Get Mystery Box with random crypto!

ሙስሊም ያልሆኑ ሴቶችን ማግባት አይበረታታም። አምላካችን አላህ በተከበረው ቃሉ በቁርኣን ላይ | አል ሂዳያ የየቲሞች መርጃና በጎ አድራጎት ጀማአ 0993632424//0703136300አዲስ አበባ

ሙስሊም ያልሆኑ ሴቶችን ማግባት አይበረታታም።


አምላካችን አላህ በተከበረው ቃሉ በቁርኣን ላይ በማኢዳህ ምዕራፍ አምስተኛ አንቀፅ ላይ የኪታብ ባለቤቶችን ሴት ማግባት እንደሚፈቀድ ነግሮናል። በዚህ የሚያስተባብል ሙስሊም አይኖርም።

ነገር ግን ምንም እንኳ የተፈቀደ ቢሆንም የሚበረታታ ግን አይደለም። ታላቁ የዘመናችን ዓሊም አልኢማም ኢብኑ ባዝ በዚህ ጉዳይ ተጠይቀው ከሰጡት ማብራሪያ መካከል የተወሰነውን ላጋራችሁ ወደድኩ።

«فيجوز للمسلم أن ينكح المحصنة من اليهود والنصارى،
ከአይሁድና ከክርስትና እምነት ተከታይ ተከታይ የሆነችን ንጹሕ (ጥብቅ) ሴት ማግናት ለሙስሊም ወንድ ይፈቀድለታል።
لكن تركها أولى وأفضل والاكتفاء بالمسلمات؛
ነገር ግን መተው (እርሷን አለማግባቱ)ማ በሙስሊሟ ሴት መብቃቃቱ እጅግ በጣም የተሻለና በላጭ ነው።
لأن نكاحها قد يجر الزوج إلى دينها، وقد يجر أولادها إلى النصرانية واليهودية ؛
ምክንያቱም እርሷን ማግባት ባልዮውን ወደርሷ እምነት እንዲያዘነብል ያደርገዋልና፤ ልጆቿንም ወደ ክርስትናና አይሁድ እንዲቀየሩ ያደርጋልና።
ولهذا كره ذلك جمع من الصحابة أصحاب النبي ﷺ وخافوا من ذلك،
ለዚህም ሲባል ከነቢዩ ﷺ ባልደረቦች መካከል ሁሉም ይህንን ጠልተውታል። ከዚህ (መዘዝ) ፈርተዋል።
وإلا ..... هن حلال بنص القرآن الكريم،
ከዚያ ውጭ ግ   በተከበረው ቁርኣን ማስረጃ መሠረት ፍቁድ ናቸው።
إذا كن محصنات عفيفات معروفات بالبعد عن الفواحش وعن الزنا حرائر لا مملوكات، فإنه يتزوجها المسلم ولو كان قادراً على مسلمة،
ንጹሕ፣ ጥብቅ፣ ከመጥፎ ነገርና ከዝሙት የራቀች በመሆኗ የታወቀች ከሆነች፣ ባሪያ ያልሆነች ጨዋ ከሆነች ሙስሊሟን ማግባት ቢችል እንኳ ሙስሊም ወንድ ሊያገባት ይችላል።
لكن نكاحه للمسلمة أولى وأفضل وأسلم وأبعد عن الفتنة له ولأولاده، نعم.
ነገር ገወን ሙስሊሟን ሴት ማግባት የተሻለና የበለጠ፣ ለርሱም ሆነ ለልጆች ከፊትና ነፃ ለመሆንና ለመራቅ የተሻለ ነዉ።


በአጭሩ ይህ ጉዳይ ምንም እንኳ የተፈቀደ ቢሆንም ከሶሐቦች ጀምሮ አንጋፋ ዑለሞች ጭምር በበርካታ ምክንያቶች ጠልተውታል።
ለምሳሌ: በሐይዽ ጊዜ እንደ ሙስሊም ሴት አትታጠብም፣ ከአጅነቢይ ወንድ አትርቅም፣ ቤተ ክርስቲያን ትመላለሳለች፣ ምናልባትም ስዕላ ስዕልና መሰል ኮተቶች ቤት ውስጥ ታመጣለች፣ በዓሏ ሲደርስ ማክበሩ… አስቡት የሚወለዱት ልጆች ላይ ሊፈጠር የሚችለውን አሉታዊ ጫና!

ሲጀመር ከማትሰግድ ሴት ጋር አብሮ ማደር፣ ቤተ ክርስቲያን ሂዳ ተሳልማ መጥታ አንተ ፈጅርን ሰግደህ መጥተህ ከርሷ ጋር መሆን አይደብርም በአላህ!
ደግሞ የምንታዘበውም ተጨባጭ አለ። አንዳንድ ሰዎች ቀስ በቀስ እናሰልማታለን ብለው አግብተው ከነ ልጆቻቸው የከፈሩ አሉ። ሲጀመር ትዳር የምትፈልግ ሙስሊም ሴት ጠፍታ ነው ይህቺኛዋ የምትገባው? ሲቀጥል የተፈቀደችው ከዝሙትና ከመጥፎ ነገር የጸዳችዋ እንጂ ዝም ብላ ማንኛዋም አይደለችም። ታዲያ አሁን እንደዛ አይነት ትገኛለች? ሲሰልስ አህለል ኪታብ የሚባሉት በኢንጂልና በተውራት የሚያምኑት ናቸው። እንደ እኛ ሃገር ተጨባጭ ከመጣን ግን ሁሉም ሊባል በሚችል መልኩ ጣዖት አምላኪ ናቸው። አህለል ኪታብ ናቸው/አይደሉም የሚለው ሌላ የክርክር ርዕስ ነው የሚሆነው። ስለዚህ ወንድሜ ሽራሽ ልብህን ከዚህ ዝንባሌ አውጣውና ሙስሊም አጋርህን ፈልግ።

ሲረብዕ ምንም እንኳ ይሄ ነገር ቢፈቀድም፤ ነቢያችን ﷺ ያዘዙን የዲን ባለቤቷን እንድናስቀድም ነው። በአልቡኻሪይ: 4802 እና በሙስሊም: 1466 ላይ ከአቡ ሁረይራህ  የተዘገበውን ሐዲሥ ተመልከት። እንኳን ከካፊሯ ከሙስሊሞቹ ሴቶች ራሱ የዲን ባለቤቷን ምረጥ ነው የተባለው። ዝም ብላ ሙስሊም ስለሆነች ብቻ አይደለም። በነገራችን ላይ እያወራን ያለነው ሙስሊም ወንድ አህለል ኪታብ የሆነችን ሴት ማግባት ይችላል ስለሚለው ጉዳይ እንጂ አህለል ኪታብ ያልሆነችን የትኛዋም ሴት ማግባት እና ሙስሊም ሴት አህለል ኪታብ ቢሆን እንኳ ወንድን ማግባት ያለምንም ጭቅጭቅ የማያመናታ እርም ነው።

ለላጤዎች ሁሉ አላህ ትክክለኛዋን ሙስሊም ይወፍቃቸው እያልኩ የጽሑፌን ጭብጥ በዚህች በገጣሚው ግጥም ላስርግ።


زواجُ النَّصَارى قبحُهُ متزايدٌ *** يؤدِي إلى كُفرِ البنيـنَ مؤكَّدا
ومَنْ يرضَ كُفرَ ابنٍ له فهو كَافرٌ *** وإنْ زعَمَ الإسْلامَ قَولاً مفنَّدا
وقـد يكـفـر الزوج اتباعاً لزوجهِ *** فيدخلَ في نارِ الجَحيمِ مخلَّدا
عليكَ بذاتِ الدين إن كنتَ راغباً *** زواجاً صحيحاً تبدُ فيه مسدَّدا
وذَرْ عنكَ أهلَ الكفر واحذرْ زواجهمُ *** فشَرهموا يبدوا كثيراً مُندَّدا
وأولادُ هذا العقدِ ليسوا لرشدةٍ ***  فيكثرُ جيلُ الخبثِ فَرعَاً ومَحتَدا

https://t.me/HiDAYATV
https://t.me/HiDAYATV