Get Mystery Box with random crypto!

‍ #አንድ_አፍታ ምክር ከጥበበኛው ሉቅማን ለልጁ #ምክር_2 #ልጄ_ሆይ ፧ | ሀድራ ጉድ ይዛለች

‍ #አንድ_አፍታ

ምክር ከጥበበኛው ሉቅማን ለልጁ
#ምክር_2

#ልጄ_ሆይ ፧ ጥበብ (እውቀት ) ምስኪኖችን የነገስታት ደረጃ አድርሳለች፡፡

#ልጄ_ሆይ ፧ አደራህን በብድር ላይ ; ብድር የቀን ውርደት የማታ ጭንቀት ነው ፡፡

#ልጄ_ሆይ ፧ የማይረዳን ከማስረዳት ቋጥኝን ከቦታው ማንሳት ይቀላል ፡፡

#ልጄ_ሆይ ፧ ባወከው ነገር እስከምትሰራ ያላወከውን አትማር ፡፡

#ልጄ_ሆይ ፧ መጥፎ ጎረቤት ከከባድ ብረት በላይ ይከብዳል ;መራራ ነገሮችን ሁሉ ቀምሻለሁ ከድህነት በላይ መራራ ነገር አልቀመስኩም፡፡

#ልጄ_ሆይ ፧ አንድን ሰው ወንድም ለማድረግ ከፈለክ መጀመሪያ አስቆጣው በቁጣው ጊዜ ካለፍክ …ካልሆነ ተጠንቀቀው ፡፡

#ልጄ_ሆይ ፧ በሰው ቤት ውስጥ ከሆንክ አይንህን ጠብቅ፤ በስብስብ መካከል ከሆንክ ምላስክን ጠብቅ ፤ በሰላት ውስጥ ስትሆን ልብህን ጠብቅ ፡፡
"
"
የእብነ ከሲር ‘ቢዳያህ ወንኒሀያህ’ ከሚለው መፅሀፋቸው ውስጥ ከ40 በላይ የሉቅማን ምክሮች ተጠቅሰዋል ፡፡ ======= ሉቅማን ፡ ቁርዓን ውስጥ የተጠቀሰ በስሙም ምዕራፍ ያለው ፡ ነብዩ አለይሂ ሰላም ሰለሱ ”
☞አሰተሳሰቡ ሰፊ፣
☞መልካም አሳቢ፣
☞ዝምታን የሚያበዛ፣
☞አላህን የሚወድ አላህም የወደደው ፣ ☞ጥበብም የቸረው ነው ” ብለውለታል

ሉቅማን አፍሪካ ውስጥ ‘ኑባ’ የምትባል ቦታ የኖረ ሲሆን ‘ጦብሪያ’ የምትባል ቦታ እንደተቀበረ ይነገራል
https://t.me/Alhamdumuredu
https://t.me/Alhamdumuredu
https://t.me/Alhamdumuredu