Get Mystery Box with random crypto!

የታላቁ አዛኝ የአለም ነብይ ጣፋጭ ታሪክ | Alif media

የታላቁ አዛኝ የአለም ነብይ ጣፋጭ ታሪክ

#ፀሀፊ_አብድልቃድር_እና---- #አንዋር

[ክፍል 5]

በካዕባ ግንባታ መሳተፋቸው

ካዕባ በአላህ ስም፣አላህን በብቸኝነት ለማምለክ የተገነባ የመጀመሪያው ቤት ነው።አባታችን ነብዩላህ ኢብራሂም(ዐ.ሰ) ከጣኦት አምልኮ ጋር ከፍተኛ ፍልሚያ ካደረጉ በኋላ ከአላህ በሆነ ትዕዛዝ ካእባን አነፁ።

وإذ يرفع إبراھيم القواعد من البيت وإسماعيل ربنا تقبل منا إنك أنت السميع العليم

" #ኢብራሒምና እስማኤልም 'ጌታችን ሆይ!ከእኛ ተቀበል።አንተ ሰሚውና አዋቂው ነህና' የሚሉ ሲሆኑ ከቤቱ መሰረቶቹን ከፍ ባደረጉ ጊዜ (አስታውስ)።"

( አል- በቀራህ 2፤127)

ካእባ ከዚህ በኋላ ለብዙ አደጋዎች ተጋልጠዋል።ነብያችን ﷺ በነብይነት ከመላካቸው ከጥቂት አመታት በፊት መካን ያጥለቀለቀው ሐይለኛ።ጎርፍ ይጠቀሳል።የአላህ መልዕክተኛ ﷺ በነብይነት ከመላካቸው በፊት ካዕባን ለማደስ በተደረገው ጥረት ላይ በንቃት ተሳትፈዋል፤በትከሻቸው ድንጋይ እየተቀበሉ ያቀብሉ እንደነበር ተዘግቧል።ያኔ እድሜያቸው 35 አመት እንደነበር ዘገባዎች ያመለክታሉ።

ቡኻሪ እንደዘገቡት ጃቢር ኢብን አብደላህ(ረ.ዐ) የሚከተለውን ሀዲስ አስተላልፈዋል፡-

لما بنيت الكعبت,ذھب النبي صلي الله عليه وسلم والعباس ينقلان الحجارت,فقال العباس للنبي صلي الله عليه وسلم:اجعل إزارك علي رقبتك,فخر علي الأرض وطمحت عيناه الي السماء فقال: أرني إزاري فشده عليه

"ካእባን በሚገነባ ጊዜ ነብዩ ﷺ እና አጎታቸው ዐብባስ (ረ.ዐ) ድንጋይ ያቀብሉ ነበር ዐብባስም ለነብዩ ﷺ "ሽርጥህን ከአንገትህ ላይ ደልድለህ ተሸከም" አሏቸው።ነብዩም ﷺ እንደተባሉት ሲያደርጉ ራሳቸውን #ስተው ወደቁ።ዐይናቸው ወደላይ ተንጋጠጠ።'ሽርጡን አቀብሉኝ'አሉና ከወገባቸው ላይ ታጠቁት።'

አላህ ይህን ያደረገው ሐፍረተ ገላቸውን ሌላ ሰው እንዳያየው ለመከላከል ነው።ይህ ክስተት እኚህ ሰው ለታላቅ ጉዳይ #የታጩ መሆናቸውን አመላካች ነው።

ጥቁሩን ድንጋይ ወደ ቦታው የመመለስን ክብር ለማግኘት በጎሳዎች መካከል የተነሳውን ውዝግብ በማፍታታቱ ሒደትም ነብያችን ﷺ ትልቅ ሚና ተጫውተዋል።ውዝግቡ ወደ ጦርነት ሊያመራ ተቃርቦ ነበር። የበኒ ዐብዱዳርና የበኒ ዐድይ ጎሳዎች በደም የተሞላ ገበታ አቅርበው ለክብራቸው በጋራ ለመፋለም እጃቸውን ከገበታው ውስጥ በማስገባት ቃል ተገባቡ።ቁረይሾች ውዝግቡን ለመፍታት ለአራት ወይም ለአምስት ቀናት ቢቀመጡም አልተሳካላቸውም። በመጨረሻም አቡ ኡመያህ አል-መኽዙሚ የተባለ ሰው፡- "ወገኖቼ ሆይ! አትወዛገቡ።ሁላችሁም የተስማሙበትን ሰው ዳኛ አድርጉ" ሲል ሀሳብ አቀረበ። "በተቀደሰው ካእባ በር መጀመሪያ ለሚገባው ሰው ዳኝነት እናድራለን" ሲሉም ተስማሙ።ያ ሰው ታማኙ ሙሐመድ ﷺ ሆኑ።" ይህ ታማኝ የሚሰጠንን ብይንስ በደስታ እንቀበላለን"አሉ።ጉዳዩን አጫወቷቸው። እርሳቸውም ኩታቸውን ዘረጉ።ሁሉም ጎሳዎች የኩታውን ጫፍ እንዲይዙ አዘዙ።ድንጋዩን አነሱና ከኩታቸው ላይ አስቀመጡት።እንዲያነሱም አዘዟቸው።ከሚቀመጥበት ቦታ ላይ ሲደርስ እርሳቸው ድንጋዩን ያዙና አስቀመጡት።ይህ ክስተት የነብዩን አዎንታዊ ስብእና፣ጥበባቸውንና የላቀ ደረጃቸውን ያሳያል።ታዲያ ወገኖቻቸው መልዕክታቸውን ላለመቀበል ለምን ያን ያህል አንገራገሩ።

የአላህ መልክተኛ ﷺ ተቀጣጥሎ የነበረውን የጦርነት እሳት ማጥፋታቸው አራት እውነታዎችን ይከስትልናል፡-

አዎንታዊነት የነብዩ ሙሐመድ ﷺ ስብዕና መሰረታዊ አካል ነው።በካዕባ ግንባታም ሆነ በሌሎች የማሕበረሰባቸው ጉዳዮች ላይ ያሳዩት የነበረው የላቀ ተሳትፎ ከዚህ ባህሪያቸው የመነጨ ነው።

ጉዳዮችን የሚያስኬዱበትን፣ችግሮችን የሚፈቱበትን እጅግ አስደናቂ ጥበብ ያሳያል።በተለይም ይህን ጥበብ የከበረ የሽምግልና ሒደት ያከናወኑት በመካከላቸው ውዝግብ በተነሱባቸው አጋጣሚዎች ሁሉ ብዙ ደም ከመፍሰሱ በፊት እርቅ በሚያወርዱ ጎሳዎች መሀል መሆኑ ደግሞ ለድርጊታቸው የበለጠ ድምቀት ይሰጠዋል።

ከቁረይሾች ዘንድ የነበራቸውን የላቀ የክብር ደረጃ ያመላክታል።"ታማኙ"(አል-አሚን) በሚል ማዕረግ ይጠሯቸው ነበር።

ከአላህ ዘንድ መልዕክት ወርዶላቸው እርሱን ማድረስ በጀመሩ ጊዜ የነዚህ ወገኖቻቸው ልቦች በክህደት መሞላታቸው፣በማስተባበልና በማወክ ጥሪያቸውን ማስተናገዳቸው በጣም ያስገርማል።በየትኛውም ቦታና ዘመን የሚገኙ የእውነት ተጣሪዎችን የሚቀናቀኑ ወንጀሎችን እኩይ ባህሪም በጉልህ ያሳያልልልልልልል።


ይህን የነብያችንን ﷺ ትልቅ ታሪክ አንብበን ስንጨርስ እኛ ጋር ብቻ እንዲቀመጥ ሳንፈቅድ ላላወቁትና ላልሰሙት ይህን ውድ ታሪክ እንድናሰማ ትልቅ አማና ጥለንባችሗል።

@Alif_media_1

ይ ላ ሉን