ማልኮስ ማልኮስ ማነው? በዮሃ 18 ላይ ከይሁዳ ጋር አብሮ: ኢየሱስን ሊይዙ ከካህናት አለቆችና እና ከፈሪሳውያንም ሎሌዎች መካከል ወይ ጦር እና ጋሻ አልያም ችቦ እና ፋና ይዞ የመጣ ነው:: ኢየሱስን ያውቅ ነበር? በፍፁም:: እንደውም ኢየሱስ:- ማንን ትፈልጋላችሁ? ብሎ ሲጠይቃቸው.... እነርሱም፡— የናዝሬቱን ኢየሱስን፡ ብለው ሲመልሱለት እርሱም : እንግዲህ፡— እኔ ነኝ ባላቸው ጊዜ ወደ ኋላ አፈግፍገው በምድር ሲወድቁ መፅሃፍ ቅዱሳችን ይነግረናል:: ታድያ በዚህ መካከል ስምዖን ጴጥሮስ ሰይፍ ስለነበረው ሰይፉን ሲመዝዘው፥ የሊቀ ካህናቱንም ባርያ/ማልኮስን መትቶ ቀኝ ጆሮውን ሲቈርጠው እንመለከታለን:: "ስምዖን ጴጥሮስም ሰይፍ ስለ ነበረው መዘዘው" ዮሃ 18:10 ሰይፍ ስላለ አይመዘዝም ጥቅስ ስላለ አይጠቀስም ድንጋይ ስላለ አይወረወርም ከኢየሱስ ይህን አልተማርንም ወዳጆቼ "እስቲ አጠገባችሁን ያለውን ሰው ጎሰም አድርጉትና: ሰይፍ ስላለህ አይመዘዝም በሉት" የሚለን ሰባኪ ያሻናል:: እንኩዋንስ ኢየሱስን እያወቀ ያጠፋ: የሳተ: የተሳሳተ:የወደቀ....ወንድማችን ይቅርና ኢየሱስ የማያውቀው ማልኮስን እንድንመታ: እንድንወግር ሰይፋችንን እንድንመዝዝ አልተፈቀደልንም:: ይህን ስል ያጠፋ አይመከር:አይገሰፅ እያልኩ አይደለም:: ነገር ግን በሰይፍ አይመከርም ነው ሃሳቤ!! አስባችሁታል ጥፋትን ያጠፋ ሰው: ሰይፍን ግራ ቀኝ እያወናጨፋችሁ "ልመክርህ ነው ስማኝ!!" ብትሉት ?? ይህ ሰው እየተመከረ በመሃል: ሳይጨርስ ወይ ጆሮ አልያም አንገቱ ሊቀላ ይችላል:: ተመካሪውም ላይሰማ እና ላይመለስ እስከወዲያኛው ልናጣው እንችላለን:: መልእክቴ ይህ ነው: ኢየሱስም ጴጥሮስን፡— ሰይፍህን ወደ ሰገባው ክተተው እንዳለው: ሰይፋችንን ወደ ሰገባችን ከትተን: እጃችንን ለማቀፍ እና ለመርዳት ይዘርጋ:: ሳሙኤል ተስፋሚካኤል ብዙነህ 3.3K views06:39