Get Mystery Box with random crypto!

መውሊዱን ናፋቂ… 6 ኢብን አባስ ረዲየላሁ አንሁ ባወሩት ሀዲስ ሀቢቢ አለይሂ ሰላት ወሰላም | አል_በሳዕ

መውሊዱን ናፋቂ… 6

ኢብን አባስ ረዲየላሁ አንሁ ባወሩት ሀዲስ ሀቢቢ አለይሂ ሰላት ወሰላም እንዲህ ብለዋል « አሏህ ፍጥረቱን በሙሉ የቀኝ ጎዶችና የግራ ጎዶች ብሎ በሁለት ከፈለው። እኔ ከቀኝ ጎዶች ነኝ። ከነሡም ምርጡ እኔ ነኝ የቀኝ ጎዶችን እንደገና በ3 ከፈላቸው። እኔ ወሳቢቁነ ሳቢቁን ከተባሉት ነኝ። ከነዚህም ምርጡ እኔ ነኝ ከአደም ልጆች በሙሉ አሏህን በጣም ምፈራው እኔ ነኝ የእኔ የትውልድ ቦታና የዘር ሀረጌ ከሁሉም ይበልጣል ይህ እውነታው ነው እንጂ።»
በሌላ ሀዲስ « አሏህ ከአደም ልጆች የኢብራሂም አለይሂ ሰላም ዘር መረጠ ከኢብራሂም አለይሂ ሰላም ዘር የእስማኢልን አለይሂ ሰላም ዘር መረጠ ከእስማኢል አለይሂ ሰላም ዘር በኒ ኪናናን መረጠ ከበኒ ኪናና ቁረይሽን መረጠ። ከቁረይሽ በኒ ሀሽምን መረጠ እኔን ከበኒ ሀሽም መረጠ። »
አቡ ሠላማና አቡሁረይራ ረዲየላሁ አጅመዒን ባወሩት ሀዲስ «ያረሡለሏህ አለይሂ ሰላት ወሰላም መቸ ነው ነብይነት የወጀበልዎት ተብለው ተጠየቁ» እርሳቸውም « አደም ገና በሩህና በጀሠድ መሃል እያለ እኔ ነብይ ነበርኩ አሉ። »

ሁሉንም ሀዲሶች ኪታቡ ሺፋዕ ቃዲ ኢያድ
ላይ በስፋት ይገኛሉ ይህ ውብ የሀቢቢ ታሪክ
ለመውሊዱ እንድታነቡት ጋብዣቹሀለሁ።"

#ምርጥ ቂሳ

#ትንሹ ነቢል ሙከረም

شريف نبيل شيخ مكرم
❀በቴሌግራም
❀ይ ላ ሉን!


@al_besaa
@al_besaa
@al_besaa