Get Mystery Box with random crypto!

📚 አል ኢማን Tube - የቁርዓን መድረሳ

የቴሌግራም ቻናል አርማ alemantv1 — 📚 አል ኢማን Tube - የቁርዓን መድረሳ
የቴሌግራም ቻናል አርማ alemantv1 — 📚 አል ኢማን Tube - የቁርዓን መድረሳ
የሰርጥ አድራሻ: @alemantv1
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.52K
የሰርጥ መግለጫ

{{ያ ሁሉን በፈጠረው ጌታህ ስም አንብብ!}}
______________
[📖አል-ቁርአን 96:1-5]
📚ኢስላማዊ ጥሪ 📢 ɪsʟᴀᴍɪᴄ ᴄᴀʟʟɪɴɢ📚
 ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-06 21:27:20 የአሹራ ቀን ፃም በተመለከተ


አቡ ቀታዳ አል አንሷርይ አላህ መልካም ስራው ይውደድለትና እንዲህ አለ፦
የአላህ መልእክተኛ ﷺ ስለ አሹራ ቀን ፆም ተጠይቀው እንዲህም አሉ 【ያለፈውን አንድ አመት ወንጀል ያብሳል】ብለዋል።
(ሙስሊም ዘግቦታል።)

#መቼ_ነው_የሚጀመረው

የአሹራ ቀን ፆም የሚጀመረው፦ አሁን ያለንበት የሙሀረ ወር አስረኛው ቀን ላይ ነው። ይህም ማለት የፊታችን ሰኞ ነሀሴ 02/2014 ይሆናል ማለት ነው

#እንዴት_ነው_የሚፆመው

ነገር ግን አህለል ኪታቦችን ለመሀለፍ ዘጠነኛውን ቀን መፆም የፈለገ (በላጩም ይህ ነውና) የፊታችን እሁድ ላይ ይጀምርና እሁድና ሰኞን በተከታታይ ይፆማል ማለት ነው።

ዘጠነኛው ቀን መጨመር ያልተመቸው ደሞ አስረኛውና አስራ አንደኛው ቀን ማለትም ሰኞና ማክሰኞንን መፆም ይችላል

አስረኛው (የአሹራውን ቀን) ብቻ እንጂ ከፊትም ሆነ ከኋላ ማስከተል ያልቻለ ችግር የለውም አስረኛውን ቀን ብቻውን መፆም ይችላል። አንዳንድ ኡለማዎች አስረኛው ቀን ብቻውን ከፊት ወይም ከኋላ ሳያስከትሉ መፆም የተጠላ ነው ቢሉም ትክክለኛው ግን ያለምንም መጠላት መፆም ይችላል የሚለው ነው።

አቅም አግኝቶ የመፆም ፍላጎት ካለው ግን ሶስቱንም ቀናቶች 9ኛው, 10ኛውና, 11ኛው ማለትም (እሁድ፣ ሰኞና፣ ማክሰኞናን) መፆም እንደሚችል ኡለማዎች ገልፀዋል።

አላህ በሰላም ያድርሰን ፆመውም ከሚቀበላቸውና ያድርገን
1.0K viewsedited  18:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-20 12:31:50
እነዘመድኩን በቀለ ሲዘውሩት የነበረው የሙስሊሞቹ መጅሊስ በስተመጨረሻ ወደ ሙስሊሞቹ ተመልሷል።

አሁንም እዛ ሰፈር እያለቀሱ ነው።
1.6K views09:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 05:33:50
386 views02:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 05:33:43 ከአል ኢማን Tube
የቁርዓን ት/ቤት

የምንሰጣቸው አስተምህሮቶች

የዓረብኛ ፊደላት አስትምሮ በአጭር ቀናት ንባብ ማስጀመር (ለጀማሪዎች)
በተጅዊድ የቁርኣን ንባብ(ቲላዋህ ነዘር)
የቁርኣን ሒፍዝ

ከዚሁ ጋር ተያይዞ

ልዩ የተጅዊድ ትምህርት (ለጀማሪዎች)
ልዩ የተጅዊድ ትምህርት (ቁርኣንን ማንበብ ለሚችሉ)

ትምህርቱ የሚሰጠው!

በኢሞ (imo) እና
በዩቱብ (You Tube)

ለመመዝገብ ከታች ያሉት ስልኮች ይጠቀሙ


1 ሰአዳ መሀመድ (ሳውዲ)
+966595309742

2 መዲና ወርቁ (ሳውዲ)
+966503738509

3 ሀያት አሊ (ሳውዲ)
+966594157769

4 ካሚላ (ሳውዲ)
+966504709485

5 አዚዛ ዩሱፍ (ጆርዳን)
+962796191477

6 ኡኽት ሙሀመድ (ዱባይ)
+971525700661

7 ሂበቱሏህ (ዱባይ)
+971509406972

በልዩነት በአጭር ጊዜ ቁርዓን ለማንበብ ይፈልጋሉ።
371 views02:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 19:29:26 #ተአምረኛው #ቁርዓን


#ይህን_ያውቁ_ኖሯል?

#በቁርዐን “ይህኛው አለም(ዱንያ)” የሚለው ቃል 115 ጊዜ ሲጠቀስ “መጪው አለም (አሄራ)” የሚለውም እንደዚሁ 115 ጊዜ ነው የተጠቀሰው፡፡

“ #መላይካ” የሚለው ቃል 88 ጊዜ ሲጠቀስ “#ሸይጣን” የሚለውም ቃል እንዲሁ 88 ጊዜ ነው የተጠቀሰው፡፡

“#ሰዎች” የሚለው ቃል 50 ጊዜ ሲሆን የተጠቀሰው “#መልዕክተኞች” የሚለውም እንደዚሁ 50 ጊዜ ነው የተጠቀሰው፡፡

“#ልማት” የሚለው ቃል 50 ጊዜ ሲጠቀስ “#ጥፋት” የሚለውም እንዲሁ 50 ጊዜ

“#ዘካ” የሚለው ቃል 88 ጊዜ ሲጠቀስ “#በረካ” የሚለውም እንዲሁ 88 ጊዜ

“#ሴት” የሚለው ቃል 24 ጊዜ ሲጠቀስ “#ወንድ” የሚለውም እንዲሁ 24 ጊዜ

“#ህይወት” የሚለው ቃል 145 ጊዜ ሲጠቀስ “#ሞት” የሚለውም እንዲሁ 145 ጊዜ

“#ጥሩ #ስራ” የሚለው ቃል 167 ጊዜ ሲጠቀስ “#መጥፎ_ስራ” የሚለውም እንዲሁ 167 ጊዜ


“#ነጳነት” የሚለው ቃል 36 ጊዜ ሲጠቀስ “#ጭንቀት” የሚለውም እንዲሁ 36 ጊዜ

“ #ትክክለኛ #ሰዎች” የሚለው 6 ጊዜ ሲጠቀስ“#የጠመሙ #ሰዎች” የሚለውም እንዲሁ 6 ጊዜ

“#ግልጵ” የሚለው ቃል 16 ጊዜ ሲጠቀስ “#ድብቅ” የሚለውም እንዲሁ 16 ገዜ

“#መውደው” የሚለው 83 ጊዜ ሲጠቀስ “#መታዘዝ” የሚለውም እንዲሁ 83 ጊዜ

“#ጥረት” የሚለው ቃል 102 ጊዜ ሲጠቀስ “#ትዕግስት” የሚለውም እንዲሁ 102 ጊዜ

“#ሰላት” የሚለው ቃል በቁርዐን ላይ 5 ጊዜ ሲጠቀስ የቀን ግዴታ ሰላቶች እንዲሁ 5 ናቸው

“#ወራቶች” በቁርዐን ላይ 12 ጊዜ ሲጠቀስ፤ በአመት እንዲሁ 12 ወራቶች ናቸው

“#ቀን” የሚለው ቃል በቁርዐን ላይ 365 ጊዜ ሲሆን የተጠቀሰው በአመትም እንዲሁ 365 ቀናቶች ናቸው።

“#ባህር” የሚለው ቃል 32 ጊዜ ተጠቅሷል፤ ”#መሬት” የሚለው ቃል ደግሞ 13 ጊዜ፡፡


እስቲ የሰባተኛ ክፍል ተማሪ የሚሰራውን ካልኩሌሽን እንስራ፡፡ቁርዐን ላይ “#ባህር” የሚለው ቃል በፐርሰንት “መሬት” እና “ባህር” ተብሎ ከተጠቀሰው ብናነጳጵር=32(32+13)x10=71.12% ሲሆን
☞“#መሬት” የሚለው ቃል ደግሞ በፐርሰንት “መሬት” እና “ባህር” ተብሎ ከተጠቀሰው ብናነጳጵር=13(32+13 )x100=28.888% ይመጣል፡፡

#በሌላ #አነጋገር 72.12% አለማችን ባህር ሲሆን 28.88% ደግሞ መሬት መሆኑን ያሳየናል፡፡

#ቀርዐን ላይ ያሉት የሱራዎች ብዛት ከአያዎቹ ጋር በ ግራፍ ሲቀመጥ ከታች ወይም ከላይ የምትመለከቱት እልቅናው ከፍ ያለውን የአላህን ስም ቅርጵ የያዘ ነው፡፡

#በቅርቡ በአሜሪካ ጥናት አድርገው በግብጵ ካይሮ ላይ በተደረገው medical conference የግብጵ ካርዲዎሎጂስትና በአሜሪካ የኢስላማዊ ህክምና ተቋም ሀላፊ የሆኑት ዶክተር አህመድ አል ቃዲ በጥናቱ እንዳረጋገጡት “#ቅዱስ #ቁርዐንን ማዳመጥ ከጭንቀት ያስወግዳል፡፡

ይህንንም ጥናት ያደረግነው ዘመናዊና ትክክለኛ በሆኑ መሳሪያዎች ነው፡፡ባደረግነው ጥናት ከ 80 ፐርሰንት በላይ የሚሆኑት ሙስሊም የሆነውም ያልሆነውም ፤ አረብኛ ሚያውቀውም ማያውቀውም ቁርአንን በሚያዳምጡ ጊዜ ጭንቀትን እንደቀነሰላቸው ተናግረዋል፡፡

#ጭንቀት በሰውነታችን ላይ ያለውን immunity እንዲቀንስ ያደርገዋል::ይህ ደግሞ ሚከሰተው በአንዳንድ የሰውነታችን ንጥረነገሮች ወይም በ nervous system እና endocrine glands መካከል በሚደረገው ውህደት በሰውነታችን ውስጥ የሚፈጠረው አለመመጣጠን ነው፡፡
429 views16:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 08:41:20
457 views05:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 05:12:30 عِـــــــــيْــــــــدٌكـــم مُــــــبَــــارك!

تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال !
464 views02:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 21:29:50 ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
በዓሉ የሰላም፣ የጤና እና የደስታ እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ፡፡
513 views18:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 21:09:12
500 views18:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ