Get Mystery Box with random crypto!

ኢስላም

የቴሌግራም ቻናል አርማ alhadith_islamic — ኢስላም
የቴሌግራም ቻናል አርማ alhadith_islamic — ኢስላም
የሰርጥ አድራሻ: @alhadith_islamic
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 610

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-04-14 21:32:29
ዚክር ያለው ትሩፋት !
18 sec
43 viewsedited  18:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-14 13:23:59 ዱዓ የማይመልስባት የጁምዓ ሠዓት!

የእውቀት ባለቤቶች የጁምዓ ቀን ዱዓ ተቀባይነት የሚሆንባት ሠዓትን አስመልክቶ ብዙ ንግግሮችን ሲጠቅሱ፤ ከነዚህ አመዛኞቹ ሁለት ንግግሮች ናቸው።

1- ኢማም ሚንበሩ ላይ ወጥቶ ከሚቀመጥበት ጊዜ አንስቶ ሶላት እስኪጠናቀቅ ድረስ።
ኢብኑል ዓረቢይ፣ በይሐቂይ፣ ቁርጡቢይ፣ ነወዊይ ፣ኢብኑ ረጀብ፣ ኢብን ዓቢዲን ይህን ንግግር አመዝነዋል።

2- ከአስር ሶላት በኋላ።
ብዙ ሠለፎችን ጨምሮ ኢማም አህመድ ፣ኢስሃቅ ኢብን ራሃወይህ፣ ኢብኑ አብድል በር፣ ኢብኑል ቀዩም፣ አልሃጃዊ ያመዘኑት ንግግር ነው።

ኢብኑል ቀዩም እንዲህ ይላል፦
ሰዒድ ኢብኑ ጁበይር (ጁምዓ ቀን) የአሱር ሶላትን ከሰገደ በኋላ ፀሃይ እስክትጠልቅ ድረስ ማንንም አያናግርም ነበር። [ዛዱል መዓድ 1/349]

ኢቢኑ ባዝ እንዲህ ይላሉ፦
" የጁምዓ ቀን ዱዓ ተቀባይነት ያላትን ተጠባቂ ሠዓት አስመልክቶ፥ ኢማም ሚንበሩ ላይ ለኹጥባ ከሚቀመጥባት ሰአት ጀምሮ ሶላት እስኪሰገድ ያለው ጊዜ እና ከዓሱር ሶላት ጀምሮ ፀሃይ እስክተጠልቅ ድረስ ናቸው።
[ፈታዋ ኑር አለደርብ 13 /240-241]

ዛሬ የረመዷን የመጨረሻው ጁምዓ ነው በቻልንው መጠን ጊዜውን በመጠቀም ጥረት እናድርግ። ዱዓ እናድርግ። አሏህ ይግጠመን።

t.me/alhadith_islamic
50 views10:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 22:05:05 اللهم اغفر للمسلمين والمسلمات والمؤمنين والمؤمنات الأحياء منهم والأموات
[ አሏሁመ ጝፊር ሊል ሙስሊሚነ ወል ሙስሊማት ወል ሙዕሚኒነ ወል ሙዕሚናት አል አህያኢ ሚንሁም ወል አምዋት ]

የሚለውን ዱዓ አብዙ ፤ ምንዳቹህ ተቆጥሮ አያልቅም ከአደም አንስቶ ባሉት በየአንዳንዱ ሙስሊሞች ምንዳን ማግኘት በሉት።
አሏህ ይግጠመን !
@alhadith_islamic
52 views19:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 21:20:40
የቀብር ጥያቄ
55 viewsedited  18:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 22:02:12
የነብዩ ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም የምሽት አተኛኘት
@alhadith_islamic
28 viewsedited  19:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 15:09:09
ኢብሊስ(ሸይጧን) ከመላእክቶች አንዱ ነበረን?

@alhadith_islamic
35 viewsedited  12:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-10 22:26:16
ቁርአን
@alhadith_islamic
53 viewsedited  19:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-10 19:21:10
30 views16:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-10 14:26:16 ለይለቱል ቀድር

- ቁርአን የወረደባት ለሊት ናት
እኛ (ቁርኣኑን) በመወሰኛይቱ ሌሊት አወረድነው፡፡[አል ቀድር 1]

- ከአንድ ሺህ ወራት በላጭ ናት
መወሰኛይቱ ሌሊት ከሺሕ ወር በላጭ ናት፡፡[አል ቀደር 3]

ከአንድ ሺህ ወራት በላጭ ናት በሚለው ፍቺ ላይ የእውቀት ባለቤቶች የተለያየ ንግግር አላቸው።
ኢብኑ ጀሪር አጥጦበሪይ እንዲህ ይላሉ፦
" ለይለቱል ቀድር ባለችበት በእዚህች አንድ ለሊት የሚሰራ ስራ ለይለቱል ቀድር ከሌለባቸው አንድ ሺህ ወራቶች ከሚሠራው ስራ በላጭ ነው"[ተፍሲር አጥጦበሪይ 30/167]
የሚለው ሃሣብ አመዛኝ መሆኑን ይናገራሉ።

- መላእክቶች እና ጅብሪልም ወደ ምድር ይወርዳሉ
በርሷ ውስጥ መላእክትና መንፈሱ(ጅብሪል) በጌታቸው ፈቃድ በነገሩ ሁሉ ይወርዳሉ፡፡[አል ቀድር 4]

ነብዩ እንዲህ ብለዋል፦ ለይለቱል ቀድር ሃያ ሠባተኛው ወይም ሃያ ዘጠነኛው ለሊት ነው። በዚህች ለሊት ላይ መላእክቶች ምድር ላይ ከጠጠሮች ብዛት በላይ ሆነው ይወርዳሉ።
[ኢብኑ ኹዘይማህ2194].

- ሠላም የሆነች ለሊት ናት
እርስዋ እስከ ጎህ መውጣት ድረስ ሰላም ብቻ ናት፡፡[አል ቀድር 5]

የእውቀት ባለቤቶች ፍቺዋ ላይ የተለያዩ ሃሣቦች አንስተዋል። ከነዚህም፦
*ከመጥፎ ሁሉ ሰላም የሆነች ለሊት ናት
*በእርሷ ውስጥ ሰላም እንጂ አይኖርም
* የመላእክቶች ሠላምታ ለምዕመናኖች
* ሸይጧን በእርሷ ለሊት መጥፎን ማድርግ አይችልም...

- የተባረከች ለሊት ናት
እኛ (ቁርኣኑን) በተባረከች ሌሊት ውስጥ አወረድነው፡፡ [ሡረቱል ዱኻን 3]
ኢብኑ ዓባስ 'ለይለቱል ቀድር' ናት ብሏል።

- አመታዊ ውሳኔዎች የሚወሰኑባት (ሚብራሩባት)ለሊት ናት
በውስጧ የተወሰነው ነገር ሁሉ ይልለያል፡፡[ሡረቱል ዱኻን 4]

- ነብዩ እንዲህ ብለዋል "ለይለተል ቀድርን አምኖ እና ከጌታው ምንዳን ፈልጎ እርሷን (በአምልኮ በስግደት) የቆማት ያለፈው ወንጀሉ ይማርለታል." [ቡኻሪይ እና ሙስሊም]

- ስያሜዋን አስመልክቶ 'ቀድር' በምትለዋ ቃል አማካኝነት የእውቀት ባለቤቶች በፍቺዋ ላይ ልዩነት አላቸው። ቀድር ማለት (ተዕዚም)ማላቅ ማለት ነው።ቁርአን ስለወረደባት፣ መላእክቶችም ስለሚጣዷት፣... ለይለቱል ቀድር ማለት የላቀች ለሊት ማለት ነው።

-ለይለተል ቀድርን መጠባበቅ እና አስርቱ ቀናት ላይ በአምልኮ ጥረት ማድረግ

-ነብዩ እንዲህﷺ ብለዋል፦
" ለይለተል ቀድርን ከረመዳን የመጨረሻ አስርቱ ጎዶሎ በሆኑ ለሊቶች ላይ ተጠባበቁ።" [ቡኻሪ እና ሙስሊም]

-ዓዒሻ አሏህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና እንዲህ ትላለች፦ ነብዩﷺ የመጨረሻ አስርቱ የረመዳን ቀናት ሲገቡ ማሠሪያቸውን(ቀበቷቸውን) ጠበቅ ያደርጉ ነበር፣ ለሊቱንም በአምልኮ ያሣልፉ ነበር፣ (ለሶላት)ቤተሰቦቻቸውንም ይቀሰቅሱ ነበር።[ቡኻሪይ እና ሙስሊም]
ቀበቷቸውን ጠበቅ ያደርጉ ነበር ማለት፦ ሚስቶቻቸውን ርቀው አምልኮ ላይ ጥረት ያደርጉ ነበር። ለማለት ነው።

ነብዩﷺ እንዲህ ብለዋል፦ " ይህ ወር በእርግጥም ተጥዷችኋል(መጥቷችኋል)፤ በእርሱ ውስጥ ከሺህ ወራቶች የሚበልጥ ለሊት አለ፤ እርሷን የተነፈገ በእርግጥም መልካም ነገር የተባለን በጠቅላላ ተነፍጓል፤ የእርሷን መልካም ገጠመኝ ያላገኘ እድለቢስ ቢሆን እንጂ አይነፈግም።[ኢብኑ ማጀህ ዘግቦታል /ሀዲሱን የሀሠን ደረጃ ሰጥተውታል]

- በዚህች ለሊት የሚወደዱ ስራዎች

በጥቅሉ መልካም በተባሉ የአምልኮ ዘርፎች ላይ ጥረት ማድረግ ይወደዳል። ነብዩ የረመዷን የመጨረሻ አስርቱ ቀናት ላይ ከሚከውኗቸው ተግባራት መካከል፦

- ኢዕቲካፍ
ዓዒሻ አሏህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና፦
"ነብዩﷺ የረመዷን መጨረሻ አስርቱ ቀናትን ዒዕቲካፍ ያደርጉ ነበር አሏህ ከዚህ አለም በሞት እስኪያሰናብታቸው ድረስ።" ብላለች [ቡኻሪ እና ሙስሊም]

- ለሊቷን በሶላት መቆም
ነብዩﷺ እንዲህ ብለዋል "ለይለተል ቀድርን አምኖ እና ከጌታው ምንዳን ፈልጎ እርሷን (በአምልኮ በስግደት) የቆመ ያለፈው ወንጀሉ ይማርለታል." [ቡኻሪይ እና ሙስሊም]

'አምኖ' ማለት ምንዳውን ከአሏህ እንደሚያገኝ አረጋግጦ እውነት ብሎ ማለት ነው።
'ምንዳን ፈልጎ' ማለት እዩልኝን ወይም ሌላን ሳይሆን የጌታውን ምንዳ ብቻ ከጅሎ ማለት ነው።

- ዱዓ
ዓዒሻ አሏህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና ለነብዩ ﷺእንዲህ አለቻቸው፦ ለይለቱል ቀድርን ብገጥም(ባገኝ) ምን ስል ዱዓ ላድርግ ?
ነብዩﷺ " አሏሁመ ኢነከ ዓፍውን ቱሂብል ዓፍወ ፈዕፉ ዓኒ" (አሏህ ሆይ! አንተ ይቅር ባይ ነህ ይቅር ማለትንም ትወዳለህና ይቅር በለኝ) በይ አሏት።[ቲርሚዚይ]

- ቤተሰቦችን ለሶላት መቀስቀስ
ነብዩﷺ "... (ለሶላት)ቤተሰቦቻቸውንም ይቀሰቅሱ ነበር።" [ቡኻሪይ እና ሙስሊም]

-ጊዜዋ
የተገደበ ጊዜዋን አስመልክቶ በእውቀት ባለቤቶች መሃከል ሰፊ ልዩነት (ወደ አርባ የሚጠጉ ንግግሮች) ሲኖሩ ከነዚህ አመዛኙና የተሻለው ብለው ያስቀመጡት "ከረመዷን የመጨረሻ አስርቱ ጎዶሎ ለሊቶች ላይ ናት እርሷም ትቀያየራለች " የሚለው ነው።

ትቀያየራለች የሚለው በተለያዩ ሃዲሶች ላይ የተለያዩ ቀናቶች በመጠቀሳቸው ነው።
ሃያ አንድ፣ ሃያ ሶስት፣ ሃያ ሰባት፣ የመጨረሻዋ ለሊት ላይ ተጠባበቋት የሚሉ ዘገባዎች አሉ።

-ለሊቷ የመደበቋ ወይም ያለ መታወቅ ምክንያት ምንድነው?

ዑባደት ኢብኑ ሷቢት እንዲህ ይላል፦
ነብዩﷺ ለይለተል ቀድር ሊያሣውቁን ወጡ(ጉዞን ጀመሩ)፤ (በመንገዳቸው ላይ) ሁለት ሙስሊሞች ተጨቃጨቁ (ሲጨቃጨቁ ተመለከቱ)፤ ከዚያም ነብዩﷺ እንዲህ አሉ፦
"ወደ እናንተ ለይለተል ቀድር መች እንደሆነ ልነግራቹህ በወጣሁበት እገሌ እና እገሌ ሲጨቃጨቁ ረሣሁት(ተወገደብኝ)፤ ለእናንተ መልካም ሊሆን ይችላል(ይሆናል)፤ ስለዚህም በሃያ አምስት፣ ሰባት እና ዘጠናኛው ለሊቶች ተጠባበቋት።" [ቡኻሪይ]

በሌላ ዘገባም ነብዩﷺ እንዲህ ብለዋል፦
" ለይለተል ቀድርን(በህልሜ) ተነገረኝ(እንዳውቅ ተደረግኩኝ) ከዚያም ከፊል ቤተሰቦቼ ቀሰቀሱኝና ረሣሁት።" [ሙስሊም]

ሃፊዝ ኢብኑ ሃጀር እንዲህ ይላሉ፦
" ይህ ሌላኛው ምክንያት ሲሆን፤ ምክንያቶቹ የተደጋገሙ ሊሆኑ ይችላሉ።አንደኛው ሃዲስ ላይ የተጠቀሰው ለሊቷን እንዲያውቁ የተደረጉት በህልም ሲሆን የመርሳታቸው ምክንያት ደግሞ የቤተሰቦቻቸው መቀስቀስ ነው። ወይም በሌላ ሀዲስ ላይ እንደተጠቀሰው የመርሳታቸው ምክንያት ጭቅጭቁ ህልማቸውን አቋርጦ ቀስቅሷቸው ነው። ወይም ሁለቱን ታሪኮች ወደ ማስማማት ሲኬድ በሁለት ምክንያቶች ሁለት መርሣቶች ተገኝተዋል ይባላል። ወይም ቤተሰቦቼ ቀሰቀሱኝና የሁለት ሰዎችን ጭቅጭቅ ሰምቼ እነርሱን ለመዳኘት በገባሁበት በእነርሡ ጉዳይ በመወጠሬ ረሣሁት የሚለውንም ፍቺ ሊሰጥ ይችላል። [ፈትሁል ባሪ 4/268]

- ለይለቱል ቀድር የመደበቋ ጥበብ

ሃፊዝ ኢብኑ ሃጀር እንዲህ ይላሉ፦
" የእውቀት ባለቤቶች እንዲህ ብለዋል፦ ለይለተል ቀድር ያለመታወቋ ጥበብ እርሷን ለማግኘት ጥረት ማድረግ እንዲኖር ተፈልጎ ነው። ለሊቷ የታወቀች ብትሆን ሰዎች እርሷን ለሊት ብቻ ይጣዱ ነበር።
[ፈትሁል ባሪ 4/315]

- ምልክቶቿ
ለሊቷ ለይለተል ቀድር መሆኗን የሚያመላክቱ ሀዲሶች ተዘግበዋል። ከነዚህም ሶሂህ ከሆኑት

- በለሊቷ ሞቃታማ እና ቀዝቃዛማ ያልሆነ የአየር ሁኔታ መታየት

ነብዩﷺ እንዲህ ብለዋል፦ "ለይለተል ቀድር መች እንደሆነ ተነግሮኝ(ተገልጦልኝ) ነበር ረሣሁት። የመጨረሻዎቹ አስርቱ ለሊት ላይ ናት። እርሷም የንጋት ፍካት የሚታይባት ሞቃት እና ብርዳማ ያልሆነች ለሊት ናት።"[ኢብን ኹዘይማህ]

t.me/alhadith_islamic
38 views11:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-10 14:18:32 ኢዕቲካፍ

|> ኢዕቲካፍ ማለት በቋንቋ ደረጃ፦ በአንድ መልካም ወይም መጥፎ ነገር ላይ መዘውተር እና ነፍስን በእርሱ ላይ መገደብ ማለት ነው።

|> እንደ ሸሪዓዊ ፍቺው ደግሞ፦ አንድ ሰው በተነጠለ (መስፈርቱን በጠበቀ መልኩ) ወደ አሏህ መቃረብን ፈልጎ መስጂድ ላይ የሚያደርገው ማዘውተር "ዒዕቲካፍ" ይባላል።

ዒዕቲካፍ ብይኑ ሱንናህ ነው። ይህ ድርጊት ከረመዷን የመጨረሻ አስርቱ ቀናቶች ላይ ለይለተል ቀድር በመኖሯ ምክንያት ይበልጥ የጠነከረ ሱንናህ ይሆናል።

|> የዒዕቲካፍ የጊዜ ገደብ

አንድ ሰው ዒዕቲካፍን አደርጋለሁ ብሎ የተሣለ ከሆነ በተሣለበት ጊዜ መፈፀም ይኖርበታል። ከዛ ውጪ ባለው በተፈቀደው 'ልቅ' በሆነው የዒዕቲካፍ ድርጊት እስከዚህ ጊዜ የሚባል የጊዜ ገደብ የለውም። ሰለሆነም መስጂድ ላይ የተወሰነ ጊዜያትንም ቢያዘወትር ኢዕቲካፍ ይሰኛል።

|> የዒዕቲካፍ ማዕዘናት

- ኒያህ
- መስጂድ ውስጥ መዘውተር
- ዒዕቲካፍ አድራጊው መገኘት
- ዒዕቲካፍ የሚደረግበት ቦታ(መስጂድ) መሆን አለባቸው።

|> ዒዕቲካፍ ለማድረግ ፆመኛ መሆን መስፈርት ነውን?

በዚህ ነጥብ ላይ የእውቀት ባለቤቶች ልዩነት ሲኖራቸው ከፊሎች ፆም ለዒዕቲካፍ መስፈርት አይሆንም ሲሉ ሌለኞቹ ደግሞ ፆምን መስፈርት አድርገዋል።
- ኡመር ኢብኑል ኸጧብ ረዲየሏሁ አንሁ
" በጃሂሊያ ዘመን በለሊቱ ክፍል መስጂደል ሃረም ላይ ዒዕቲካፍን ሊያደርግ ተስሎ ነብዩ ﷺ "ስለትህን ሙላ" ብለውታል። ቡኻሪይ እና ሙስሊም

-ይህንን ሃዲስ በመያዝ ፆም በለሊቱ ክፍለ ጊዜ ስለማይኖር ዒዕቲካፍ ለሚባለው ድርጊት ፆም እንደመስፈርት አይወሰድም ብለዋል።
-ነብዩﷺ አስርቱን የመጀመሪያ የሸዋል ቀናቶች ዒዕቲካፍ አድርገው ነበር።[ቡኻሪ እና ሙስሊም]
ከነዚህ አስርት ቀናቶች መካከል አንዱ ዒድ ሲሆን በዒድ ፆም መፆም የተከለከለ ነው። ስለሆነም ይህ ሃዲስም የሚያመላክተው ለዒዕቲካፍ ፆም መስፈርት አለመሆኑ ነው። ብለዋል።

-ሌለኞቹ፦ ዓዒሻ አሏህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና እንዲህ ብላለች "ዒዕቲካፍ ለሚያደርግ አካል ሱንናው ፆመኛ መሆኑ ነው።" [አቡዳውድ]
-አንድ ሶሃብይ "ሱንናው እንዲህ ነው..." ካለ ይህ ንግግሩ ወደ ነብዩﷺ የተጠጋ ንግግር(የነብዩ ንግግር) ተደርጎ ይወሰዳል። ብለዋል።

-ኢብኑል ቀይም እንዲህ ይላል፦ አሏህ ዒዕቲካፍን ከፆም ጋር አቆራኝቶ እንጂ አልጠቀሰም፤ ነብዩም ከፆም ጋር እንጂ አልፈፀሙትም።
[ዛዱል መዓድ 2/87]

ቃዲ ዒያድ እንዲህ ይላል፦ "ይህ ንግግር የአብዝሃኛዎቹ የእውቀት ባለቤት ንግግር ሲሆን፤ አመዛኙና ትክክለኛውም እርሱ ነው።"[ነስቡራያህ 2/489] ሲል ፆም ለዒዕቲካፍ መስፈርት መሆኑን አመዝኗል።
ይህን አቋም ኢብን ተይሚያህ፣ ጀሷስ[አህካሙል ቁርዓን1/245] እና ኢብን ዓብድል ሐዲይ ያመዘኑት አቋም ነው።

-ነብዩ የሸዋል የመጀመሪያ አስርት ቀናቶችን ዒዕቲካፍ አድርገዋል ለሚለው የሠጡት ምላሽ

ኢብን ዓብድል ሐዲይ እንዲህ ብለዋል፦
" ነብዩﷺ ያደረጉት ዒዕቲካፍ የመጀመሪያው የፊጥር ቀን (የዒድ ቀን) መሆኑን በግልፅ አልተጠቀሰም(ግልፅ አይደለም)። በሁለተኛው ቀን ሊሆንም ይችላል ዒዕቲካፍ ያደረጉት። እንደውም ይህ ነው ግልፅ ሆኖ ሚታየው።"
[ነስቡ ራያህ2/489]

|> የዒዕቲካፍ ቦታ

አሏህ በቁርአኑ እንዲህ ይላል፦
[እናንተም በመስጊዶች ተቀማጮች ስትኾኑ አትገናኙዋቸው፡፡]

ዒዕቲካፍ የሚደረግበት መስጂድ የጀመዓ ሶላት የሚደረግበት መስጂድ መሆኑ የተሻለ እና በላጭ ነው። ከፊሎች እንደ መስፈርት ጠቅሰውታል።

ኢብን ቁዳማህ እንዲህ ይላል፦
" ይህ እንደመስፈርት የተቀመጠው የጀመዓ ሶላት ዋጂብ(ግዴታ) በመሆኗ ነው። አንድ ሰው በጀመዓ ማይሰገድበት መስጂድ ዒዕቲካፍ በማድረጉ ሁለት ነገሮችን ያጣል፤ አንደኛው ግድ የሆነችውን የጀመዓ ሶላት መተው ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ መቆጠብ እየቻለ ካለበት መስጂድ ጀመዓ ሶላት ወደ ሚሰገድበት መስጂድ በመውጣት ዒዕቲካፍ ካደረገበት ቦታ መውጣትን ሊደጋግም ነው። ይህ ደግሞ ኢዕቲካፍን ያፈርሳል።"
[አል መጝኒ 3/187]

|> ኢዕቲካፍ አድራጊ መቼ ወደ ኢዕቲካፍ ማድረጊያው(መስጂድ) ይገባል? መቼስ ኢዕቲካፉን ጨርሶ ይወጣል?

- አብዝሃኛዎቹ የእውቀት ባለቤቶች ኢዕቲካፍ አድራጊ ወደ ኢዕቲካፍ ማድረጊያው የሚገባው ሃያኛው ቀን ፀሃይ ስትጠልቅ (የሃያ አንደኛው ለሊት መጀመሪያ ላይ) ነው። ከኢዕቲካፉ ቦታ የሚወጣው ደግሞ የመጨረሻው የረመዷን ቀን ፀሃይ ከጠለቀች በኋላ ነው። ብለዋል።

ሌለኞቹ ደግሞ፦
- ሃያ አንደኛው ንጋት ላይ ከፈጅር በኋላ ወደ ኢዕቲካፍ ማድረጊያው ገብቶ የዒድ ንጋት ላይ ከኢዕቲካፍ ማድረጊያው ይወጣል። ብለዋል።

|> ኢዕቲካፍ አድራጊን የሚነጥሉ ስራዎች

የኢዕቲካፍ ዋና አላማው ነፍስን ወደ አሏህ በሚያቃርቡ ስራዎች ማሰር እና ማጠር ሲሆን፤ ኢዕቲካፍ በሚያደርግበት መስጂድ ውስጥ ባሉ መልካም ስራዎች[ሶላት፣ ዚክር፣ ቂርአት..] ሊሣተፍ ይገባል። ሌሎች የእውቀት ባለቤች ከመስጂድ ውጪ ያሉ አምልኮዎችን መስራት [የታመመን መጠየቅ፣ የሟችን ሬሳ መሸኘት ..] እንደሚችል ጠቁመዋል።

|> ኢዕቲካፍ አድራጊ ሊፈፅማቸው የተቻሉ ድርጊቶች

- ኢዕቲካፍ አድራጊ ለመፀዳዳት(ሽንት ቤት) መሄድ፣ የሚመገበውን ምግብ ሚያመጣለት ከሌለም ለማምጣት መውጣት ይችላል።
- ውዱእ ለማድረግ እና ገላን ለመታጠብ መውጣት
- ፀጉሩን ማበጠርም ሆነ መላጨት፣ ጥፍሩን መቁረጥ
- የተቻለ ከሆነ ለብቻው የሆነን ቦታ መስጂድ ውስጥ ማዘጋጀት
- ያለ እርሱ ሊከወኑ ማይችሉ ግድ የሆኑ የግዢ ወይም የሽያጭ ግብይቶችን መፈፀም
- ኢማም አን ነወዊይ እንዲህ ይላሉ፦ " ኢዕቲካፍ አድራጊ ማግባትም ሆነ ሌላን መዳር ይችላል።
- ሽቶ መቀባት
- በአስገዳጅ ሁኔታ ለምስክርነት ከተፈለገ ከኢእቲካፉ ቦታ መውጣት
- ልጅ የምታጠባ እናት ኢዕቲካፍ ማድረግ ትችላለች። ሃይድ ላይ ያለችም እንዲሁ(በነጥቡ ላይ የሃሣብ ልዩነት ያለው ቢሆንም) ኢዕቲካፍ ማድረግ ትችላለች።

|> ኢዕቲካፍን የሚያፈርሱ ተግባሮች

- 'አውቆ' ግንኙነት ማድረግ
- ረስቶ ከሆነ ኢዕቲካፉ አይበላሽም። ምንም የለበትም።
- የዘር ፈሳሽን ማውጣት
- ኢዕቲካፉን ለማቋረጥ ቁርጥ የሆነ ኒያን ማስገኘት...

t.me/alhadith_islamic
32 views11:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ