Get Mystery Box with random crypto!

ስንቶታችን ነን ቤተሰቦቻችን እረጋ ለስለስ ባለ መልኩ ወደ ተውሒድ ጥሪ ያደረግነው? የተውሒድ | Al HiDAYA MidiA የተበዳይ ሙስሊሞች ጉዳይ ያሳስበኛል📚ተዉሂድ የሁለት ሀገር የስኬት 🔑ቁልፍ ነዉ📖

ስንቶታችን ነን ቤተሰቦቻችን እረጋ ለስለስ ባለ መልኩ ወደ ተውሒድ
ጥሪ ያደረግነው? የተውሒድ አባት
ኢብራሒም አባዬ እያለ አባቱ ወደ
ተውሒድ ሲጠራው እንዲህ ይላል


إِذْ قَالَ لِأَبِيهِ يَا أَبَتِ لِمَ تَعْبُدُ مَا لَا يَسْمَعُ وَلَا يُبْصِرُ وَلَا يُغْنِي عَنكَ شَيْئًا

ለአባቱ ባለ ጊዜ (አስታውስ) «አባቴ ሆይ! የማይሰማንና የማያይን ከአንተም ምንንም የማይጠቅምህን (ጣዖት) ለምን ትግገዛለህ

يَا أَبَتِ إِنِّي قَدْ جَاءَنِي مِنَ الْعِلْمِ مَا لَمْ يَأْتِكَ فَاتَّبِعْنِي أَهْدِكَ صِرَاطًا سَوِيًّا

«አባቴ ሆይ! እኔ ከዕውቀት ያልመጣልህ ነገር በእርግጥ መጥቶልኛልና ተከተለኝ፡፡ ቀጥተኛውን መንገድ እመራሃለሁና፡፡

يَا أَبَتِ لَا تَعْبُدِ الشَّيْطَانَ ۖ إِنَّ الشَّيْطَانَ كَانَ لِلرَّحْمَٰنِ عَصِيًّا

«አባቴ ሆይ! ሰይጣንን አትግገዛ፡፡ ሰይጣን ለአልረሕማን አመጸኛ ነውና፡፡

يَا أَبَتِ إِنِّي أَخَافُ أَن يَمَسَّكَ عَذَابٌ مِّنَ الرَّحْمَٰنِ فَتَكُونَ لِلشَّيْطَانِ وَلِيًّا

«አባቴ ሆይ! እኔ ከአልረሕማን ቅጣት ሊያገኝህ ለሰይጣንም ጓደኛ ልትኾን እፈራለሁ፡፡»
///ሱረቱ መርየም///

ወደ ተውሒድ ሰዎችን ስንጣራ ሊሰድቡን፦ ሊያመናጭቁን፦ ሌላም ነገር እንደሚሰሩ ማወቅ አለብን።
እና አባቱ ተውሒድን ተቀበለ እንዴ ላ እንደው ማስፈራራት ጀመረ።


قَالَ أَرَاغِبٌ أَنتَ عَنْ آلِهَتِي يَا إِبْرَاهِيمُ ۖ لَئِن لَّمْ تَنتَهِ لَأَرْجُمَنَّكَ ۖ وَاهْجُرْنِي مَلِيًّا

(አባቱም) «ኢብራሂም ሆይ! አንተ አምላኮቼን ትተህ የምትዞር ነህን ባትከለከል በእርግጥ እወግርሃለሁ፡፡ ረዥም ጊዜንም ተወኝ» አለ፡፡
(((((ሱረቱ መርየም))))

ባይቀበሉንም ትግስት ልናረግ ጥሩ ንንግግር ልንናገራቸው ይገባል አሁንም ኢብራሒም የራሱ ጉዳይ ብሎት አልሄደም እንዲህም አለው።


قَالَ سَلَامٌ عَلَيْكَ ۖ سَأَسْتَغْفِرُ لَكَ رَبِّي ۖ إِنَّهُ كَانَ بِي حَفِيًّا

«ደህና ኹን፡፡ ወደፊት ከጌታዬ ምሕረትን እለምንልሃለሁ፡፡ እርሱ ለኔ በጣም ርኅሩኅ ነውና» አለ፡፡
///ሱረቱ መርየም////
=
@AlhidayaMidi