Get Mystery Box with random crypto!

አል-አሚን አል-ሀድራ ጀመዐ

የቴሌግራም ቻናል አርማ alaminalhadrajemea — አል-አሚን አል-ሀድራ ጀመዐ
የቴሌግራም ቻናል አርማ alaminalhadrajemea — አል-አሚን አል-ሀድራ ጀመዐ
የሰርጥ አድራሻ: @alaminalhadrajemea
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 519
የሰርጥ መግለጫ

አሰላሙአለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ ውድ የቻናላችን ተከታዮች በዚህ ቻናል
💚የተለያዩ የሀድራ መንዙማዎች
💛የጀመዐውን ስራዎች
🧡የተለያዩ አዳብያቶች
♥️ሲራ እና መንዙማዎች
❤️የኸይር ስራ ትሩፍት እና ሀዲሶች ምታገኙበት ቻናል ነው።
ጀመዐው በተጨማሪ ለሰርግ ለኒካህ ለተለያዩ ፕሮግራሞች የሀድራ አገልግሎት እንሰጣለን።
0933537268
0919170774 መደወል ትችላላችሁ።

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-11 21:19:34
53 viewsAbdure Al @min , 18:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 21:19:34
53 viewsAbdure Al @min , 18:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 21:19:34
ታላቅ የምስራች
***
አል ፋሩቅ መልቲሚዲያ ፕሮዳክሽን ከተለመደው የኦዲዮቪዥዋል ስራዎቹ በተጨማሪ የናንተን የውድ ሙስሊሞች ፍላጎት ለማርካት በህትመት ስራ ብቅ ብሏል። በመሆኑም መልቲ ሚዲያ ፕሮዳክሽናችን በእውቁ የኢስላማዊ ስነ ፅሁፍ ባለሙያ፣ ደራሲና ገጣሚ፣ የመድረክ ሰውና የበዙ ተሰጥዖዎች ባለቤት ሷሊሕ አስታጥቄ በግጥም ተዋዝቶ "መጅኑን ለይላ (እብዱ የፍቅር ሰማዕት) በሚል ርዕስ የተዘጋጀውን አዲስ መፅሀፍ አሳትሞ ወደ እናንተ ለማድረስ ጥቂት ቀናት ብቻ እንደቀሩን ያበስራል።

መፅሀፉ በዐለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ እውቅና ያገኘውንና ከአንድ ሺህ አመት በፊት በዐረቢያ ምድር በገሀድ ተከስቶ በላቀው የስነ ግጥም ውጤቶቹ ተውቦ እስከ ዛሬ ሳይከስም የዘለቀውን እንዲሁም በመላው ዐለም በነበሩ ታላላቅ ዑለማኦች ዘንድ እንደ ታላቅ የፍቅር ተምሳሌትነትና የነብዩ ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም ፍቅር መመሰያ ተደርጎ ሲነገርለት የኖረውን የመጅኑን ለይላ (የለይላው እብድ) ወይም በትክክለኛ ስሙ የቀይስ ኢብኑል ሙለውሕን ጥልቅና ድንቅ የፍቅርና የናፍቆት ታሪክ በላቀ የስነ ፅሁፍ ርቃቄና አቀራረብ በኢስላማዊ አደብ ይተርካል።

ይህን ዘመን አይሽሬ መፅሀፍ ለውዱ ህዝባችን ስናበረክትም በታላቅ ደስታ ነው።
48 viewsAbdure Al @min , 18:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 06:18:14 #ዐደደማ
#ተለቀቀ ለሌሎችም እንዲደርስ ላይክ እንዲሁም ሸር ያድርጉ


45 viewsІбрагім , 03:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-29 06:26:57 الحمد لله رب العالمين والصلام والسلام على سيدنا محمد المعصوم من الكفر وعلى آله وصحبه أجمعين
በዚህ በአኺረ ዘማን በጣም አስደንጋጭና አሳፋሪ ንግግሮች ጥራዝ ነጠቅ ከሆኑ ተራ ግለሰቦች እየሰማን ነው!!

ቀደም ሲል ነብያቾችን በማዋረድና በማውገዝ የምንሰማቸው ከነበሩ ንግግሮች ውስጥ ምንጫቸውና መነሻቸው የረሱል ጠላቶችና ሙስሊም ያልሆኑ ግለሰቦች ሆነው እናገኛቸዋለን አሁን ደግሞ ሙስሊም ነኝ ከሚል አንድ #አህመዲን_ጀበል የሚባል ግለሰብ ታላቁ ነብይና የአንቢያኦች ሁሉ የበላይ የሆኑትን ሰይዳችንን ዐለይሒ ሶላቱ ወሰላም #ሰለምቴ ነበሩ ሲል ለጆሮ ሰቅጣጭ ንግግርን ለተከታዮቹ አድርሷል!!!

የአህመዲን ጀበል ንግግር ላዳመጠው ሰው ከመሰረቱ ሊጠይቅ የሚገባው ሰለምቴነት ሲባል ምንድን ነው የሚለውን ነው!!

#ሰለምቴ ሲባል ቃሉ ራሱ የሚያሳየው እስልምና የሚባል ሐይማኖት ኖሮ ከክህደት ወደነበረው የኢስላም እምነት እንደተመለሱ ነው ይሄ ዘግናኝ ንግግር ከአንድ ሙስሊም ነኝ ከሚል ሰው የሚነገር ንግግር አልነበረም!!


ነብያችን በነበሩበት ወቅት ከ40 አመታቸው በፊት ወሕይ አይውረድላቸው እንጂ በነብይነት መሾማቸው በይፋ አይታወጂ እንጂ በዘመናቸው ነብይነታቸው ለአረብ ሙሽሪኮችና ለአለም በይፋ ከመታወጁ በፊት አሏህን በብቸኝነት የሚገዙ ሐኒፊያዎች(የአባታችም ነብዩሏህ ኢብራሒም) መንገድ የተከተሉ ሰዎች ነበሩ ለአብነትም
#ዘይድ_ኢብኑ_ዐምር_ኢብኒ_ኑፈይል ከ ዓስሩ በጀነት የተመሰከረላቸው አንዱ የሆኑት #የሰዒድ_ኢብኑ_ዘይድ አባት የሆነና ነብያችንም ዘይን ኢብኑ ዐምር ኢብኑ ኑፈይልን ጀነት ገብቼ ሁለት ደረጃዎቹን አየሁለት ብለው የመሰከሩለት አይነት ሰው ነበር፡፡

አህመዲን በንግግሩ ግን ከዘይድ ኢብኑ ዐምር ኢብኒ ኑፈይልና መሰል ሰዎችም #የወረዱ አድርጎ የሚያስላቸውን ንግግር መናገሩ ንግግሩን አደገኛ ያደርገዋል!!

ጂብሪል ዐለይሒ ሰላም #ወሕይ ይዞ ሲወርድ ወደ ኢስላም ተመለስ አላላቸውም ይልቁንም ሱረቱል ቀለም ውስጥ ያሉትን 5 አያቶች አንብብ እያለ ነበር የጎተጎታቸው


#ወሕይ ከመውረዱ በፊትም ሶሂሁል ቡኻሪ የመጀመሪያው ክፍል ስለ ወህይ አወራረድ የሚገልጸው ሐዲስ ላይ
فيتحنث فيه الليالي ذوات العدد
ወህይ ከመውረዱ በፊት ጋሩ ሒራእ (የሒራእ ዋሻ) ውስጥ በቁጥር ሊቆጠሩ የሚችሉ ለሊቶችን #በኢባዳ ያሳልፉ ነበር ሲሉ አሏህን #እንደሚገዙ የሚያስገነዝብ ንግግር ሰፍሮ እናገኛለን!!

አህመዲን ጀበል ከዒልምና ከመረዳት ግንዛቤ ድክመት አንጻር ጠማማ ፊርቃዎች የሚያምኑትን #እምነት መግለጹ አሳፋሪና የነብያችንን ክብር ያልጠበቀ ለመሆኑ አንድ ዓቂል ሰው የሚረዳው ጉዳይ ነው!!


የአህመዲን ጀበል ንግግር በኡለማዎች ሚዛን
============================
ከዓራቱ መዛሒቦች አደራጂ አንዱና አንጋፋው ታላቁ የሰለፍ አሊም #አቡ_ሐኒፋ ፊቅሑል አክበር በሚባለው ኪታባቸው ላይ ነብያችን በኩፍር እንደማይገለጹ
ይሄን አስፍረዋል

(( ومحمد (صلى الله عليه وسلم) حبيبه وعبده ورسوله ونبيه وصفيه ونقيه لم يعبد الصنم #ولم_يشرك_بالله عز وجل طرفة عين ولم يرتكب صغيرة ولا كبير قط))
ትርጉም
[[ ሙሐመድ(ሶለሏሁ ዓለይሒ ወሰለም)
የአሏህ ምርጥ ወዳጂ ባሪያው መልዕክተኛው ነብዩ የመረጣቸውና ከሁሉ ንጹህና ጽዱ ሲሆኑ ጣኦት አልተገዙም በፍጹም በአሏህም ላይ #አላጋሩም ትንሽም ሆነ ትልቅ ወንጀል በጭራሽ አልሰሩም]]

قال الإمام النووي «اتفقوا أن النبي صلى الله عليه وسلم لم يعبد صنماً قط، والأنبياء قبل النبوة معصومون من الكفر))
مصدر:(روضة الطالبين: 3/498)
ኢማሙ ነወዊ ደግሞ
((ዑለማዎች በሙሉ ነብያችን ዓለይሒ ሶላቱ ወሰላም በፍጹም ጣኦት አልተገዙም ነብያቶች ለነብይነት ከመታጨታቸው በፊት ከኩፍር የተጠበቁ ናቸው))
قال ابو حنيفة فى الفقه الاكبر
((والانبياء عليهم السلام منزهون عن الصغائر والكبائر والكفر))
قال ملا علي القارئ شارحا قول ابي حنيفة
(والكفر خص لانه أكبر الكبائر ))
ሙላ ዐሊዩኒል ቃሪእ የአቡሐኒፋን ንግግርን ሲተረጉሙ አንቢያኦች ሑሉ ከትንንሽ ከትልልቅ ወንጀሎችና ከኩፍር የጸዱ ናቸው የሚለውን ኩፍር ተለይቶ የተጠቀሰው ከትልልቅ ወንጀሎች ሑሉ ትልቅ ወንጀል በመሆኑ ነው ብለዋል))

ነብያችን ሲገልጹ ታላቁ ሊቅ አልመቅሪዚ
فلم يرغب لهم في صنم قط، ولا شهد معهم عيدا، ولم يسمع منه كذب قط، ...... وكان يواصل الأسبوع صوما ويقول: إني أظل عند #ربي يطعمني ويسقيني، وكان يبكي حتى يسمع لصدره أزيز كأزيز المرجل،
በፍጹም ጣኦት ለማምለክ #አልፈለጉም (ፍላጎት አላሳዩም) ከነርሱም(ከጣኦታውያን) ጋር ክብረ ባዕላቸው ላይ #አልታደሙም ውሽት የሚባል ነገር (ከአንደበታቸው) አልተሰማም ሳምንቱን በተከታታይ በጾም ያሳልፉ ነበር እኔ #ፈጣሪየ ጋር እቆያለሁ እሱም ይመግበኛል ያጠጣኛልም ይሉ ነበር
ያለቅሱም ነበር ልክ እሳት ላይ የተጣደ ድስት እንደሚንፈቀፈቀው ሁሉ (የለቅሷቸው ብርታት) ከደረታቸው የመንፈቅፈቅ ድምጽ ይሰማ ነበር))
#ምንጭ፥አልመቅሪዚ ከዒምታዑል አስማዕ ኪታብ ቅጽ 4 ገጽ 212
ጌታየ ያሉት አሏህን ነበር የሚጾሙትም ለአሏህ ነበር፡፡


ይህ የአል መቅሪዚ ንግግር በአህመዲንና መሰሎቹ መጤና ፈሊጥ በሆነው ተውሒድን የመከፋፈል እምነትና ግንዛቤያቸው እንኳን ተውሒዱል ኡሉሒያ ላይ እንከን አላቸው ብሎ ለማውራት የማያስደፍር የሆነ መረጃ ነው !!

ይህን የምንለው አህመዲን ትንሽ እንኳን ቢረዳ ለማለት እንጂ ተውሒድን የመክፈል መሰረት አለው ማለታችን አይደለም!!


በዚህ የዑለማዎች ንግግር ነብያችን ማሻረክ የሚባልና ክህደት ባጠቃላይ እንዳላጋጠማቸው ሙስሊሞች ስምምነታቸውን ጠቅሰዋል በመሆኑም #አህመዲን_ጀበል የተናገረው ንግግር ፍጹም የነብያችንን ክብር የጠበቀ ስላልሆነ ከሚከተለውም ሽይኹ ከኢብኑ ተይሚያ ንግግር የወጣ ለመሆኑ [[አሳሪመል መስሉል አላ ሻቲሚ-ረሱል ]] የሚለውን ኪታብ ጭብጥ ተገንዝቦ ጭምር ሙስሊሞች ባጠቃላይ ለነብያችን ክብር ዘብ በመቆም አህመዲን ጀበል የሚባለውን ግለሰብ ከወደቀበት አሳፋሪና ዘግናኝ ንግግር ህዝበ ሙስሊሙን ይቅርታ እንዲጠይቅና ከንግግሩ በሽሪዐው ህግ መሰረት አስተማሪና ተገቢ ሁክም ተስጥቶበት እንዲመለስ እናሳስባለን!!

በመሆኑም ሙስሊሙ ማህበረሰብ በኢስላም ሽፋን ተጠልለው እንደ አህመዲን ጀበልና መሰል የነብያችንን ክብር የሚያረክሱ ንግግሮች ለሚናገር ማንኛውንም ቡድንና ግለሰቦች ጭምር እንደማይታገስና በነብያችን ክብር እንደማይደራደር ለማሳወቅ እንወዳለን
!!

#አሏሁ_አክበር

@finding_hubullah
234 views|乃尺ㄖ 𝐀𝐥-𝐀𝐦𝐢𝐧 , 03:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-29 06:26:57 ሰይዳችንን ﷺ ሰለምቴ ብሎ መግለፅ በሸሪዐው እንደተከለከለ ዑለማዎች የተናገሩት ብይን

ዑስታዝ ሸምሰዲን ሀምዛ

t.me/finding_hubullah
134 views|乃尺ㄖ 𝐀𝐥-𝐀𝐦𝐢𝐧 , 03:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-29 06:26:57
140 views|乃尺ㄖ 𝐀𝐥-𝐀𝐦𝐢𝐧 , 03:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-16 08:09:37
208 views|乃尺ㄖ 𝐀𝐥-𝐀𝐦𝐢𝐧 , 05:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-14 16:12:08
አንድአንድ ግዜ ሀቅ ሲመጣ በፍጥነት ነው:: የኔ ሙፍቲህ እንደማያደርጉትኮ ሁልህም ታውቃለህ ምክንያቱም በተርቢያ ነው ያደጉት

ይሄን ቪዲዮ Share ማድረግ ግዴታችን ነው ሁሉም ሊያዳምጠው ይገባል

#ፀሀይን_መርጫለሁ

በአሏህ አማና ሼር አድርጉ እውነታውን ሁሉም ሙስሊም ይወቀው።
JOIN
https://t.me/finding_hubullah
156 viewsAbdure Al @min , 13:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-10 22:04:12 የነጃሳ ትርጉምና አይነቶቹ ነጃሳ ማለት ሸሪዓው እንድንርቀው ያዘዘን ማንኛው ፀያፍ አካል ሲሆን ነጃሳ ሁለት አይነት ነው:: 1. ግኡዝ አካላዊ ነጃሳ፡- እንዲህ አይነቱን ነጃሳ ነገሩ ራሱ ነጃሳ በመሆኑ ማፅዳት አይቻልም፡፡ ለምሳሌ ደም፣ ሽንትና የመሳሰሉት ማለት ነው:: 2. አካል ላይ በማረፍ ሶላትን የሚከለክል ነጃሳ፦ እዚኛው ውስጥ በዉዱእ የሚወገድ ትንሹ ሀደስና በትጥበት የሚወገድ ትልቁ ሀደስ ይካተታል:: ነጃሳን የምናስወግድበት ዋናው አስወጋጅ ውሃ ነው፡፡ ውሃ እያለ በሌላ ነገር ማፅዳት አይቻልም፡፡ አላህ አንዲህ ይላል፡- ‹‹ውሃውንም በእርሱ ሊያጠራችሁ… በእናንተ ላይ ከሰማይ ባወረደላችሁ ጊዜ (አስታውሱ)፡፡›› (አል አንፋል 11) ነጃሳ በሶስት ይከፈላል፦ ከባድ ነጃሳ፡- ይህ ውሻና የእሱ ተዋላጅ ነው፡፡ ቀላል ነጃሳ፡- ምግብ ያልጀመረ የወንድ ህፃን ልጅ ሽንት ነው፡፡ መካከለኛ ነጃሳ፡- የተቀሩ ነጃሳዎች በአጠቃላይ ለምሳሌ ሽንት፣ ሰገራና በክት እዚህ ውስጥ ይካተታሉ፡፡


https://t.me/AlAminAlHadraJemea
499 viewsAbdure Al @min , 19:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ