Get Mystery Box with random crypto!

"ኤልሮኢ ዘተዋህዶ"

የቴሌግራም ቻናል አርማ aleroe — "ኤልሮኢ ዘተዋህዶ"
የቴሌግራም ቻናል አርማ aleroe — "ኤልሮኢ ዘተዋህዶ"
የሰርጥ አድራሻ: @aleroe
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.81K
የሰርጥ መግለጫ

ኤልሮኢ
"በእውኑ የሚያየኝን ጌታ አየሁት"
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ
አምላክ አሜን።
ይህ መንፈሳዊ ቻናል
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ:- ዝማሬ
ምክሮች
ስነፅሁፎች
አጫጭር ትርክቶች እንዲሁም
ምስባክና
ወንጌል ይለቀቁበታል።

ለበለጠ መረጃ @AleroeBot
ግሩፑን ለማግኘት @alero

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-05-09 07:56:47 ኤልሮኢ:( ትምህርት )

ልደታ ለማርያም


እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ለሰው ወገን ሁሉ የድኅነት ምክንያት ናት፡፡ ፍጥረታት ሁሉ እርሷን ያመሰግኗታል፡፡ የፍጥረት ሁሉ መዳን በርሷ እጅ ነበርና፡፡ አዳም አባታችን በተሰደደ ጊዜ መጽናኛው እርሷ ነበረች፡፡ አዳም አባታችን ሲሰደድ አምላካችን በገባለት ቃል ኪዳን መሠረት ዘመኑ ሲቃረብ ከእርሷ ሊወለድ እሷ ተወለደች፡፡
እንደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ግንቦት አንድ ቀን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተወለደች፡፡ የእመቤታችን መወለድ አስቀድሞ በነቢያት የተነገረ፤ በብዙ ሕብረ አምሳል የተገለጠ ነው፡፡ በነገረ ማርያም እንደምንረዳው እመቤታችን ከመወለዷ አስቀድሞ ቅድመ አያቶቿ፣ አያቶቿና ወላጆቿ ምልክት አይተዋል፡፡ የእመቤታችን የትዉልድ ስፍራ ሊባኖስ የተባለዉ ተራራማ ሀገር ነዉ፡፡ ሊባኖስ ከገሊላ በስተሰሜንና ከፍንቄ በስተ ምስራቅ ይገኛል፡፡ ሙሽራዬ ሆይ ከሊባኖስ ከእኔ ጋርነይ የሚለዉ ቃለ ትንቢት ምስጢርም የእመቤታችን መካነ ልደት የሊባኖስ ተራራ መሆኑን ያጠይቃል፡፡መኃ 4-7

ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ የጌታ መንገድ ጠራጊ፣ የአዋጅ ነጋሪና ታማኝ ምስክር በመሆኑ በተወለደ ጊዜ በመልአኩ ቅዱስ ገብርኤል በመወለዱ ብዙዎች ደስ ይላቸዋል ብሏል፡፡ ሉቃ 1-14 የቅዱስ ዮሐንስ መወለድ ለብዙዎች ደስታና የምስራች አብሳሪ ከሆነ ድኅነተ ሥጋ ወነፍስ የሚሰጠውን ኢየሱስ ክርስቶስን የወለደች የድንግል ማርያም ልደት ምንኛ ያስደስት፡፡
የቀርጤሱ ቅዱስ እንድርያስ ስለ እመቤታችን ልደት እንዲህ ብሏል ይህ በዓል በሐዲስና በብሉይ ኪዳን መካከል መገኛ ሆነ፡፡ ምሳሌዎቹ በእዉነታ፣ አሮጌዉ በአዲስ ቃል ኪዳን ተተኩ፡፡ ፍጥረት ሁሉ በደስታ ይዘምራል የዚህን ቀንም ደስታ ይካፈላል፡፡ ይህ መቅደሱን የሰራበት ዕለት ነዉ፡፡ ይህ ዕለት ትልቅ ሕንፃ የታነጸበትና ፍጡር የፈጣሪ ማደሪያ ለመሆን የተዘጋጀበት ዕለት ነዉ ብሏል፡፡
እመቤታችን ለፀሐዩ መምጣት የተዘረጋች ሰማይ፡ በቅድመ አያቶቿ በነቴክታና ጰጥሪቃ ሕልም እንደታየችዉ በሌሊት የምታበራ ጨረቃ፤ የብሉይ ኪዳን ማብቂያ፤ የሐዲስ ኪዳን መጀመሪያ ናትና ልደቷ ለሰዉ ልጅ ሁሉ ደስታ ነዉ፡፡
ነቢያት በብዙ ሕብረ አምሳል የተናገሩላት መሰረቶቿ የተቀደሱ ተራራዎች ናቸዉ፤ ከእሴይ ሥር በትር ትወጣለች አበባዋም ከግንዱ ይወጣል፤ ሙሽራዬ ሆይ ከሊባኖስ ነይ ብለዉ ተናገሩላት፤ ልደቷ የትንቢታቸዉ ፍፃሜ ነዉና ደስታቸዉ ታላቅ ነዉ፡፡ መዝ 86፡1 ኢሳ. 11፤1

በእግዚአብሔር የሚያምኑ ጰጥሪቃና ቴክታ የሚባሉ በሀብት የከበሩና ደጋግ ባልና ሚስቶች በኢየሩሳሌም ይኖሩ ነበር፡፡ እነዚህ ደጋግ ሰዎች በሀብት ይክበሩ እንጂ ሀብታቸውን የሚወርስ ልጅ አልነበራቸውም፤ መካን ነበሩ:፡

ከዕለታት አንድ ቀን ጰጥሪቃ ወደ ቤተ መዛግብቱ ገብቶ ሀብቱን ሰፍሮና ቆጥሮ ቴክታን እህቴ ሆይ ይህ የሰበሰብነው ገንዘባችንን ምን እናደርገዋለን? የሃብታችን ብዛት ስፍር ቁጥር የለውም፡፡ የሚወርሰን ልጅ የለን፡፡ አንቺም መካን ነሽ እኔም ካንቺ በቀር ሌላ ሴት አላውቅም አላት፡፡ እርሷም ወንድሜ ሆይ አምላከ እስራኤል ለኔ ልጅ ቢነሳኝ አንተ ያለ ልጅ ትቀራለህን? ከሌላ ሴት ውለድ አለችው፡፡ ጰጥሪቃም እንዲህ ያለ ነገር እንኳንስ ላደርገው በልቦናዬ እንዳላስበው አምላከ እስራኤል ያውቅብኛል አላት፡፡ እሷም እንግዲህ አምላከ እስራኤል የሚያደርገውን ያውቃል፡፡ ትላንትና ማታ በሕልሜ ነጭ አንስት ጥጃ ከማኅጸኔ ስትወጣ፣ ያችም ነጭ ጥጃ ሌላ ነጭ ጥጃ ስትወልድ እንዲሁ እስከ ሰባት ትውልድ ሲዋለድ ሰባተኛይቱ ጨረቃን ስትወልድ፤ ጨረቃዋም ፀሐይን ስትወልድ አየሁ አለችው::

እርሱም በጠዋት ከሕልም ፈቺ ዘንድ ሄዶ ቴክታ የነገረችውን ሕልም ለፈቺው ነገረው፡፡ ያም ሕልም ፈቺ እግዚአብሔር በምኅረቱ አይቷችኋል ሰባት አንስት ጥጆች መውለዳቹ ሰባት ሴቶች ልጆች እና የልጅ ልጆች ትወልዳላችሁ፡፡ ሰባተኛይቱ ጨረቃ መውለዷ ከሰው የበለጠች ከመላእክትም የከበረች ደግ ፍጥረት ትወልዳላችሁ፡፡ የፀሐይ ነገር ግን አልታወቀኝም አለው:፡ ጴጥሪቃም ሕልም ፈቺው የነገረውን ሁሉ ለቴክታ ነገራት፡፡ እርሷም አምላከ እስራኤል የሚያደርገውን ማን ያውቃል? ብላ ዝም አለች፡፡ በዚያም ወራት ቴክታ ጸነሰች፡፡ በዘጠኝ ወሯ ሴት ልጅ ወለደች፡፡ ስሟንም ሄዔሜን ብለው አወጡላት፡፡ ሄዔሜን አድጋ ለአካለ መጠን ስትደርስ አጋብተዋት ሴት ልጅ ወለደች በስምንተኛ ቀኗ ደርዲ ብለው ስም አወጡላት፡፡ ደርዲ ማለት ከአባቶች ወገን የተወለደች ማለት ነው:: ደርዲም አድጋ እንዲሁ ሴት ወለደችና ቶና አለቻት፡፡ ቶና ማለት ራዕይ አይተን ነገር አግኝተን የወለድናት ማለት ነው):: ቶናም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ሲካር አለቻት፡፡ ሲካር ማለት ከዘመዶቻችን የተወለደች ማለት ነው:: ሲካርም እንዲሁ አድጋ ለአካለ መጠን ስትደርስ ባል አጋቧት ሴት ልጅም ወልደች፡፡ በስምንተኛ ቀን ስሟን ሴትና ብለው አወጡላት ፡፡ ሴትና ማለት ሙያዋ ያማረ፣ ምግባሯ የሰመረ በጎ ቆንጆ ማለት ነው፡፡ ሴትናም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ሄርሜላ አለቻት፡፡ ሄርሜላ ማለት ከክቡሮች ከባለጸጋ ወገን የተወለደች ማለት ነው፡፡ ሄርሜላም እንዲሁ አድጋ ለአካለ መጠን ስትደርስ አጋብተዋት ሴት ልጅ ወለደች በስምንተኛ ቀኗም ሐና ብለው ስም አወጡላት፡፡ሐና ማለት ምን ማለት በሐይማኖት በምግባር የጸናች፣ በንጽሕና በቅድስና የተሸለመች ክብርት ወልዕልዕት ደግ ፍጥረት ማለት ነው፡፡

ከጴጥርቃና ከቴክታ የተወለዱ ስድሳ ሰባት ወንዶች ልጆች አሉ የእመቤታችን የድንግል ማርያምን ትውልድ ለመቁጠር ትንቢት አልተነገረላቸውም ሱባኤ አልተቆጠረላቸውምና አልተፃፈም፡፡ ሐና አደገች ለአካለ መጠን ስትደርስ ከቤተ መንግሥት ወገን፣ ከዳዊት ወገን ከሆነው ከቅዱስ ኢያቄም ጋር አጋቧት::

ቅዱሳን ኢያቄም እና ሐና ሲኖሩ ልጅ አጡ፡፡ ከሰው የሚደርስባቸውን ሽሙጥና ኀዘናቸውን ያርቅላቸው ዘንድ በቀንና በሌሊት ወደ እግዚአብሔር ፈጽሞ ይማልዱ ነበር፡፡

አንድ ቀን ወደ ቤተ እግዚአብሔር ሒደው ሲፀልዩ ሲያዝኑ ዋሉ፡፡ ኀዘናቸው እንዴትስ ነው? ቢሉ፡፡ ኢያቄም አቤቱ የአባቶቼ የእስራኤል አምላክ እኔን ባርያህን ስማኝ፡፡ ጸሎቴን ተቀበል ለዐይኔ ማረፊያ ለልቤ ተስፋ የሚሆን የተባረከ ልጅ ስጠኝ ብሎ ሲለምን ዋለ:: ሐናም በበኩሏ አቤቱ ጌታዬ የአባቶቼ የእስራኤል አምላክ ባርያህ እለምንሃለው፡፡ ለዐይኔ ማረፊያ ለልቤ ተስፋ የምትሆነኝ የተባረከች ልጅ የማኅፀኔን ፍሬ ስጠኝ ብላ ስትለምን ዋለች:: እንዲህ ብለው ሲያዝኑ ሲጸልዩ ዋሉ፡፡ በዚህ ወቅት ርግብ ከልጆቿ ጋር ስትጫወት አይታ አቤቱ ጌታዬ ለዚች ግእዛን ለሌላት እንስሳ ልጅ የሰጠህ አምላክ ምነው ለኔ ልጅ ነሳኸኝ ብላ አምርራ አለቀሰች፡፡ ወዲያው ከሊቀ ካህናቱ ከዘካርያስ ዘንድ ሄደው አቤቱ ጌታችን ሆይ ወንድ ልጅ ብንወልድ ተምሮ ቤተ እግዚአብሔርን አገልግሎ እንዲኖር እንሰጣለን፡፡ ሴት ልጅም ብንወልድ ውኃ ቀድታ መሶበ ወርቅ ሰፍታ መጋረጃ ፈትላ ካህናትን አገልግላ እንድትኖር እንሰጣለን ብለው ተሳሉ::

ሊቀ ካህኑ ዘካርያስም እግዚአብሔር ጸሎታችሁን ይስማችሁ ስዕለታችሁን ይቀበልላችሁ ጻህቀ ልቦናችሁን ይፈጽምላችሁ ብሎ ጸሎታቸውን አሳረገላቸው፡፡ ሰውን የሚወድ እግዚአብሔርም ከዘራቸው ለዓለሙ ሁሉ መድኃኒት ይሆን ዘንድ መልካም የሆነ ሀሳባቸውን ተመለከተ፡፡
542 viewsTesfabel, 04:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-01 18:06:56 ኤልሮኢ:( መንፈሳዊ ግጥም )

፨ገድፍሃል፨

አንደበትህ ክዶህ ሀሰት ከለመደ
መልካሙን ናቅ አርጎ ሴራ ከወደደ
እንደ አምሳል መሰረት ቀረ ሰው መሆንህ
አምላክም አይኖርም ሳይጣን ነው ከጎንህ
በህይዎት እየኖርክ ከሆንክ አሜኬላ
እኔ ሰው ነኝ እያልክ ልብህ ሰው ከጠላ
በእምነቱ ፀንተህ ወስጋ ከደሙ
አልገለጽ ካለህ የህይወት ትረጉሙ
እውነቱን ተቀበል
ጾምህን ገድፍሃል
ለምን! ማለት ጥሩ ለምን ይመስልሃል?
ውሰጥ ተመርዞ
ልብህ ቂም አርግዞ
ላይሰምር ሱባኤ
ልብ ሳይኖር ጉባኤ
ገደብ የለሽ ምኞት
ከአንገት በላይ ፀሎት
በላይኛው አለም ወንዝ አያሻግርም
እዚ እንደለመደከው ማጭበርበር አይኖርም።



@aleroe
@Aleroebot
667 viewsTesfabel, 15:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-24 12:48:08 ኤልሮኢ:( ትምህርት )

ከትንሣኤ እሁድ በኋላ ያሉ ዕለታት ስያሜ

ሰኞ

ማዕዶት ይባላል፡- ማዕዶት ማለት መሻገር፣ ማለፍ ማለት ነው፡፡ በዚህ ዕለት በፋሲካችን በክርስቶስ ትንሣኤ ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን፣ ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከሲኦል ወደ ገነት፣ ከሃሳር ወደ ክብር መሻገራችንን እናስባለን፡፡

ማክሰኞ

ቶማስ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቶማስ ጌታን አይቶ ማመኑ፤ ጌታዬና አምላኬ ብሎ መመስከሩ ይዘከራል፡፡ ዮሐ. 20፡27-29

ረቡዕ

አልአዛር ይባላል፡- በዚህ ዕለት ትንሣኤና ሕይወት የሆነው ጌታ ኢየሱስ አልአዛርን ከሞት እንዳስነሳው እናስባለን፡፡ ክርስቶስ የሞትን ስልጣን የሻረ የሕይወት ራስ፤ የመቃብርን ሥርዓት ያጠፋ ትንሣኤ፡ በድልም ያረገ ንጉሥ መሆኑን እንመሰክራለን፡፡

ሐሙስ

አዳም ሐሙስ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ለአዳም የተሰጠው ተስፋ እና የተገባለት ኪዳን እንደተፈጸመ አዳምና ልጆቹ ነጻ እንደወጣን እናስባለን፡፡

ዓርብ

ቅድስት ቤተክርስቲያን ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ስለመመስረቷ ይሰበካል፡፡ ክርስቶስ ስለ እርሷ ራሱን አሳልፎ ሰጥቶ ቤዛ ሆኖ በደሙ አንጽቶ በትንሣኤው ድል ሰጥቶ እንዳከበራት ይነገራል፡፡ ቤተክርስቲያን ስንል ሕንፃውን ሳይሆን አማኞችን ነው፤ ክርስቶስ ለሕንፃ አልሞተምና፡፡

ቅዳሜ

ቅዱሳት አንስት ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቅዱሳት አንስት የክርስቶስን አካል ሽቶ ለመቀባት ጨለማ አቋርጠው ወደ መቃብር መምጣታቸውና ትንሣኤውንም ቀድመው ማየታቸው ይሰበካል፡፡

እሁድ

ዳግም ትንሣኤ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ክርስቶስ ለሦስተኛ ጊዜ ለደቀመዛሙርቱ ተገልጦ ሰላምን መስበኩ እና ሥልጣንን መስጠቱ ይሰበካል፡፡

@aleroe
@Aleroebot
910 viewsTesfabel, 09:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-22 20:33:13
ኤልሮኢ:( ፊልም )

The PASSION OF CHRIST
በአማርኛ ቋንቋ ስቃይ የሚበዛበት
የኢየሱስ ክርስቶስ ፊልም

@aleroe
@Aleroebot
623 viewsTesfabel, edited  17:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-20 20:28:54 ኤልሮኢ:( ትምህርት )

#ሰሙነ_ሕማማት
============

ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ሰሙነ ሕማማት የጾመ ሁዳዴ የመጨረሻው ሳምንት፤ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሕማም የሚታሰብበት፤ ካህናትና ምእመናን በአጸደ ቤተክርስቲያን ተሰብስበው የሕማሙን ነገር የሚያወሳውን ዜማ የሚያዜሙበት፤ ግብረ ሕማም በመባል የሚታወቀውን መጽፍ የሚያነቡበትና የሚሰሙበት፤ በነግህ፣ በሠልስት፣ በስድስት፣ በተሰዓት /ዘጠኝ /ሰዓት፣ በሰርክ /በዐስራ አንድ/ ሰዓት እየመላለሱ የሚሰግዱበትና የሚጸለዩበት ልዩ ሳምንት ነው ከሆሳዕና ማግስት እስከ ትንሳኤ።
በዚህ ሳምንት በተለይ ካህናት ጥቁር ልብስ ይለብሳሉ ምክንያቱም ጌታችን የደረሰበትን መከራና ስቃይ እንዲሁም የሰው ልጅ ፭ ሺ ፭ መቶ ዘመን በጨለማ ግዞት ይኖር እንደነበር ለማዘከርም ጭምር ነው።
የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን መከራና ሕማም በጽኑ እንድናስበው ያስተማሩን ሐዋርያት ናቸው። ለእነርሱም የነገራቸው ደግሞ ራሱ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
ሰሙነ ሕማማት የጌታችንን ሕማማት ከማሰብ ጋር በየዕለቱ በርካታ ድርጊቶች መፈጸማቸውን የምናስታውስበት ሳምንት ነው፦

#ሰኞ
መርገመ በለስ የተፈጸመበት ሰኞ ይባላል፦
በዚህ ዕለት ጌታችን ከቢታኒያ ሲወጣ ተራበ ቅጠል ያለባትን በለስ ተመልክቶ ወደ በለሲቱ ቢቀርብ ከቅጠል በቀር ምንም ነገር ባለማግኘቱ “ከአሁን ጀምሮ ለዘላለም ምንም ካንቺ ፍሬ አይበላ” ማር ፲፩፥፲፬ በማለት ስለረገማት መርገመ በለስ የተፈጸመበት ሰኞ ይባላል።

አንጽሖተ ቤተመቅደስ ይባላል፡-
ጌታ ወደ ቤተመቅደስ ሄዶ በቤተመቅደሱ የሚሸጡትን እና የሚለውጡትን “ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች” ማቴ ፳፩፥፲፫ በማለት ከቤተመቅደስ ገርፎ አስወጥቷቸዋልና።

#ማክሰኞ
የጥያቄ ቀን ይባላል፦
ሰኞ ዕለት በቤተመቅደስ ሲሸጡ እና ሲለውጡ የነበሩትን ሁሉ እየገረፈ በማባረሩ ምክንያት ለሰው ልጅ ሹመትንና ስልጣንን የሰጠ ጌታ “በምን ስልጣን ይህንን ታደርጋለህ?” ማቴ ፳፩፥ ፳፫ ተብሎ በፈሪሳውያን ተጠይቋልና የጥያቄ ቀን ይባላል።

የትምህርት ቀን ይባላል፡-
በዚህ ዕለት በቤተመቅደስ ረጅም ትምህርት ስላስተማረም የትምህርት ቀን ይባላል። ሉቃ ፳፩ ፥፳፰ ፣ ማር ፲፪፥፪።

#ረቡዕ
ምክረ አይሁድ ይባላል፦
ረቡዕ እለት የአይሁድ ሊቃነ ካህናትና ጸሐፍት ጌታን እንዴት መያዝ እንዳለባቸው የመከሩበትና ውሳኔ ያሳለፉበት ቀን በመሆኑ ምክረ አይሁድ ይባላል። ወቅቱ የፋሲካን በዓል የሚያከብሩበት ቀን በመሆኑ እና ብዙ ህዝብም ጌታን ይከተለው ስለነበር ሁከት እንዳይነሳ ስጋት ነበራቸው ። ነገር ግን ከአስራ ሁለቱ ሐዋርያት አንዱ የአስቆሮቱ ይሁዳ አሳልፎ እንደሚሰጣቸው ስለነገራቸው ሉቃ ፳፪፥፩-፮ ጭንቀታቸው ተወግዶ በጌታ መያዝ ተስማምተዋል።

የመልካም መዓዛ ቀንም ይባላል፡-
ጌታችን በዚህ ዕለት በለምጻሙ በሰምዖን ቤት ተቀምጦ ሳለ መላ ሕይወቷን ለዝሙት አስገዝታ ትኖር የነበረችው ማርያም እንተ እፍረት/ባለሽቶዋ ማርያም/ ዋጋው እጅግ ውድ የሆነ የአልባጥሮስ ሽቱ አምጥታ በራሱ ላይ በማርከፍከፍ ስለቀባቸው ማቴ ፳፮፥፮-፯ የመዓዛ ቀን ይባላል።

የእንባ ቀን ይባላል፡-
ባለሽቱዋ ሴት (ማርያም እንተ እፍረት) ኃጢአቷን ይቅር እንዲላት እየለመነች በእግሩ ስር ተደፍታ በእንባዋ እግሩን አርሳለችና ማር ፲፬፥፱ የእንባ ቀን ይባላል።

#ሐሙስ
ጸሎተ ሐሙስ ይባላል፦
ጌታችን ለአይሁድ ተላልፎ ከመሰጠቱ በፊት በጌቴሴማኒ የአትክልት ስፍራ ሲጸልይ በማደሩ ማቴ ፳፮፥፴፮ ጸሎተ ሐሙስ ይባላል።ጌታችን የደቀመዛሙርቱን እግር በፍጹም ትህትና ዝቅ ብሎ ያጠበበት ዕለት በመሆኑም ዮሐ ፲፫፥፫-፲፩ ሕጽበተ ሐሙስ ይባላል።

የምስጢር ቀን ይባላል፡-
ከሰባቱ ምስጢራት አንዱ የቅዱስ ቁርባን ምስጢር ማቴ፳፮፥፳፮-፳፱ በዚህ ዕለት ተፈጽሟልና የምስጢር ቀን ይባላል።

የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ይባላል፡-
መሥዋዕተ ኦሪት /በእንስሳት ደም የሚቀርብ መሥዋዕት/ቀርቶ ለአለም ድኅነት ራሱን ያቀረበበት ቀን በመሆኑ ሉቃ ፳፪፥፳ የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ይባላል።

የነጻነት ሐሙስ ይባላል፡-
ለኃጢአትና ለዲያቢሎስ ባሪያ ሆኖ መኖር ማብቃቱን እንዲሁም የሰው ልጅ ያጣውን ክብር መልሶ ማግኘቱ የተረጋገጠበት ቀን ስለሆነም ዮሐ ፲፭፥ ፲፭ የነጻነት ሐሙስ ይባላል።

#ዓርብ
የስቅለት ዓርብ ይባላል፦
ጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳምና ለልጆቹ ሁሉ ቤዛ ሆኖ በመልዕልተ መስቀል ላይ ተሰቅሎ የዋለበት ዕለት ነውና ማቴ ፳፯፥፴፭ የስቅለት ዓርብ ይባላል።

መልካሙ ዓርብ ይባላል፡-
ከጌታ ስቅለት በፊት በተለይም በሮማውያን ህግ የወንጀለኛ መቅጫ ምልክት የነበረውን መስቀል ጌታችን በደሙ ቀድሶ የምህረት፣ የሕይወት አርማ፣ የዲያቢሎስ ድል መንሻ ስላደረገው፤ በሞቱ መልካሙን ሕይወት ስላገኘን መልካሙ ዓርብ ይባላል።

#ቅዳሜ
ቀዳም ስዑር ትባላለች ፦
ይህች እለት ከድሮ በተለየ መልኩ የጌታችንን መከራ በማሰብ በጾም ታስባ ስለምትውል የተሻረች ቅዳሜ ይባላል።
ለምለም ቅዳሜ ይባላል፡-
ካህናቱ ለምእመናን ለምለም ቀጤማ የሚያድሉበት ዕለት በመሆኑም ለምለም ቅዳሜ ይባላል። ምዕመናንም ይህንን ለምለም ቀጤማ እስከ ትንሣኤ ለሊት በራሳቸው ላይ ያስሩታል።

ቅዱስ ቅዳሜ ይባላል፡-
ቅዱስ የሆነው እግዚአብሔር በጥንተ ተፈጥሮ ፍጥረታትን አከናውኖ ያረፈበት ቀን ሲሆን በዘመነ ሐዲስ ደግሞ የማዳን ስራውን ሁሉ ፈጽሞ በሥጋው በመቃብር ሲያርፍ በነፍሱ ወደ ሲኦል ወርዶ ሲኦልን በርብሮ ባዶዋን ሲያስቀራት በዚያ የነበሩትን ነፍሳት የዘላለም ዕረፍትን ያወረሰበት ዕለት ስለሆነ ቅዱስ ቅዳሜ ይባላል።

@aleroe
@Aleroebot
706 viewsTesfabel, 17:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-28 23:17:58 ኤልሮኢ:
ምክረ አበው

“ #እምነት-አለኝ” ብሎ ምግባር የሌለው ሰውና፥ “ምግባር አለኝ” ብሎ እምነት የሌለው ሰው እኩል ናቸው፤ ኹለቱም መንግሥተ ሰማያት አይገቡም፡፡
ስለዚህ “እምነት አለን” ብለን ልል ዘሊላን አንኹን ብዬ እማልዳችኋለሁ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስም እንዲህ ይላልና፡- “በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ፥ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም” (ማቴ.7፡21)፡፡
ስለዚህ እምነት እንደሌላቸው ሰዎች ከመንግሥተ ሰማያት ውፁአን እንዳንኾን #የእግዚአብሔርን ፈቃድ ነቅተን እንሥራ፡፡ ምግባር ትሩፋትን ተግተን እንሥራ፡፡ አምነን ልጅነትን ከተቀበልን በኋላ ልጅነታችንን አጽንተን የምንጠብቀው፣ ርስቱንና መንግሥቱንም የምንወርሰው ይህን ያደረግን እንደ ኾነ ነውና ነቅተን እንሥራ፡፡
እኛ ሥራ ሠርተን አንበቃምና ጽዋ ተርታችን ዕድል ፈንታችን ይህ ይኾን ዘንድ ከባሕርይ አባ ከአብ፣ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ጌትነቱ፣ ኃይሉና ክብሩ አንድ የሚኾን ጌታችንና መድኃኒታችን በቸርነቱና ሰውን በመውደዱ ይርዳን፤ እስከ ዘለዓለሙ ድረስ አሜን!!!

@aleroe
703 viewsTesfabel, 20:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-28 23:17:44 ኤልሮኢ:
፨ጊዜዬን ባርክልኝ፨
በዝናብ አብቅለህ በፀሐይ አብስለህ
የምትመግብ ጌታ ሁሉን አዘጋጅተህ
ነጻነቱን ሰጥተህ ጥበቡን አድለህ
እዚህ ላደረስከኝ ምስጋና ይድረስህ
ሁሌም ጠብቀኸኝ በምሕረት ጥላ
ጊዜን ባርክልኝ ሰርቼ እንድበላ
ከፍጥረታት ሁሉ አልቀህ ፈጥረኸኝ
የጸጋን ገዢነት በፍቅርህ አድለኸኝ
ከቤትህ እንድኖር ርስትአውረሰኸኝ
ለዚህ ያበቃህኝ ከቶ እኔ ማነኝ
ያለኝ ምስጋና ነው አምላክ ክበርልኝ
እኔ ስበድልህ አንተ ስትምረኝ
በምሕረት ታግለህ ፈጥነህ ሳታጠፋኝ
ንስሐ እንድገባ ጊዜን ባርክልኝ።

@aleroe
525 viewsTesfabel, 20:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-28 23:17:34 ኤልሮኢ:
#እያለፈ_ነው_ዘመኔ

እያለፈ ነው ዘመኔ ትእዛዙን ሳልፈጽም
ወየው ለእኔ/2/ 
በጠራኝ ጊዜ ምን እላለሁ
ና ብሎ ወደእኔ/2/ 

በወጣትነቴ ሳልሠራ እያየሁ አለፈኝ
ብዙ አዝመራ/2/ 
ከእንግዲህ በመሥራት ጌታ ሆይ
ልኑር ከአንተ ጋራ/2/ 

የማስብበት በየለእቱ ንጹሕ ልብን
ስጠኝ አቤቱ /2/ 
ከትእዛዝህ ውጪ በመሆን
እዳልቀር በከንቱ /2/ 

እንደየሥራው ለመስጠት
በግርማ መንግሥቱ ሲመጣ/2/ 
ማን ይሆን የሚቆም ከፊቱ
ፊተናን የወጣ/2/ 

እንዳያስቷችሁ ተጠንቀቁ
እየተማራችሁ ከቃሉ/2/ 
ይመጣሉና በእርሱ ስም
አምላክ ነን የሚሉ/2/ 

ትእግሥትን በመያዝ ሁላችሁ
እስከመጨረሻው ጠንክሩ/2/ 
ያን ጊዜ ይሆናል በእርሱ ዘንድ
የማዳን ተግባሩ/2/


@aleroe
517 viewsTesfabel, 20:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-04 14:48:53
#ዜና_ዕረፍት

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አራተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ከዚህ ዓለም ድካም ዐረፉ።

ሃሌ ሉያ ግሩማን መላእክት ሱራፌል ወኪሩቤል እለ አክናፊሆሙ ነበልባል ወረዱ ዮም ይተቀበሉከ በብሒል አማን መርቆሬዮስ

#በዕለተ_መርቆሬዎስ_መርቆሬዎስ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አራተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ከዚህ ዓለም ድካም በትናንተናዎ ዕለት ከለሊቱ 6 ሰዓት ዐርፈዋል።

አቡነ መርቆርዮስ ከብፁዓን ጳጳሳት ጋር ከሀያ ስድስት ዓመት ስደት በኃላ ሐምሌ 25/2010 ዓ.ም አስራ ዘጠኝ ሊቃነ ጳጳሳት እና አገልጋይ ካህናት ጋር ወደ ሀገር ቤት ተመልሰዋል።

#ከስደት_ወደ_ሃገራቸው_የተመለሱትም_ያረፉትም_በዕለተ_መርቆሬዎስ_ነው

በረከታቸው አትለየን።
◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈

@FENOTESELAM27
❖◈❖◈❖◈❖◈❖◈❖◈❖◈❖◈❖◈
|የቡራዩ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ካቴድራል ፍኖተ ሰላም ሰንበት ትምህርት ቤት
925 viewsTesfabel, 11:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ