Get Mystery Box with random crypto!

ታላቅ የምስራች *** አል ፋሩቅ መልቲሚዲያ ፕሮዳክሽን ከተለመደው የኦዲዮቪዥዋል ስራዎቹ በተጨማሪ | አል-አሚን አል-ሀድራ ጀመዐ

ታላቅ የምስራች
***
አል ፋሩቅ መልቲሚዲያ ፕሮዳክሽን ከተለመደው የኦዲዮቪዥዋል ስራዎቹ በተጨማሪ የናንተን የውድ ሙስሊሞች ፍላጎት ለማርካት በህትመት ስራ ብቅ ብሏል። በመሆኑም መልቲ ሚዲያ ፕሮዳክሽናችን በእውቁ የኢስላማዊ ስነ ፅሁፍ ባለሙያ፣ ደራሲና ገጣሚ፣ የመድረክ ሰውና የበዙ ተሰጥዖዎች ባለቤት ሷሊሕ አስታጥቄ በግጥም ተዋዝቶ "መጅኑን ለይላ (እብዱ የፍቅር ሰማዕት) በሚል ርዕስ የተዘጋጀውን አዲስ መፅሀፍ አሳትሞ ወደ እናንተ ለማድረስ ጥቂት ቀናት ብቻ እንደቀሩን ያበስራል።

መፅሀፉ በዐለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ እውቅና ያገኘውንና ከአንድ ሺህ አመት በፊት በዐረቢያ ምድር በገሀድ ተከስቶ በላቀው የስነ ግጥም ውጤቶቹ ተውቦ እስከ ዛሬ ሳይከስም የዘለቀውን እንዲሁም በመላው ዐለም በነበሩ ታላላቅ ዑለማኦች ዘንድ እንደ ታላቅ የፍቅር ተምሳሌትነትና የነብዩ ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም ፍቅር መመሰያ ተደርጎ ሲነገርለት የኖረውን የመጅኑን ለይላ (የለይላው እብድ) ወይም በትክክለኛ ስሙ የቀይስ ኢብኑል ሙለውሕን ጥልቅና ድንቅ የፍቅርና የናፍቆት ታሪክ በላቀ የስነ ፅሁፍ ርቃቄና አቀራረብ በኢስላማዊ አደብ ይተርካል።

ይህን ዘመን አይሽሬ መፅሀፍ ለውዱ ህዝባችን ስናበረክትም በታላቅ ደስታ ነው።