Get Mystery Box with random crypto!

ሪያል ማድሪዶች የአውሮፓ ሱፐር ካፕ አሸናፊ ሆነዋል ! የ2022ቱ የአውሮፓ ሱፐር ካፕ የዋንጫ ጨ | All Sport

ሪያል ማድሪዶች የአውሮፓ ሱፐር ካፕ አሸናፊ ሆነዋል !

የ2022ቱ የአውሮፓ ሱፐር ካፕ የዋንጫ ጨዋታ የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ አሸናፊውን ሪያል ማድሪድ ከዩሮፓ ሊግ አሸናፊው ኢንትራክ ፍራንክፈርት ጋር በሄልሲንኪ ኦሊምፒክ ስታድየም ባገናኘው ጨዋታ ሪያል ማድሪድ 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል።

ለሎስ ብላንኮሶቹ ግቦቹን ዴቪድ አላባ እና ልማደኛው ካሪም ቤንዜማ አስቆጥረዋል።

ይህንንም ተከትሎ የስፔኑ ሀያል ክለብ ሪያል ማድሪድ ለአምስተኛ ጊዜ የአውሮፓ ሱፐር ካፕን ማሸነፍ ችሏል።

ጣልያናዊው ዝምተኛ አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ ይህን ጨዋታ ማሸነፉን ተከትሎ 4 የአውሮፓ ሱፐር ካፕ ዋንጫን ማሸነፍ የቻለ የመጀመሪያው አሰልጣኝ ሆኗል።