተር ሲቲ
ቶተንሃም
አርሰናል

ቼልሲ