Get Mystery Box with random crypto!

የነጃሳ ትርጉምና አይነቶቹ ነጃሳ ማለት ሸሪዓው እንድንርቀው ያዘዘን ማንኛው ፀያፍ አካል ሲሆን ነጃ | አል-አሚን አል-ሀድራ ጀመዐ

የነጃሳ ትርጉምና አይነቶቹ ነጃሳ ማለት ሸሪዓው እንድንርቀው ያዘዘን ማንኛው ፀያፍ አካል ሲሆን ነጃሳ ሁለት አይነት ነው:: 1. ግኡዝ አካላዊ ነጃሳ፡- እንዲህ አይነቱን ነጃሳ ነገሩ ራሱ ነጃሳ በመሆኑ ማፅዳት አይቻልም፡፡ ለምሳሌ ደም፣ ሽንትና የመሳሰሉት ማለት ነው:: 2. አካል ላይ በማረፍ ሶላትን የሚከለክል ነጃሳ፦ እዚኛው ውስጥ በዉዱእ የሚወገድ ትንሹ ሀደስና በትጥበት የሚወገድ ትልቁ ሀደስ ይካተታል:: ነጃሳን የምናስወግድበት ዋናው አስወጋጅ ውሃ ነው፡፡ ውሃ እያለ በሌላ ነገር ማፅዳት አይቻልም፡፡ አላህ አንዲህ ይላል፡- ‹‹ውሃውንም በእርሱ ሊያጠራችሁ… በእናንተ ላይ ከሰማይ ባወረደላችሁ ጊዜ (አስታውሱ)፡፡›› (አል አንፋል 11) ነጃሳ በሶስት ይከፈላል፦ ከባድ ነጃሳ፡- ይህ ውሻና የእሱ ተዋላጅ ነው፡፡ ቀላል ነጃሳ፡- ምግብ ያልጀመረ የወንድ ህፃን ልጅ ሽንት ነው፡፡ መካከለኛ ነጃሳ፡- የተቀሩ ነጃሳዎች በአጠቃላይ ለምሳሌ ሽንት፣ ሰገራና በክት እዚህ ውስጥ ይካተታሉ፡፡


https://t.me/AlAminAlHadraJemea