Get Mystery Box with random crypto!

ዉድ ሙስሊም ወንድሞቼና እህቶቼ አሰላሙአለይኩም ወራህመቱሏሂ ወበረከትሁ أسَـــــلَــ | አል ሂዳያ የየቲሞች መርጃና በጎ አድራጎት ጀማአ 0993632424//0703136300አዲስ አበባ

ዉድ ሙስሊም ወንድሞቼና እህቶቼ

አሰላሙአለይኩም ወራህመቱሏሂ ወበረከትሁ

أسَـــــلَــمُــــعَــــلَـــيـكُم
وَرَحـــــمَــت ألَـــــلَّـــــهِ
وَبـَـــــرَكَــــتـــــه‍ُ
እዴት ናቹህ የአሏህ ሰላምና ጥበቃ ከናተጋር ይሁን

ኢንሻ አሏህ አዲት ነገር ላስታዉሳቹህ
አል ሂዳያ በጎ አድራጎት ጀማአ ሴቶችንም ወንዶችንም ያካተተ ጀማአ ሲሆን
እየተመሰረተ ያለበት ዋናና ብቸኛ አላማ የተቸገሩ ወገኖቻችንና የቲሞችን እንርዳ ነዉ ኢሻ አሏህ

የተመሰረተበት አላማ
▬▬▬▬▬▬▬▬
(1ኛ ) የተቸገሩ እናቶችንና ወገኖቻችንን ስንረዳ በተለያዩ መገዶች ሲሆን

(1ኛ)አቅመ ደካማ የሆኑ እናቶቻችንን ቤታቸዉ ድረስ በመሄድ ለአንድ ወር ድረስ የሚበቃቸዉ የቤት አስቤዛና ልብስ የቤት እቃወች የመሰሳለሱትን ይዘንላቸዉ በመሄድ የቤታቸዉን ልብሶችና ብርድ ልብሶቻቸዉን በማጠብና ቤታቸዉን በማፅዳት እዲሁም ቤታቸዉ ቀለም የሚያስፈልገዉ ከሆነ  ቤታቸዉንም ቀለም በመቀባት እድሳትም የሚያስፈልገዉ ከሆነ ቤታቸዉን በማደስ እደዚሁም  የመብራትና የዉሀ መክፈል አቅቷቸዉ ለተቸገሩ ቤተሰቦች አዋተን በመክፈል እዲዚሁም ጉሊት ለሚሰሩ እናቶቻችን የሚሰሩበትን ቦታ በክረምት በዝናብና በጭቃ  እዳይቸገሩ በበጋ ደሞ በፀሀይ እዳይሰቃዩ የሚሰሩበትን ቦታ በማስተካከል እዲሁም ስራ ለሌላቸዉ ወገኖቻችን የስራ እድል መፍጠር የሊስትሮ እቃም ካስፈለጋቸዉ ገዝተን በመስጠት ጀምሎም መስራት ለሚፈልጉ ወገኖቻችንም ሙሉ እቃዉን ገዝተን በመስጠት ስራ ማስጀመር

(2ኛ) የቲሞችን ስንረዳ እናትና አባት ምንም ቤተሰብ የሌላቸዉን የቲሞችን ብቸኝነት እደይሰማቸዉ ከቤት ወጣ አድርገን ወደ መናፈሻና እነሱን ሊያስደስቱ የሚችሉ ሀላል የሆኑ ቦታወች በመዉሰድ የቲምነታቸዉን እዲረሱ እህትህ ነኝ ወንድምሽ ነኝ በማለት እነሱን በማስደሰት እደዚሁም አቅማችን ከፈቀደ እራሳችንን ችለን አንድ አንድ የቲም ልጅ በመያዝ በየ ወሩ ሂደን በመዘየርና የሚያስፈልጋቸዉን አልባሳትም ሆነ ጫማወችን በመግዛት በወር አንድ ጊዜ በመዘየር በዚ መልኩ የቲሞችን መርዳት እንረዳለን

(3ኛ) በተለያዩ አካባቢወች የሚሰሩ መስጂዶችና ኢስላማዊ ተቋማት ባሉበት ድረስ በመሄድ ስራ መርዳት መድረሳ ሊሆን ይችላል መስጂድ ሊሆን ይችላል ሙሉ በሙሉ የመስጂድ ምጣፍ በማጠብና መስጂዱን ግቢዉን ማፀዳትና መስጂዱ ቀም መቀባት የሚያስፈልገዉ ከሆነ የቀለም መቀባት ስራና ችግኞችን በመስጂዱ ዙሪያ መትከል  እደዚሁም አዳዲስ የበሚሰሩ መስጂዶችጋ በመሄድ መስጂዱ የሚያስፈልገዉን የስራ አይነት ማገዝና መርዳት እደዚሁም ለተለያዩ መስጂዶችና መድረሳወች ቁርአአኖች ኪታቦች ኢስላማዊ መፀሀፎች ገዝቶ መስጠትና ገዝታቹህ መስጠት ለምትፈልጉ አህለል ኸይሮች ወገኖች አማናችንን ተወተን ተረክበን ወስደን ቁርአንና ኪታብ ለሚያስፈልጋቸዉ መስጀዶችና መድረሳወች ማስረከብ

እነዚህን እርዳታወች ለመስጠት ዝግጁ ሆነን በጎ አድራጎት ጀማአችንን እየመሰረትን እንገኛለን
እና መሳኪኖችን ሰብስቦ ሰደቃ ማብላት
እደዚሁም አቅማችን ከፈቀደና እስፖሰር የሚሆነን ባለሀብቶችና አህለል ኸይሮችን ካገኘን ወደ ክፍለሀገርም ሂደን እርዳታ የመስጠትም ፍቃደኛ ነን አላማዉም አለን

አል ሂዳያ በጎ አድራጎት ጀማዓ ትልቁ አላማወቹ እነዚ ናቸዉ




ኑ ተባብረን ባለን አቅም የቲሞችንና የተቸገሩ ሙስሊም ወገኖቻችንን እንርዳ
በልብስ
በገዘብ
በአስዜዛ
በጉልበት
በሀሳብና
በተለያዩ በቤት ቁሳቁሶች መርዳት ትችላላቹ

አባል መሆን ለምትፈልጉ
ለበለጠ መረጃ
tel:
0993632424
tel:
0703136200
ወይም በኢቦክስ
@RidAmirsab

ሰደቃ ወጀልን ታብሳለች ረሱል (ﷺ)
ጉሩፓችንን መቀላቀል ከፈለጉ

አል ሂዳያ የየቲሞች መርጃና በጎ አድራጎት ጀማአ

https://t.me/ALHidayaTv/19929