Get Mystery Box with random crypto!

የሕይወት ምክር (PSYCHOLOGY)

የቴሌግራም ቻናል አርማ alazaryehiwotmiker — የሕይወት ምክር (PSYCHOLOGY)
የቴሌግራም ቻናል አርማ alazaryehiwotmiker — የሕይወት ምክር (PSYCHOLOGY)
የሰርጥ አድራሻ: @alazaryehiwotmiker
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 263
የሰርጥ መግለጫ

በተለያዩ መንፈሳዊ ሥነ ልቦናዊና ማሕበራዊ ጉዳዬች ዙሪያ ምክር የሚሰጥበት ቻናል ነው (አልዓዛር ሱፋ)

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-01 22:58:00
እኛ በሕይወታችን በጣም የምንመኛቸው ዝናና ገንዘብ እጅግ የተረፈው ክርስቲያኖ ብዙ ነጻነት የሌለው ሕይወት እንዳለው ተመልከት ሁሉም ሰው ላይ በየትኛውም ደረጃ ባለ ሰው ላይ በብዙ ሙላት ውስጥ ብዙ ጉድለቶች አሉ የምትመኘውን ሕይወት እስክታገኝ አትጠብቅ አሁን ባለሕ ነገር ደስተኛ ሁን ።
292 viewsedited  19:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-25 11:11:50 • ሙሴ የፈርኦን የልብ ድንዳኔ ውጤት ነው ፡፡ ፈርኦን ሙሴን ”እባክህ እኔ እና አንተ እንስማማ እባክህ ይህን ወይም ያንን አታድረግብኝ …“ እያለ እየለመነው መልሶ እዛው ክፋትና ጥፋት ውስጥ የሚዋኝ ሕዝቡን የሚያሰቃይ ምርጥ ተዋናይ ነበር፡፡ ለፈርኦን የኤርትራ ባህር የገባበት 11ኛው መቅሰፍት ድረስ ሁሉም ነገር ቀልድ ነበር ግፍ የማይፈራ ስለነበር የሚያወራው እና የሚሠራው ፍጹም የተራራቀ ነው፡፡
በመጨረሻም ሙሴ የእግዚአብሔር የምሕረቱና የቸርነቱ የቁጣውም ውጤት ነው ፈርኦንን ተጠቀመበት ልቡን አደንድኖ ሕዝቡን አስተማረበት ለሚፈረድላቸው ቸርነቱ ስትደርስ ለሚፈረድባቸው ግን ቁጣው ነደደች አጠፋቻቸውም ፡፡
አቤቱ ሙሴን ስጠን

አልዓዛር
https://t.me/alazarsayehiwotmiker
https://t.me/alusa0910
426 views08:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-25 11:11:50 አሻጋሪው መሪ
መሪ የመሆንን ጉዳይ ሲነሳ እንደ ሙሴ ምሳሌ ሆኖ የሚቀርብ አላየሁም ሙሴ ምርጥ የመሪ ምሳሌ ነው በመምራት ጥበቡ ሕዝቡን አንተ ብቻ ምራን ያሰኘ ሚገርም መሪ ነው ፡፡ ታዲያ ሙሴን የመምሰል እና እንደ ሙሴ አይነት መሪ መሆን የመሪዎች ምርጫ አይደለም ምክንያቱም ሕዝቡን ከባርነት ማውጣት ባህሩንም ማሻገር የግዴታ አማራጭ የሌለው ጉዳይ ስለሆነ፡፡ ሕዝቡን ይዘህ መንገድ ጀምረህ ሕዝቡ እጅህ ላይ ወድቆ ከማሻገር ውጪ ምንም አማራጭ የለህም አለበለዚያ ወይ ባህሩ ወይ ፈርኦን አንተንም ሕዝቡንም ይበላል ፡፡


አሻጋሪው ሙሴ ማነው ምን አይነት ስብዕናዎችስ ነበሩት ? ሙሴ ገራሚ መሪ ነው ፡፡ ሙሴ በጣም ትሁት ነበር እንደ ሙሴ ትሁት የሆነ ሰው አልነበረም የተባለለት መሪ ነበር ሙሉ የመሪ ስብዕና የተሞላ ሰው ሆኖ ሳለ ነገር ግን እንዲህ ሲል አንሰማዋለን ”እኔ አፈ ኮልታፋ ነኝ ይሄንን አደርግ ዘንድ እንዴት ይቻለኛል…!!!“ ሰው መርጦት አክብሮት እንዲመራ ተደርጎ ቢሆን ዘመዳቸው ስለሆነ ጥቅም ፈላጊዎች ስብስቦ ተመረጠ ደግሞም ሕዝቡ ተሸውዶ ይሆናል ልንል በቻልን ነበር ነገር ግን ሁሉን አዋቂ ጌታ እግዚአብሔር “መምራት ትችላለህ ሕዝቡን ነጻ ለማድረግ አንተን በፈርኦን ላይ አምላክ አድርጌኅለው“ ቢለው እንኳን እኔ ለዚህ አልበቃም ያለ ሙሴ ትሁት ነበር ያልኩት እግዚአብሔር በግልጽ መርጦት ሳለ ራስን ዝቅ በማድረግ ኃይለኛነቱን ስለገለጠ ነው ፡፡


ቅን መሪ የሚፈጠሩትን ችግሮች ወደ ጥሩ አጋጣሚ የመለወጥ አቅም ያለው መሪ ነው እንደገናም ደጋፊዎችም ተቃዋሚዎችም የሚናገሩትን በቅን ኃሳብ መውሰድ እና መረዳትን የሚችል መሪ ማለት ነው፡፡


አንድ ቅን መሪ ሁሌም የሚያስበው ከዛሬ ነገ ይሻላል ብሎ ነው ዛሬ ላይ ሆኖ ነገን በቅንነት ይሠራል እንኳን ላየው እና አብሮት ላለው ይቅርና ላላየው ገና ላልተፈጠረው ትውልድ ጭምር ይሠራል ፡፡ ውስጡ ተንኮል እና አሻጥር የለበትም የሚሠራው የሆነን አካል ለመበቀል ወይም ለማጥፋት አይደለም የሱ ኃሳብ ሁሉን ወደ ትክክለኛው ሀገር ማሻገር ነው ፡፡


እሥራኤል በጣም አስቸጋሪ ሕዝብ ነው በዛ ላይ በበረሃ ጎድሎባቸው ደግሞ ምን ያህል መርዛማ እንደሚሆኑ ማሰብ አያዳግትም ፡፡ ሙሴ ይሄንን ሕዝብ በፍጹም ቅንነት ክፉ ኃሳባቸውን በቅን ልቡ እያቀና ይመራው ነበር ፍላጎታቸው እጅግ የሚያስደንቅ ነበር በፍላጎታቸው መብዛት የ 40 ቀኑን መንገድ ወደ 40 ዓመት ቀይረውታል አልቅሰው የወጡበት የግብጽ ባርነት ሳይቀር ዳግም ይመኙት የነበሩ ግሩም ሕዝብ እኮ ነው!!!


ይህንን ሕዝብ ታግሶ መምራት ነው መሪ መሆን የሚያሰኘው፡፡ ልጅ ምንም ክፉ ቢሆን ልጅ ነው ለሙሴም ሕዝቡ ምንም ያህል አስቸጋሪ ቢሆን ከእነሱ ቀድሜ እኔ ልጥፋ ያለ አባት ነው መሪ የዋህ እና ልባም መሆን ያለበት ስለዚህ ነው፡፡

ሕዝብ መሪውን አምኖ በመሪው ተማምኖ መጓዝ ለርሱ አማራጭ የሌለው ጉዳይ ሆኖ የሚቀርብበት አጋጣሚ ብዙ ነው ምክንያቱም በብዙ ሺ እና ሚሊየን ጭንቅላቶች መመራት መጨረሻው መበታተን ነው ምንም ያህል ሕዝቡ መልካም ቢሆን ያለ መሪ ከመሄድ ክፉም መሪ ቢመራው ይመርጣል አንድ ግዜ የሱማልያ መሪ እንዲህ ሲል ተናግሯል “መሪ ከሌለው ሕዝብ ሕዝብ የሌለው መሪ(መንግስት) ይሻላል ”፡፡


መሪዎች ወደ ሥልጣን ሲመጡ ከሚገልጹት ፣ ከሚታየውና ከምንረዳው ዓላማቸው ባሻግር የተሰወረ ድብቅ ዓላማ ይኖራቸዋል እያደር የሚገለጸው ይሄ ነው ወደ ሥልጣንም የሚሔዱበት ዋና ጉዳያቸውም ይሄ ነው ሕዝቡ እየቆየ ይገባዋል ዓላማቸው ጥፋት እና የራስ ጥቅም ላይ ያተኮረ ከሆነ ሕዝብ ማጉረምረም ይጀምራል ፍትህ እያጣ የመጣ እንደሆነ ”ወይ ፍረድ ወይ ውረድ..” ይላል ሙሴ ትልቁ የእግዚአብሔር ዓላማ ዓላማው በመሆኑና ግላዊ ጥቅም ላይ ያተኮረ እና ቤተሰቡን ብቻ የመጥቀም መርህ ባለመከተሉ እርሱ ተሻግሮ ሕዝቡን አሻግሮታል፡፡


እሥራኤል ግብጽን ለቆ ሲወጣ የት እንደሚወስደው እንዴት እንደሚወስደው እንኳን ብዙ መረዳት የለውም የገዛ መሪው ሊያሻግረው ወይም ደግሞ ሊያሰጥመው እንደሚፈልግ አያውቅም ልብን መመርመር የሚችለው እግዚአብሔር ብቻ ስለሆነ እርሱ መሪውን ተከትሎ ከነአንን የመውረስ ተስፋ ብቻ ይዞ የመንጎድ ግዴታ ብዙኃኑ ላይ ይወድቃል፡፡


ታዲያ መሪ ሕዝቡን ካልወደደ ምን ያህል ማጥፋት እንደሚችል አስቡት አንዳንዴ ሕዝብ የእውር ድንብር የሚሆነው ማስተዋል ስለሌለው ሳይሆን ሹመቱን ከፈጣሪ ነው ብሎ ስለሚቀበልና በመሪ ላይ የሚደረግ ነውጥ ብዙ ችግር ያመጣል ብሎ ከመሪው በተሻለ ስለሚያስተውል ነው፡፡ እንጂማ አመጽ ምንም አይነት ትምህርት እና ልምድ አይጠይቅም ሁሉም ሰው ሊያደርገው የሚችል ተራ ጉዳይ ነው ጉዳቱ ቢብስም ታዲያ ያ ሲሆን በምትጠላው መመራት የግድ ይላል፡፡


ሙሴ የሚጠሉትን የሚወድ መሪ ነበር ሕዝቡ ብዙ ብለውታል እርሱንም የመግደል ሙከራ አድርገውበታል የገዛ ቤተሰቦቹ ሳይቀር የርሱን መሪነት ማጣጣልና ማዋደቅ ይዘው ነበር ግን በቂም በበቀል ወደ አነርሱ አልመጣም በምሕረት አይን ተመለከታቸው እንጂ ተንኮል ቢያስብ ሙሴ የሚወዱትን እየለየ ያጠፋቸው ነበር ግን ራሱን አዋርዶ የራሱን ድሎት ሳይሆን የሕዝቡን ድሎት መረጠ አሻጋሪ መሪ ስትሆን ጠላትህን ወዳጅህን ለሁለቱም ምርጥ ቦታ ይኖርኃል፡፡

ታዲያ ሙሴ ሰጦታ ነው ምርጫ?

• ሙሴ በፍጹም የምርጫ ጉዳይ አይደለም ሙሴ ስጦታ ነው ሙሴን ያመጣው ጸሎትና ንስሃ ነው ሕዝብ በድያለሁ ብሎ ሲያምን እና ፈጣሪ ይህን እንዲያስተካክልለት ሲለምነው ብቻ ሙሴ ከበረሃ ይመጣል ፡፡ ሙሴ ራስን የመምረጥም እኔ ነኝ ማስተካክለው የማለትም ጉዳይ አይደለም ሙሴ ራስን ዝቅ በማድረግ በትህትና ለእረኛነት ራስን የማዘጋጀት ጉዳይ ነው፡፡


• ሙሴ መሪ የለም በተባለ ጊዜ መሪ ሆኖ የወጣ ምርጥ መሪ ነው ሰው ሰውኛውን ሲታይ ሁሌም ቢሆን ደግ እና ጥበበኛ መሪ የለም ግን እግዚአብሔር ጋር አለ እንዴት ከርሱ ይህን ስጦታ እንቀበል ነው ጉዳዩ፡፡


• ሙሴ የመከራ እና የእንባ ውጤት ነው ይህን ባልናገር ልጆቿን ጭቃ ውስጥ ሲያስረግጧት ደም አንባ ያነባችው እንባዋም ሰማይ ወጥቶ መልስ ይዞ የመጣው ራሔል ምን ትለኛለች…?? የማይታይ የሚመስለው እንባ እርሱ በእግዚአብሔር ይታያል


• ሙሴ የአስተዋይ እናት የአስተዳደግ ውጤት ነው ምን ብላ እየነገረች እንዳሳደገችው አልነግራችሁም የሙሴ ሥራው ስለሚገልጽላችሁ እናቶች የሙሴን እናት ሳትመስሉ ሙሴን አትጠብቁ፡፡


• ሙሴ የቅንዓት ውጤት ነው የወገኑ መራብ መከራና ስቃይ ከሱ በንጉስ ቤት ከኖረበት ምቾት ይልቅ በለጠበት ለወገኑ ሲል ተሰደደ
315 views08:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-15 18:08:19 አንተም እንደራስህ ትኩረትህ ያለህ የሠራኸው መልካም ነገር ላይ ይሁን ሰዎችንም ስትመለከት ኃላፊዎችንም ስታስብ ያላቸው መልካም ነገር ላይ አተኩር በተሠራው መልካም ነገር የምታመሰግን ሁን ትችትህ በፍቅርና በትህትና አድርገው ስንዴውን ተንከባከብ እንጂ እንክርዳዱን በመንቀል ጊዜህን አታጥፋ ፡፡
አልዓዛር
https://t.me/alazarsayehiwotmiker
https://t.me/alusa0910
138 views15:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-15 18:08:19 የመንቀፍ የመተቸት(የመቃወም) መንፈስ
*****************************************
አንድ ጤነኛ ያልሆነ አስተሳሰብ ላይ መሆንህን ለማወቅ ከፈለግኅ 2 ነገሮችን አጢን ሰው ሁሉ የሚሠራው የማይጥምህ አንተ ግን ምንም ለመሥራት የማትፈልግ ስትሆን እና የሰው ከፍታ ስኬት የማያስደስትህ ወይም የሚያበሳጭህ ሲሆን እነዚህን መንቀፍና መቃወም አደገኛ ምልክቶች ናቸው፡፡


ነገራችንን ብንመለከት እንደ ሀገርም የመመሰጋገን እና የመተጋገዝ ባህላችን በጣም የሚያስገርም ነው ማመስገን እና አመስጋኝ የሚጠላበት ሀገር ፡፡

ችግሮችን ነቅሶ በማውጣት መወያየት፤ ለመፍትሄውም መምከር የሚበረታታም የሚፈለግም ጉዳይ ነው፤ ከብዙ መልካም ነገሮች ይልቅ ጥቂት ስህተቶችን እየለቃቀሙ አንድም መፍትሄ ሃሳብ ሳይዙ ነቀፌታ ላይ ማተኮር ግን በሽታ ነው።

ሶቅራጦስ አለ ብሎ ያነበብነውን እስቲ እንመለክት። አንድ ሰውዬ ወደ ታዋቂው ፈላስፋ ሶቅራጦስ ይቀርባል፤ “ስለ ጓደኛህ አንድ ወሬ ልነግርህ ነበር…” ይለዋል።ሶቅራጦስም “ቆይ አንዴ! ምንም ነገር ሳትነግረኝ በፊት ሦስቱ ወንፊቶች ወይም ማጥለያዎች ብዬ የምጠራቸውን ጥያቄዎቼን ላንሳልህ…”ሲል ይጠይቀዋል።

“ሦስቱ ወንፊቶች?” ሲል ሰውዬው ራሱን ጠየቀ። “አዎ!” ሲል ሶቅራጦስ መለሰ።የመጀመሪያው ወንፊት እውነታ ነው፤ አሁን የምትነግረኝ ነገር እውነት መሆኑን እርግጠኛ ነህ?” ሲል ሶቅራጦስ ሰውዬውን ይጠይቀዋል። ሰውዬውም “እርግጠኛ አይደለሁም! እኔ እንጃ! ሰው ነው የነገረኝ…”ሲል ይመልሳል።

ሶቅራጦስ “ስለዚህ… እውነት ይሁን አይሁን አታውቅም!” ብሎ በሁለተኛው ወንፊት ላይ ተመስርቶ ጥያቄውን ያስከትላል።ሁለተኛው ወንፊት መልካም ዜና ወይም ወሬ ነው? የሚል ነበር፤ አይደለም ሲል ሰውየው ይመልሳል፤ እንደውም በተቃራኒው ነው አለው።ሶቅራጦስ “በአጭሩ… ልትነግረኝ የመጣኸው… ስለ ጓደኛዬ እውነት መሆኑን ያላረጋገጥከውን መጥፎ ነገር ነው ማለት ነው›› ሲል መለሰለት።

አንድ ወንፊት ይቀራል! በሱ ወንፊት ካለፍህ ወሬውን ልሰማህ እችላለሁ…” ሲል ሶቅራጦስ ይገልጻል።በ“ሶስተኛው ወንፊት የምትነግረኝ ለኔ ይጠቅመኛል?” ሲል ሰውዬውን ይጠይቀዋል።ሰውዬውም “ይጠቅምሃል ለማለት አልደፍርም! ግን…” ይላል።ሶቅራጦስም “የምትነግረኝ ነገር እውነት ካልሆነ እንዲሁም የማይጠቅመኝ ከሆነ ለምን ልትነገርኝ መጣህ?” ሲል ሰውዬውን ይጠይቀዋል።ሰውዬው ምላሽ አልነበረውም።

ቀደም ሲል ለተጠቀሰው አይነት በሽታ አንዱ መፍትሄ የሶቅራጦስ አይነት ማንጠሪያ ማዘጋጀት ነው፤ ሌላኛው ደግሞ ማንኛውም ሰው ችግር አየሁ ብሎ አንዳች ነቀፌታን በሚሰነዝርበት ቅጽበት የመፍትሄ አካልም እንዲሆን መጋበዝ ነው፤ በዚህም አይነት መንገድ ክፉ ብቻ የሚታያቸውን በመተቸት የተካኑ ግለሰቦች ላመጡት ነቀፌታ መፍትሄ እንዲያቀርቡ ሲጠየቁ በጎንም ለማየት ይሞክራሉ፤ አሊያም ለአንደበታቸው ልጓም ያበጃሉ።


ሁሌም ቢሆን አሉታዊ ኃሳብና ንግግር የሚያመጣው አሉታዊ ውጤት ነው፡፡ ታዲያ ብዙ ሰዎች በተሠራው አንድ ቁም ነገር ላይ ”በጣም ጥሩ ተሠርቷል የበለጠ የምትሠሩበትን ጤና እና ብርታት ይስጣችሁ“ ለሚሉት ቃላት በጣም ሩቅ ናቸው እንደውም ይህን መናገር አሸርጋጅነት፣ተለማማጭነት ተደርጎ ይወሰዳል ጉድለት ጉድለቷን እያሰሰ ችግሮችን እየቆፈረ ለማሳጣት፣ለማዋረድ የሚደክም ጀግና ይባላል፤ ነገር ግን ያ ሰው አንድ ውጤት ለማበርከት ወይም በትንሹ ኃላፊነቱን ለመወጣት ወይም ውኃ እንኳን ለማቅናት አይፈልግም አንተስ ? በመረጃ ላይ ሳይመሠረቱ መፍረድ፣መተቸትና መላምት መስጠት ከማዋረድ እና ከማጥፋት ባሻገር መቼም ቢሆን ደስታ እና ሰላም አይሰጥም።


በፊት በምሠራበት መሥሪያ ቤትም የገጠመኝ ይህንኑ ነው ችግር በጣም ማየት የሚቀናቸው ሰዎችን ተከትለን በአለቆቻችን ላይ አመጽን ነገሩ እንዳልነው ሆኖ ሜዳውም ፈረሱም ያው ሲባል ግን የአመጹ ቀስቃሾች አንድም ነገር ማድረግ አልፈለጉም ትተውን ዞር አሉ ለካ ኃላፊዎችን ማሳጣት ፣ መተቸት፣ ማጣጣል፣አንድ ክፍተት ሲገኝባቸው በአመጽ ማውረድ ለነርሱ ሥራቸው መዝናኛቸውም ሱሳቸውም ነበር፤ ያን ትተው ሌላ የሚያጣጥሉት ደግሞ መፈለጉን ያዙት ነገር ግን ተያይዘን ገደል ገባን እንጂ አንድም ያተረፍነው ነገር አልነበረም፡፡


እንደዚህ ያሉ ሰዎች ከፍተኛ የሥነ ልቦና ችግር ውስጥ ናቸው ይቀናሉ፣ መበለጥ አይፈልጉም፣ እኔ ከሌለው ሠርዶ አይብቀል እንዳለችው አይነት እኔ ካላሰብኩት፣ እኔ ካልተናገርኩት ፣እኔ ካልሥራሁት ይውደም የሚል ጽንፈኛ መንፈስ አላቸው በዚህም

1. ችግርን ብቻ በማየት ነቀፋን በመናገር አድማ ላይ በመሥራት የተሻለ እየሠሩ እንደሆኑ ስለሚሰማቸው ረብሻን ይፈጥራሉ
2. በአስተዳደጋቸው ቤተሰቡ በመነቃቀፍ ፍልስፍና የመጣ ከሆነ እንዲሁ ቤተሰባቸውን በነቀፌታ ይገነባሉ
3. የሰው ስኬት ደስታ የማያስደስታቸው የሚያስቀናቸው ሲሆን ለበጎ ነገር ቀናኢ መስለው ማዳከምና የሰው ውድቀት ሲያዩ ደስ የሚላቸው ይሆናሉ ይህንንም ከራሳቸውም አልፈው ሌሎችን የነሱ ውድቀት ውስጥ እንዲተባበሩ ያደርጋሉ


እኔና አንተስ ምን እያደረግን ነው ?


እንደ ሀገርም እንደ ቤተ ክርስቲያንም እንደ ግልም ማደግ የማንችልበት ትልቅ ማነቆ እንዲህ ባሉ ክፉ ድሮች እርስ በእርስ መጓተታችን ነው፡፡


ችግርን በባሕሪው ደጋግመህ ካወራኸው ችግሮች ወገን ዘመድ ሆነውኅ ነው የምትኖረው ችግርን ስታስብ ስለ ችግር ስታወራ የበለጠ ችግሩ እየጨመረ ነው የሚሄደው በግል ሕይወታችንም በማህበራዊ ግንኙነታችንም ችግራችን ላይ ስለምናተኩር ነው ከችግር መውጣት ያቃተን ድክመቶቻችንን እያሰብን መቼም ከድካም አንወጣም ስንት መልካም ነገር እያለን ለምን ድካማችን ላይ እናለቃቅሳለን ለምን በጠንካራ ጎናችን በኩል አንበረታታም ?
መነቃቀፍና መተቻቸት ላይ ብቻ ማተኮራችን ምን አመጣብን..?
1. ደጎች የእኛን አፍ ፈርተው ስለሚሸሹ ብዙ ጨካኝ ሰውን የማይሰሙ ግዴለሽ መሪዎችን ፈጠርን
2. ደግ ሰዎች በሠሩት መልካም ሥራ እንዲቆጩና ወደ መጥፎ ማንነት እንዲቀየሩ አደረግን
3. ሥራችንን ውኃ ቅዳ ውኃ መልስ ሆነ
4. በወሬና በሃሜት እራሳችንን አቁስለን ሌሎችን አቆሰልን
5. መተቸትና መንቀፍ እንደ አንድ ትልቅ የሥራ መስክ እንዲቆጠር አደረግን
6. ችግርን እያሰብን ችግርን እያወራን በችግር እየኖርን ነው


ከእግዚአብሔር በላይ በዓለም ላይ ያለ ሰው ሰይጣንን ያውቀዋል ለምን? ችግር ስለሚቀናን ነው በቀን ውስጥ እግዚአብሔር ከሚጠራው በላይ ሰይጣን አሳሳተኝ ሰይጣኔን አመጣው የሰይጣን አሠራር ነው ሰይጣን አደረበት ሰይጣን ለከፈው እርሱ ሰይጣን ነው…….. እያልን የወደቀው ሰይጣንን ስሙን ስናገነው እንውላለን ይህ የሚሆነው ውድቀትን ችግርን የማየት እርሱንም የመተንፈስ መንፈስ ሲጸናወተን ነው፡፡

ጻድቁ እዮብ ሰይጣንንም የባልንጀሮቹንም ትችት ቦታ ሳይሰጥ ሃብቱን ንብረቱን ያወደመበት ሠይጣን መሆኑን እያወቀ እግዚአብሔር ሰጠ እግዚአብሔር ነሳ ያለው ለሰይጣን ኃሳብ እና አሠራር ለሠይጣንም ቦታ እና እውቅና ላለመስጠት ሲል ነው፡፡ እክህደከ ሰይጣን የሚለው ቃል የመጣው ከሱ ከኢዮብ መሆን አለበት የእርሱ ጉዳይ እግዚአብሔርና እግዚአብሔር ብቻ ነውና ሰይጣንን ለሰይጣን ቦታ አልነበረውም፡፡
117 views15:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-13 15:48:05 የትኛው ይሻለኛል…?

(ምን መሰለኅ እኔ ዲፓርትመንት ልመርጥ ነው ከ ……... እና ከ ……. የትኛው ይሻለኛል ? ተምሬ ስወጣ ሥራ ላገኝበት የምችልበትን ነው የምፈልገው እባክኅ እርዳኝ የምትፈልጊውን ምረጥ እንዳትለኝ ምክንያቱም እኔ ሥራ ማገኝበትን ብቻ ነው የምፈልገው፡፡) ከቻናሌ አባል የተጠየቀ

ይህን ጥያቄ ከብዙ ሰው ሰማሁት በይበልጥ 12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈትነው ለከፍተኛ ትምህርት የታጩ የነገ ሀገር ተረካቢዎች ጭንቀት ነው በጣም ተቸግረው አይቻለው ይህ በኔ እይታ በግልም እንደ ቤተሰብም እንደ ሀገርም ትልቅ ኪሳራ ነው ፡፡ ለምን?

አንድ ተማሪ እስከ 12ኛ ክፍል ድረስ ምን መሆን እንዳለበት ሳያውቅ ከተማረ እመኑኝ ቀሪ ዘመኖቹ በዚው ጉዳይ ዋጋ እየከፈለ እየተወዛገበ እንዲሔድ ያደርገዋል ወዴት መሄድ እንደምትፈልግ ሳታውቅ እንዴት ጉዞ ትጀምራለህ ይህ የጨለማ ጉዞ ምናልባትም መጨረሻው የከፋ ሊሆን ይችላል? አስታውሳለው የዲግሪ 1ኛ ዓመት ተማሪ ሆኜ እኔ ማነኝ ? ምን መሆን ነው የምፈልገው? ወዴት መሄድ ነው የምፈልገው..? እያልኩ መሐል መንገድ ቁጭ ብዬ በኃሳብ ጦርነት የተሰቃየሁበትን ቀን በፍፁም አልረሳውም ለኔ ይሄ በጣም ከባድና አስጨናቂ የውስጥ ጥያቄ ነበር በዚህ ጉዳይ እንደተሰቃየሁት የተሰቃየሁበት ኃሳብ ያለ አይመስለኝም ከድቅድቅ ጨለማ የመውጣት ያህል ለነፍሴ በጣም አስጨናቂ ነበር ለሁሉም እንደተሰጠው ለራሴም ለሰው ልጆችም አንድ የምጠቅምበት ነገር እንደተሰጠኝ እረዳለው ግን እንዴት ላግኘው? ለሕይወት አስፈላጊ ጥያቄ ግን ደግሞ መልስ ለመስጠት አንገትን የሚተናነቅ የበዛ ኃሳብ የሚያከናንብ ከባድ ጥያቄ ..፡

ብዙ ሰው ይሕን ጥያቄ ለመመለስ ይፈራል ለምን?
1. የሚወደውን ነገር እንዳያገኝ ሰይጣን ይሸፍንበታል ምክንያቱም ያን አገኘ ማለት የተፈጠረበትን የሚሞትበትንም ጸጋውን ሙያውን አገኘው ማለት ነው
2. መስዋዕትነት እንደሚከፈልበት ስለሚያውቀው ይህን ለመክፈል ዝግጁ የሆነ ማንነት ካልፈጠረ ይፈራል
3. የሰዎችን ኃሳብ እየሰማ ግራ መጋባት ውስጥ ይገባል እናቱን አባቱን ቤተሰቡን ጓደኞቹን መምሕራኖቹን ለማስደሰት በማሰብ የምርጫ መደበላለቅ ውስጥ ይገባል
4. ገንዘብ ባላገኝበትስ..? በማለት ገንዘብን የሕይወቱ ምሰሶ በማድረጉ ነገሮች ይቃወሱበታል
5. እና…እናንተ በምታውቋቸው መሰል ምክንያች ይፈራል

አንድ ትልቅ ነጥብ የምንስተው ተሰጥኦ ወይም ጸጋ የምንለውን ጉዳይ የተፈጥሮ እውቀት እንደሆነና ለእያንዳንዳችን ይሕ እንደተሰጠን መዘንጋታችን ነው፡፡ ትምህርት ቤት ገብተን የምናገኘው እውቀት በተፈጥሮ ለተሰጠን ተሰጥኦ የሚያጠናክር የሚያግዝ እንጂ በራሱ ሙሉ እውቀት አይደለም፡፡

ይህ ምን ማለት ነው ?

ምሳሌ ስኬታማ ሰዓሊ ወይም ደራሲ ወይም……ለመሆን የሚፈልግ ሰው በቅድሚያ ማየት ያለበት ፍላጎቱን እና ተሰጥኦውን ነው ወይስ ገንዘብ አገኝበታለሁ ወይም ሰዎችን አስደስትበታለሁ የሚለውን ? የቱን ነው ማየት ያለበት ?ስኬታማ ሰዐሊም ሆነ ደራሲ ትምህርት ቤት ገብተህ ስለተማርኅ አትሆንም ትመስላቸው ይሆናል እንጂ ለሌላውም መስክ እንዲሁ ነው ፡፡

ባለህ ተሰጥኦ ላይ ስትማርበት ስታነብበት ስትመራመርበት ያኔ አንተ የሕይወትን ቁልፍ አገኘህ ማለት ነው የስኬታማ ሰዎች መነሻም መድረሻም ይህ ነጥብ ነው፡፡
እንደ ሀገር ተምረን መኪና ጠገንን እንጂ መኪና አልሠራንም ተምረን ስልክ እንጠግናለን እንጂ ስልክ አልፈጠርንም ለምን ?

ሁለት ነገር ይታየኛል እንደ ሀገር ትምህርት ቤቶቻችን መርኃችንም በተፈጥሮ ለታደልነው ጥበብ ትኩረት የማይሰጥና ሀገር በቀል እውቀትን ባለማሳደጋችን ነው

ራስህንም ሀገርህንም ለመለወጥ ዋናው ጉዳይ ከአምላክህ ምን ተቀበልኅ አንተስ ምን ብትሠራ ደስ ይልሃል? ምን የመሥራት ፍቅር አለህ? የሚለውን መመለስ ነው ::


ገንዘብ መሰብሰብ የሕይወትህ መስመር አስማሪ (ትልቅ ሕልምህ) መሆን በፍጹም የለበትም ገንዘብ በየትኛውም መስክ ብትሠማራ ተርፎ ሊትረፈረፍ ወይም ደግሞ እጅህ ላይ አልገባ እያለ ሊያሰቃይህ ይችላል

እንግዲያውስ ገንዘብ የመሰብሰብ ራዕይ ወይም ሕልም አይኑርህ እርሱ አንተ ውስጥ ያለውን ጸጋ በጥንካሬ እና በትጋት እንዴት እንደምትሸጠው የማወቅ እና ለመትደክመው ድካም የሚሰጥ በረከት ብቻ ነው የትኛውም ፊልድ በራሱ ገንዘብ የማምጣት የማስቀረትም አቅም የለውም ለምን?፡

የትኛውም ነገር ውስጥ ብትገባ ኃሳብህን ወይም እውቀትህን ወይም እቃህን እንዴት እንደምትሸጠው ካላወቅኽ በምንም ተአምር ገንዘብ አንተ ጋር አይሰበሰብም ይሁንና ቢመጣም አያድግም ቢያድግም ያለ ማቋረጥ አያድግም ተመልሶ ይጠፋል ሀብታም መሆንህ ደሀ ላለመሆን ዋስትና አይሆንህም ዋስትና የሚሆንህ እውቀትህ ፍላጎትህ ትጋትህና የፈጠርከው የግንኙነት መረብ ነው መዋኀድ ነው፡፡

ከተረዳኸኝ ገንዘብ ማግኘት አንድን ነገር እንዴት እንደምትሸጠው እና ትርፍ እንዴት እንደምታገኝበት የማወቅ ዱዳይ ነው እንጂ ነጋዴ ወይም ተቀጣሪ አካውንታትን ወይም ዶክተር የመሆን ጉዳይ አይደለም ሕልምህ ግን የተፈጠርክበት እና የምትሞትለት ጉዳይ ነው፡፡

እና ምን ላድረግ ?
እነዚህ ጥያቄዎች እራስህን ጠይቅ ደጋግመህ እየጻፍክ ፈልጋቸው
1. እኔ ማን ነኝ ?(ምንድነው ዝናባሌዬ ምን ላይ ሥሠራ ደስተኛ ነኝ ? ምን ምን ላይ ብሠራ ለሰዎች አንድ ነገር አበረክታለሁ….?)
2. እንደ ማን ነው መሆን የምፈልገው? (የምትወደውን ሰው አርአያ የምታደርገውን ሰው ባህርያት ጻፋቸው እና አንብባቸው ታዲያ የሠውየው የምትወዳቸው ባህርያት የአንተው እንደሆኑ በእርግጠኝነት ልነግርህ እወዳለው)
3. የት መድረስ ነው የምትፈልገው ?(በየትኛው የስኬት ማማ ላይ ራስህን ከወዲሁ ታየዋለህ..?)
ስለዚህ አንተ የተፈጠርኅበትን እውነተኛ ጉዳይ (ሕልምህን) ለይ አዎ ይህን ስልህ ብዙ ተቃዋሚ ሊኖርብህ ይችላል ብዙ ሰው ሊያጣጥልብህ ይችላል ልትሠማራ ያሰብኅበትን ጉዳይ ሊያናንቅብህ ይችላል ይህ ያንተ ጉዳይ መሆን የለበትም የአንተን ሕይወት የምትወስነው ራስህ ነህ በቅድሚያ ግን መወሰን የምትችልበት ቁመና ላይ መሆንህን አረጋግጥ፡፡


ሲጠቃለል መቼም እየሔድን አይደለም የት መሄድ እንዳለብን የምንወስነው ወስነን ነው ጉዞ የምንጀምረው አንተም እንዲሁ አድርግ ከልብህ የምትወደውን የምትፈልገውን ሁን እርሱም ላይ ከልብህ ሥራ ኃሳብህን እና እውቀትህን ወይም ፈጠራኅን እንዴት ወደ ገንዘብ እንደምትቀይረው ተማር ሁሌም ለሰው ልጆች እንዴት አዲስ ነገር ለመፍጠር እንደምትችል ተመራመር


እንደዚህ ሲሆን አንተ የትም መሔድ አይጠበቅብህም ሰው ራሱ ያለህበት ድረስ ፈልጎህ አፈላልጎህ ይመጣል የትኛው ይሻለኛል ካልኸኝ የተፈጠርኅበትን ጉዳይ ለይ በርሱ ላይ ተማር ተመራመር ፣ ሥራ ፣ ሽጥ ፣ለውጥ…አለቀ ያኔ ካንተ በላይ ስኬታማ አይኖርም ፡፡
መልካም የምርጫ ጊዜ
https://t.me/alazarsayehiwotmiker
ጥያቄና አስተያየት ለመስጠት https://t.me/Josi0921


አልዓዛር
297 viewsedited  12:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-07 11:51:38 እምቢ በል

በሕይወትህ የሚያዘናጉህን ነገር እምቢ ማለትን ያህል ውጤታማ የሚያደርግም ነገር የለም የአፕል ካምፓኒ መሥራች ስቲቭ ጆብ እንዲ ብሎ ነበር “እሺ ካልኩት ነገር ይልቅ እምቢ ያልኩት ይበልጣል ውጤታማ ያደረገኝ እሺ ያልኩት ሳይሆን እምቢ ያልኩት ነው..” ሲል ይነግረናል አሱ ለደረሰበት ትልቅ ደረጃ እሺ ሳይሆን እምቢ ነው ያገዘው፡፡

እምቢ ፡- ራሱ ምን ማለት ነው ?

እምቢ ማለት የማይጠቅምህን ላለማሰብ ፣ ላለመናገር ወይም ላለማድረግ ራስን መቆጣጠር ነው ፡፡

የተሳሳተ ኃሳባችን እና ልማዳችንን በየጊዜው ችግር ውስጥ ሊከተን ይችላል ታዲያ ይህን መቃወም እምቢ ማለት ትልቅ ችሎታ ነው ፡፡

ምን እምቢ ልበል ?
ለሕይወታችን የማይጠቅሙን ደግሞም እንደሚጎዳን በግልጽ የምናውቃቸውን ነገር ግን ደግሞ ሁሌ የምናደርጋቸው ብዙ ልማዶች አስተሳሰቦች አሉን እነዚህን እምቢ በማለት አደብ ማስገዛት ነው ትልቁ ጉዳይ፡
• የበዛ እንቅልፍ አልጋ ላይ ዝም ብሎ የመጋደም ስንፍና
• ማለዳ ያለመነሳት አባዜ
• ክፉ ክፉውን ብቻ የማሰብ ሟርት
• ቀጠሮ የማርፈድ ልማድ
• ሶሻል ሚዲያ ላይ ተጥዶ መዋል ማደር
• ከትዳር ውጪ የመማገጥ ፍላጎት
• ራስን በራስ የማርካት ጉስቁልና
• ለሰውነታችን ተስማሚ ያልሆነ አመጋገብ
• ጊዜን በከንቱ በጨዋታ የማሳለፍ ……ከብዙ በጥቂቱ

በሕይወታችን ብዙ እምቢ የምንላቸው ጉዳዮች ይኖራሉ እነሱን እምቢ ባልክ ቁጥር ኃይልህን ታድሳለህ እችላለው አሸንፋለው የሚለውን መንፈስ በራስህ ላይ ትፈጥራለህ ፡
ለኃጢአትም እንዲሁ ነው ቅዱስ ጳውሎስ “ደምን እስከማፍሰስ ከኃጢአት ጋር አልተጋደላችሁም …“ መጋደል እምቢ ከማለት ተከትሎ የሚመጣ ፈተና ነው ፡፡

እንዴት ነው እምቢ ማለት የሚቻለው ?

እምቢ ማለት የሚቻለው አንድን ነገር ያለውን ጉዳት በመረዳት ላይ ነው የጉዳዩን አስከፊነት አጥናው ምን ያህል እየጎዳህ እንደሆነ በደንብ አጢነው፡


ጥሩውን ሕይወት እወቀው ተመኘው ያን ያንተ እንዳይሆን እንቅፋት እርሱ እንደሆነ እወቅበት


በአቅምህ ጀምረው የምትችለውን ትንሽ ነገር ጀምር የምትችለውን ቀላል ነገር በቅድሚያ እምቢ በል “በጥቂቱ የታመነ በብዙ ይሾማል..” ይላል መጽሐፍ

እየመረረህ ቢሆን እዛው ላይ እምቢ እንዳልክ ቆይ ደስ ብሎህ መተው እንዳለብህ የምታስብ ከሆነ መቼም አትተወውም እምቢ ስትል ይደብርሃል ይከፋሃል ሌላ ችግር ውስጥ የገባህ ይመስልሃል ብቸኝነት ይሰማሃል የምታደርገው ግራ ይገባሃል…..ወ..ዘ..ተ ይሔ ሊሆን ግድ ይላል ይህ እምቢ ስትል የሚታይ የራስህ የመጀመሪያ ደረጃ ለውጥ ነው፡፡

አንተ ግን ራስህን በማስገደድ ወደፊት ቀጥል ይህ የሚሆንብህ ለጥቂት ጊዜ ነው የበለጠ ደስተኛ የሚያደርግህን ሕይወት እየፈጠርክ ስለሆነ መከራውን በደስታ ተቀበለው እምቢ በል አንተ እምቢ ስትል ሁሉም ነገር እሺ ይሆንልሃል፡፡

https://t.me/alazarsayehiwotmiker
መልካም ቀን ይሆንልን ዘንድ ይሁንልን
አልዓዛር
403 views08:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-26 13:24:26 እወነተኛ እውቀት


እውነተኛ እውቀት ማለት እውቀትን በኃሳብ ደረጃ በቃልም በተግባርም ማወቅ ነው ።

ይሕ ምን ማለት ነው ? የምታውቀው እውቀት በሦስቱም ደረጃዎች የማይረጋገጥ ከሆነ እመነኝ እውቀት ያለሕ ቢመስልህ እንኳን እውቀትሕ ምንም አይጠቅምም እንዴት....?


ስለ ሥራ ማወቅ እና ሥራን ማወቅ ይለያያል ስለ ሕክምና ማወቅ እና ሕክምናን ማወቅ የተለያዩ ነገሮች ናቸው ስለ መኪና ማወቅ ስለ ስልክ ወዘተ ማወቅ እውነተኛ ማወቅ አይደለም


ለምሳሌ እጃችን ላይ ስላለው ስልክ የምናውቅ ይመስለናል ግን እውቀታችን ተጠቃሚ እንጂ ሠሪ ስለማያደርገን እውቀታችን ቁንጽል ነው ማለት ነው ስለ ስልኩ ካሜራ እንጂ ሴቲንጉን አናውቀውም ሴቲንጉን እናወቀዎለን የሚሉ የስልክ ጠጋኞቻችን ሳይቀሩ ስልኩን መሥራት የሚያስችል እውቀት የላቸውም ግን ለምን?

እውነተኛ እውቀት ለግልም ለሀገርም እጅግ ጠቃሚ ነገር ነው ይሕ ሲኖረን ነው የፈጠራ ችሎታ የሚኖረን


ከዩኒቨርስቲ የሚወጡ ታዳጊዎች አብዛኞቹ የመቀጠር እንጂ ሥራ የመፍጠር እውቀት ይዘው ስለማይወጡ በየትኛውም መስክ የላቀ ወይም የፈጠራ ችሎታ አይገኝባቸውም


ደራሲና የስነ ምሕዳር ባለሙያ አለማየሁ ዎሴ አንድ ቀን ቃለ መጠይቅ ሲደረግለት እንዲሕ አለ ''ዩኒቨርስቲ ገብቼ የተማርኩት ትምሕርት አንድም ቀን ለሥራዬ አልጠቀመኝም '' ።

በርግጥም በዓለም ላይ ትልልቅ ተጽዕኖ ፈጣሪ የሆኑ ስኬታማ ሰዎች የቀለም ትምሕርቱን በአግባቡ የዘለቁ አይደሉም ነገር ግን ሁሉም ለኛ መምሕራኖቻችን ሁነው በመጽሐፋችን ታትመዎል ።
ለማያደርገን
ሞች አሉ ነገር ግን ሰው ለመታከም የሚፈልግባቸው ሃኪሞች በጣም ጥቂት ናቸው እነርሱም ከብዷቸው ለህክምና ወደ ውጪ የሚላኩት ታካሚዎች የትየለሌ ሆነዎል ሃኪም ጠፍቶ አይደለም አዎቂ ሀኪም ጠፍቶ እንጂ ስለ ሕክምናው የሚተማመንበት ሃኪም አጥቶ ነው ሕዝቡ የሚሰቃየው :

በሁሉም ዘርፍ ውስጥ smart and intelligent የሆኑ ሰዎችን ማግኘት ከባድ ነው አንድ ምርጥ አዎቂ ጥበበኛ ሰው ሲገኝ አቤት የሚሻማው መብዛቱ ይሕ የሁላችንም ትዝብት ይመስለኛል ።


ሀገር በቀል የሆኑ ትምሕርቶቻችንን መጣላችን ደግሞ ሁሌም የነጭ ተመራማሪዎች ባሪያ እንድንሆን ያስገድደናል


የእኛው አባቶች የሠሩትን የአክሱም እና ላሊበላ የድንጋይ ውቅር እኛ ለመጠገን እንኳን ሳይንሱ እውቀቱ ጠፍቶን ከጣለያን እና ከፈረንሳይ መጥተው መጠገናቸው የሚያሳየን እውቀት ምን እንደሆነ ነው ለኔ እውቀት በመማር ሳይሆን በምርምር የሚገኝ ነው እንድል ያደርገኛል ።


ለመንፈሳዊውም ሕይወት እንዲሁ ነው ስለ እግዚአብሔር ማወቅና እግዚአብሔርን ማወቅ በጣም የተለያዩ ነገሮች ናቸው እግዚአብሔርን የሚያውቁ ሰዎች በኃሳባቸው በቃላቸውና በሥራቸው እርሱን የሚመስሉት ናቸው ።


ለዚሕም ነው ቅዱስ ዩሐንስ አፈወርቅ '' የምታውቀውን መንፈሳዊ ሕግ በሥራ እስካልገለጥከው ድረስ አታውቀውም '' የሚለው


በቀን 7 የጸሎት ሰዓት አለ ብትል የጸሎት ጥቅም ምንነት ብትዘረዝር ነገር ግን ለ1 ሰከንድም ቢሆን ከልብ ካልጸለይክ ጸሎት ምን እንደሆነ አታውቅም ማለት ነው ።


ከተማርከውና ካነበብከው በላይ ጸሎት ስትጸልይ ብዙ ነገሮች ይገለጽልሃል ብዙ ምሥጢራትን ትረዳለህ ።

እንደኔ እንደኔ ምንም ነገር ከማድረግሕ በፊት ማወቅህ ልክ እና ጠቃሚ እንደሆነ እወቅ

ትክክለኛ የሆነ ለብዙ ሰው መትረፍ የሚችል እውቀት ባላቸው ሰዎች እቀናለው

አልዓዛር

ግንቦት 18/14
181 views10:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-18 14:10:34 እነዚህ የሕይወት መመሪያዎች ላንተ እጅግ አስፈላጊ እንደሆኑ አምናለው
++++++++++++++++++++++++++++++
1. ትልልቅ የሕይወት ውሳኔዎችን ተረጋግተህ ደጋግመህ አስብ ወስነህ ደግመህ እንዳትጸጸት
2. ራስህን የምትረዳበት መንገድ አስተካክል ጥንካሬህን ወይም ድካምህን በሰው ልኬት አትለካው አንተ ከራስህ ዕቅድ ጋር ተወዳደር
3. ችግርን አግዝፈህ አትይ ለችግር ቦታ አትስጥ መፍትሔው ላይ ብቻ ትኩረት ስጥ ቅን ኃሳቦችን ብቻ ተቀበል አሉታዊ ኃሳቦችን በጣም ችላ በል
4. ለሁሉም ሰው ጥሩ ለመሆን አትሞክር
5. የምታደርገውን መልካም ነገር መልሱን ከሰው አትጠብቅ ስለ እግዚአብሔር ስትል ብቻ አድርገው ብድራቱንም ከርሱ ጠብቅ
6. ደምቀው አምረው ከሚታዩ ነገር ግን ውስጣቸው መከራና ስቃይ ከሆኑ ጉዳዮች ራስህን ጠብቅ ናቀውም
7. ደስታን ውጪ ካሉ ነገሮች ለማግኘት አትሞክር ሲሳካልኝ ደስተኛ እሆናለው አትበል ደስተኛ ስትሆን ነው ሚሳካልህ
8. ዓላማ እና ዕቅድ ይኑርህ የት መድረስ ምን መሥራት እንደ ማን መሆን ነው የምትፈልገው ይህን መጀመሪያ ለራስህ መልስ የዕውር ጉዞ እንዳይሆንብህ
9. በጣም ስለሠራህ ሳይሆን በጣም ስላሰብክ ነው ስኬታማ የምትሆነው እነዚህን አስብ ሕልሜ ምንድነው? እንደማን መሆን ነው የምፈልገው? ምን መሥራት ነው የምፈልገው?
10. ነገ እሠራለው ዛሬ ልረፍ አትበል ዛሬ ሠርቼ ነገ አርፋለው በል

መልካም ቀን ይሁንልን
አልዓዛር ሱፋ
https://t.me/alazarsayehiwotmiker
https://t.me/alazarsayehiwotmiker
https://t.me/alazarsayehiwotmiker
527 views11:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-06 10:04:01 እንደ አጠቃቀምህ ነው
********************************
ስልክ ስገዛ ስልክ ለሚሸጥልኝ ሰው እንዲሕ አልኩት ባትሪው ምን ያሕል ይቆያል? ልጁም ባትሪው በጣም አሪፍ ባትሪ ነው ነገር ግን ደግሞ ዎናው አጠቃቀምሕ ነው አለኝ አጠቃቀሜ ምን ሆነ ? ያው አወራበታለው ፋይል እላላክበታለው ኢንተርኔት እጠቀምበታለው ሌላ ምንም አላደርግም አልኩት እርሱም እነዚሕ ምን ምን እንደምትጠቀም ነው የነገርከኝ ነገር ግን በምን ያሕል መጠን በምን ያሕል ጊዜ የምትጠቀመው የሚለው ነው የባትሪውን ሕይወት ሚወስነው ሲለኝ ደነገጥኩ ሕይወት ሲል ሕይወቴ ትዝ አለኝ ለምሳሌ እኔ ፈጣሪዬን የኔ ሕይወት ምን ያሕል ይቆያል ብለው እንደ አጠቃቀምሕ ነው እንደሚለኝ ተሰማኝ፡፡


ይህች ዓለም በውስጥህ ገነትም ሲኦልም የመሆን እድል አላት ለካ ዎናው አጠቃቀማችን ነው አንዳንድ ሰው ጊዜ እንደ ቁንጣ ሲያጥረው አንዳንዱ ደግሞ ቀኑ አልመሽ ሰዓቱ አልሔድ አለኝ እያለ ጊዜውን በምን እንደሚያጠፋው ሁሉ ያስባል ሕይወት እኛው እንደተጠቀምንበት ነው የሚሆነው እዚህ ምድር ላይ ለሁሉም የራሱ እድል አለው የሕይወት እና የመኖር ጥበብ ሲገባህ ከራስህ አልፈህ ለሌሎችም መኖር ማሰብ ትጀምራለህ ካልሆነ ደግሞ ለራስህም መኖር አትችልም ፡፡


አንዱ ከሌላው ወይም እርሱ ከኔ ለምን ተለየ ካልክ ሕይወት ላይ ባለህ አረዳድና ሕወትን የምትጠቀመምበት መንገድ ነው ዋናው ጉዳይ የአዕምሮ፤የጊዜ፤የገንዘብ እና የጉልበት አጠቃቀማችን ነው በኑሮ የመለያየታችን ምስጢር ፡፡


አዕምሮህን እንዴት እየጠተቀምከው ነው? ስለ አዕምሮ አሠራር ምን ታውቃለህ? አዕምሮህ ውስጥ ስላለው የኃሳብ ሞገድ ምን ትረዳለህ? ሕልምሕስ በአዕምሮህ ውስጥ አለ ወይ? ጊዜ ምንድነው ለአንተ የጊዜ አሠራሩ ምን ይመስላል? ጊዜህን ምን ላይ እያዋልከው ነው? ገንዘብ እንዴት ነው የሚመጣው? ገንዘብን እንዴት ነው የምታሠራው? ለምን ጉዳይ ትወጣለሕ ትወርዳለህ ኃይልህን እያባከንክለት ያለው ጉዳይ ምንድነው? መስዋዕትነት የምትከፍልለት ጉዳይስ እንዴት ታየዋለህ? እነዚህን ጥያቄ ለራስህ ስታቀርብ አንድ የሚገለጽልህ ነገር ይኖራል::
ሁሉም ነገር እንደ አጠቃቀምህ ነው ……
አልዓዛር
https://t.me/alazarsayehiwotmiker
https://t.me/alazarsayehiwotmiker
https://t.me/alazarsayehiwotmiker
805 viewsedited  07:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ