Get Mystery Box with random crypto!

አል_በሳዕ

የቴሌግራም ቻናል አርማ al_besaa — አል_በሳዕ
የቴሌግራም ቻናል አርማ al_besaa — አል_በሳዕ
የሰርጥ አድራሻ: @al_besaa
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 173

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-10-06 04:04:00 መውሊዱን ናፋቂ…3

አባታችን አደም ዐለይሂ ሰላም ና እናታችን ሀዋ አለይሂ ሰላም ሁሌም ሚወልዱት መንታ መንታ ነበር። ይህ ባህል ግን ሽይዝ አለይሂ ሰላም የተባለው ልጃቸው ሲወለድ አልሆነም። ሽይዝ አለይሂ ሰላም ብቻውን የተወለደ ብቸኛ ልጃቸው ነው። ነብይም የሆነ ብቸኛ ልጃቸው ነው። አንድ ቀን አባታችን አደም ዐለይሂ ሰላም ለሽይዝ አለይሂ ሰላም እንዲህ አሉት « ከእኔ ጀርባ ኑር ነበር። አንተ ስትወለድ ወደ አንተ ተላልፎል። ስለዚህ ሀላል እንጂ ሀራም እንዳትበላ። ጡሃራ ማህፀን ላይ እንጂ ዘርህን የትም እንዳታፈስ። » ሺዝም አለይሂ ሰላም እንዲህ ሲል ጠየቀ? ኑር ምንድነው ? አባታችን አደምም ዐለይሂ ሰላም « የሙሀመድ አለይሂ ሰላት ወሰላም ኑር ነው። ከዘሬ በአንተ አርጎ አልፎ የሚሄድ ነው። » ሙሀመድን አለይሂ ሰላት ወሰላም እንዴት ልታውቀው ቻልክ አለ ሽይዝ አላይሂ ሰላም ።አባታችን አደምም ዐለይሂ ሰላም « በጀነት ስንቀሳቀስ የትም ቦታ ስሙ ከአሏህ ስም ጋ ተቆራኝቶ ተቀምጧል። ጀነት ላይ ከዛፉም ከመግቢያውም ስሙ በክብር ተፅፎል። የሁረል አይኖች ግንባር በእሡ ስም ያብለቀልቃል። በአጠቃላይ ጀነት ላይ ስሙ ያልተፃፈበት ቦታ የለም። ያኔ ነው ያወቁት። አሉ አባታችን አደም ዐለይሂ ሰላም። » ሽይዝ አለይሂ ሰላም እሽታውን ሠጠ።

"ኽሶኢሡ ነብዮል ኻቲም __
በሸይኽ ፈውዛ ሙሀመድ አቡ የዚድ
በተዘጋጀ ድንቅ የሀቢቢ ታሪክ ይህ ታሪክ በሠፊው ቀርቦል።"

#ምርጥ ቂሳ

#ትንሹ ነቢል ሙከረም

شريف نبيل مكرم
❀በቴሌግራም
❀ይ ላ ሉን!


@al_besaa
@al_besaa
@al_besaa
18 viewsشريف نبيل مكرم, 01:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-06 03:49:01 መውሊዱን ናፋቂ…4

ሁሉም ሡሃቦች ረሡሉን አለይሂ ሰላት ወሰላም በማላቅና በማክበር የታነፁ ነበሩ ።
ዑመር ረዲየላሁ አንሁ እንዲህ ይሉናል « ከእኔ ዘንድ እንደ ረሡል አለይሂ ሰላት ወሰላም ተወዳጅ የለም። በሙሉ አይኔ አይቻቸው አላውቅ።በአሏህ ይሁንብኝ የረሡሉን ( ሠአወ) መልክ እንዴት እንደሆነ ብጠየቅ መግለፅ አልችልም።በትክክል አላውቀውም።»
የሆነ ጊዜ ሙሃጅሮችና አንሶሮች መስጊዱን ሞልተውታል። ሞቀ ያለ አጀንዳም እያወሩ ነበር። በድንገት ሀቢቢ አለይሂ ሰላት ወሰላም ገቡ። መስጊዱ በቅፅበት ፀጥ ረጭ አለ። ሁሉም አንገቱን ደፋ። አቡበከርና ዑመር ረዲየላሁ አንሁሙ ትንሽ ከአንገታቸው ቀና አሉ ።ከሀቢቢ አለይሂ ሰላት ወሰላም ጋርም አይን ለአይን ተጠጋጠሙ። በምልክት ቋንቋም የሡሃቦቹ ሁኔታ ገርሞቸው ፈገግ አሉ።
ሀቢቢ አልይሂ ሰላት ወሰላም ካለፉ በሆላም ይህ ክብር በታዕቢዮች ቀጥሎል። የፈቂሆች ቁንጮና የእነ ኢማሙ አቡ ሀኒፋ ሸህ ጃዕፈር ኢብን ሶዲቅ ያለ ውዱዕ ሀዲስ አይነኩም ነበር። ረሡሉ አልይሂ ሰላት ወሰላም ሲወሡ ይተክዙም ነበር። ልባቸው እንደሚንቀጠቀጥም ተናግረዋል።
ዙኻይሪይ ረዲየላሁ አንሁ ተጫዋችና ቀለል ያለ ባህሪ የነበራቸው ታዕብይ ናቸው። ረሡሉ አለይሂ ሰላት ወሰላም ሲወሡ ግን ባህሪያቸው ይቀየራል ። አይናቸው እምባ ይቆጥራል። አፋቸው ይንተባተባል። ቁሞ ሀዲስ ሚያነብ ሠው ሲያዮ ይገረማሉ _ አደብ ማጣት ነው ብለው ያስቡ ነበር።

#ምርጥ ቂሳ

#ትንሹ ነቢል ሙከረም

شريف نبيل مكرم
❀በቴሌግራም
❀ይ ላ ሉን!


@al_besaa
@al_besaa
@al_besaa
13 viewsشريف نبيل مكرم, 00:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-06 03:48:53 መውሊዱን ናፋቂ…5

አንድ በደውይ በስራው ተስፋ ይቆርጥና ምህረት ባገኝ ብሎ ወደ ረሡሉሏህ አለይሂ ሰላት ወሰላም ቀብር ይሄዳል። እንዲህም ሲል አሏህን ይቅርታ ጠየቀ።
«ያ አሏህ ይህ ቀብር የአንተ ወዳጅ ነው። እኔ ባርያህ ነኝ ።ሸይጧን ጠላትህ ነው። ይቅር ካልከኝ ይህ ወዳጅህ ይደሠታል። ባርያህ ስኬታማ ይሆናል ጠላትህ ይናደዳል። ካልመርከኝ ግን ወዳጅህ ያዝናል። ባርያህ ይከስራል። ጠላትህ ይደሠታል።
ያ አሏህ በእኛ በአረቦች ባህል ቸር የሆነ ሠው ሲሞት ቀብሩ ላይ ባርያዎቹ ነፃ ይወጣሉ። ይህ ከፊት ለፊቴ ያለው ቀብር ደግሞ የሀቢቢ አለይሂ ሰላት ወሰላም ነው ከቸሮች ሁሉ የበለጠ ቸር ነው ። ስለዚህ ከእሡ ቀብር የቆምኩትን ባርያህን ነፃ አውጣኝ።»
ይህን ዱአ ብሎ እንደጨረሰ ከሠማይ እንዲህ የሚል የኻቲፍ ድምፅ ሠማ « በወዳጀ ስለጠየቅኝ ምሬሃለሁ። አጠያየቅህን ስላሳመርክም ኒዕማን ጨምሪሃለሁ። »

#ምርጥ ቂሳ

#ትንሹ ነቢል ሙከረም

شريف نبيل مكرم
❀በቴሌግራም
❀ይ ላ ሉን!


@al_besaa
@al_besaa
@al_besaa
13 viewsشريف نبيل مكرم, 00:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-06 03:48:40 መውሊዱን ናፋቂ… 6

ኢብን አባስ ረዲየላሁ አንሁ ባወሩት ሀዲስ ሀቢቢ አለይሂ ሰላት ወሰላም እንዲህ ብለዋል « አሏህ ፍጥረቱን በሙሉ የቀኝ ጎዶችና የግራ ጎዶች ብሎ በሁለት ከፈለው። እኔ ከቀኝ ጎዶች ነኝ። ከነሡም ምርጡ እኔ ነኝ የቀኝ ጎዶችን እንደገና በ3 ከፈላቸው። እኔ ወሳቢቁነ ሳቢቁን ከተባሉት ነኝ። ከነዚህም ምርጡ እኔ ነኝ ከአደም ልጆች በሙሉ አሏህን በጣም ምፈራው እኔ ነኝ የእኔ የትውልድ ቦታና የዘር ሀረጌ ከሁሉም ይበልጣል ይህ እውነታው ነው እንጂ።»
በሌላ ሀዲስ « አሏህ ከአደም ልጆች የኢብራሂም አለይሂ ሰላም ዘር መረጠ ከኢብራሂም አለይሂ ሰላም ዘር የእስማኢልን አለይሂ ሰላም ዘር መረጠ ከእስማኢል አለይሂ ሰላም ዘር በኒ ኪናናን መረጠ ከበኒ ኪናና ቁረይሽን መረጠ። ከቁረይሽ በኒ ሀሽምን መረጠ እኔን ከበኒ ሀሽም መረጠ። »
አቡ ሠላማና አቡሁረይራ ረዲየላሁ አጅመዒን ባወሩት ሀዲስ «ያረሡለሏህ አለይሂ ሰላት ወሰላም መቸ ነው ነብይነት የወጀበልዎት ተብለው ተጠየቁ» እርሳቸውም « አደም ገና በሩህና በጀሠድ መሃል እያለ እኔ ነብይ ነበርኩ አሉ። »

ሁሉንም ሀዲሶች ኪታቡ ሺፋዕ ቃዲ ኢያድ
ላይ በስፋት ይገኛሉ ይህ ውብ የሀቢቢ ታሪክ
ለመውሊዱ እንድታነቡት ጋብዣቹሀለሁ።"

#ምርጥ ቂሳ

#ትንሹ ነቢል ሙከረም

شريف نبيل شيخ مكرم
❀በቴሌግራም
❀ይ ላ ሉን!


@al_besaa
@al_besaa
@al_besaa
12 viewsشريف نبيل مكرم, 00:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-06 03:48:19 መውሊዱን ናፋቂ… 7

ኢማሙ ረባኒ አብዱልወሃብ ከሠይድ አሊ ኽዋስ እንዲህ ሠማሁ ይሉናል « አሏህን የሆነ ሀጃ መጠየቅ ከፈለጋቹሁ በሙሀመድ አለይሂ ሰላት ወሰላም ጠይቁት። ያ አሏህ ቢሀቂ ሙሀመድ አለይሂ ሰላት ወሰላም ይህን ይህን ሀጃየን ፈፅምልኝ በሉት። ይህን ስትፈፅሙ ለዚህ የተወከለ መላኢካ ለሀቢቢ አለይሂ ሰላት ወሰላም እንትና ሚባል ባሪያ በአንቱ ተወስሎ አሏህን ሀጃ ጠይቆል ይላቸዋል። ሀቢቢም አለይሂ ሰላት ወሰላም ለዚህ ባሪያ ዱአ ያረጉለታል። ሀቢቢ አለይሂ ሰላት ወሰላም ዱአ ያረጉበት ነገር ደግሞ ያለ ምንም ጥርጥር ሙስተጃብ ነው። ሀጃው ይፈፀማል ።»
የሶሪያው ታላቅ አሊም ረመዷን ቡጢ ረሂሙሁላህ እንዲህ ይሉናል። « ያ አሏህ እንትን ስጠኝ …… ብሎ አሏህን በቀጥታ አንጠልጥሎ መጠየቅ የአደብ ማነስ ምልክት ነው። መባል ያለበት ያ አሏህ ቢጃሂ ረሡል አለይሂ ሰላት ወሰላም ፣ያ አሏህ ቢጃሂ ሀቢቢ አለይሂ ሰላት ወሰላም ፣ ያ አሏህ ቢጃሂ ሙሀመድ አለይሂ ሰላት ወሰላም ………ና በሌሎችም ረሡሎችና አውሊያዎችም ጭምር ተወስሎ ነው ዱአ ሚደረገው። የዱአ ትክክለኛ አጠያየቁ ይህ ነው ይሉናል።
በመጨረሻም በአቡ ሀሠነል ሻዚልይ ረዲየላሁ አንሁ ድንቅ ንግግር ልሠናበታቹሁ « ወደ አሏህ ሀድራ ለመቅረብ በራፉ ሀቢቢ አለይሂ ሰላት ወሰላም ናቸው። ለየትኛውም ስጦታና ፈድል መክፈቻው ረሡሉ አለይሂ ሰላት ወሰላም ናቸው። ወደ «ሪጃሎች» መድረስ የሚፈልግ መንገዱ እርሳቸው ናቸው። ለየትኛውም ምሉዕነትና ውበት መክፈቻው ሀቢቢ አለይሂ ሰላት ወሰላም ናቸው። ሁሉን ሠጭ ወደ ሆነው አሏህ ሚገባው በዚህ በራፍ ብቻ ነው __ ሌላ በር የለውም። »

#ምርጥ ቂሳ

#ትንሹ ነቢል ሙከረም

شريف نبيل مكرم
❀በቴሌግራም
❀ይ ላ ሉን!


@al_besaa
@al_besaa
@al_besaa
12 viewsشريف نبيل مكرم, 00:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-06 03:47:46 መውሊዱን ናፋቂ …8

ኢብን አባስ ረዲየላሁ አንሁ ባወሩት ሀዲስ ሀቢቢን አለይሂ ሰላት ወሰላም ሠማይ ላይ ካሉ ፍጥረታት በዚህ አንቀፅ አሏህ እንዳስበለጣቸው ተናግረዋል ። ሠማይ ላይ ያሉትን እንዲህ አላቸው « ወመን የቁል ሚንሁም ኢኒ ኢላሁን ሚን ዱኒ ፈዛሊከ ነጅዚሂ ጀሃነም… …( አል አንቢያ 29) ሀቢቢን አለይሂ ሰላት ወሰላም ግን « ሊየግፊረለከ ሏሁ ማተቀደመ ሚን ዘንቢከ ወማተአኽር » አላቸው _ መላኢካዎችን ወንጀል ከፈፀማቹሁ አልምራቹሁም ሲሆን ሀቢቢን አለይሂ ሰላት ወሰላም ግን የፈለከውን ስራ ያለፈውም የወደፊቱም ወንጀልህን ምሬሃለሁ ነው ።
ሁዘይፋ ረዲየላሁ አንሁ ባወሩት ሀዲስ « ጌታየ እንዲህ ሲል አበሠረኝ። መጀመሪያ ጀነት ምትገባው አንተ ነህ። ከአንተ ጋ ያለ ምንም ሂሳብ 70 ሺ ሠው አብሮህ ወደ ጀነት ይገባል……»
ኡነይስ ረዲየላሁ አንሁ ባወሩት ሀዲስ ከረሡሉ አለይሂ ሰላት ወሰላም እንዲህ ሠምቻለሁ « የውመል ቂያማ በእኔ ሸፈዐ ከጀሃነም ነፃ ሚሆነው ምድር ላይ ካለው ዛፍና ዲንጋይ ቁጥር በላይ ነው። »
አልይ ከረመላሁ ወጀሁ ይህን ሀዲስ ነግረውናል « እያንዳንዱ ነብይ 7 ኑጀባ ( የመቃም ደረጃ ነው እንደ ገውስ፣ ቁጥብ፣ አብዳል… እንደሚባሉት አይነት ነው ኑጀባ) ተሠጦል። አንተ ግን 40 ሺ ኑጀባ ተሠጣሃል። አቡበከር፣ ዑመር፣ ብን መስኡድና አማር ብኑ ያሲር ከኑጀባዎች ውስጥ ናቸው።»

#ምርጥ ቂሳ

#ትንሹ ነቢል ሙከረም

شريف نبيل مكرم
❀በቴሌግራም
❀ይ ላ ሉን!


@al_besaa
@al_besaa
@al_besaa
15 viewsشريف نبيل مكرم, 00:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-06 03:47:33 መውሊዱን ናፋቂ …9

መውሊድ በሚቀራበትና ሶለዋት በሚባልበት ሀቢቢ አለይሂ ሰላት ወሰላም ይገኛሉ ( ያሃድራሉ ) ትላላቹሁ እንዴት አለሙን ሁሉ በአንዴ ማካበብ ቻሉ ብሎ ለአንድ መሻኢህ ጠየቃቸው። እርሳቸውም « ፀሃይ ጧት ወጣ ብርሃኖን ስትረጭ ምድርን በሙሉ ታበራለች አይደል አሉት። አወ አለ። ግዑዞ ፀሃይ ይህን መፈፀም ከቻለች የቀልብ ፀሃይ ሲራጀን ሙኒራ _ ተብለው በአሏህ የተገለፁት ረሡለሏህ በአንዴ ሶለዋት በሚሉ አንዋር ሙዕሚኖች ቀልብ ላይ እንዴት ማብራት ይሳናቸዋል? ግዑዙ የፈፀመውን ተግባር ምርጡ ነብይ እንዴት መፈፀም ይከብዳቸዋል ? አሉት ። ጠያቂውም ቀልቡ እርጥብ ስለነበር በሸሁ መልስ ረክቶና አመስግኖ ተለየ።

#ምርጥ ቂሳ

#ትንሹ ነቢል ሙከረም

شريف نبيل شيخ مكرم
❀በቴሌግራም
❀ይ ላ ሉን!


@al_besaa
@al_besaa
@al_besaa
19 viewsشريف نبيل مكرم, 00:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-29 05:52:42 መውሊዱን ናፋቂ … 10
ነብዮ ሙሀመድ ( ሠአወ) ከባልደረቦቻቸው ጋ መስጊድ ውስጥ ተቀምጠዋል። አንድ የሩቅ አገር ግለሠብ መጣና ወደ መስጊዱ ገባ። መስጊዱ ለተሠበሠቡትም « የአሏህን መልዕክተኛ የት ላገኛቸው እችላለሁ ? ብሎ ጠየቀ… ………»
ሀዲሡ ይቀጥላል ። እኔ ግን በዝች አገላለፅ ብቻ እሠናበታለሁ ። ምክኒያቱም ሀቢቢ ከሶሃቦች ጋ ተቀምጠው ረሡሉ የት ናቸው ብሎ ይህ ግለሠብ መጠየቁ የሀቢቢን ከፍተኛ የትህትና ደረጃ አሳይቶኛልና!!!!

#ምርጥ ቂሳ

#ትንሹ ነቢል ሙከረም

شريف نبيل شيخ مكرم
❀በቴሌግራም
❀ይ ላ ሉን!


@al_besaa
@al_besaa
@al_besaa
9 viewsشريف نبيل مكرم, 02:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-29 05:52:27 መውሊዱን ናፋቂ… 11
ሃፊዝ አቡበከር ብን ሙዕሚን አሸይራዚ ባወሩት ሀዲስ « በአሏህ ላይ ተወኩሉ እንዲጨምር የፈለገ አህለል በይትን ( የረሡሉን ቤተሠቦች) ይውደድ። ከቀብር ቅጣት መዳን የፈለገ አህለል ቤትን ይውደድ። ጥበበኛ መሆን የፈለገ አህለል በይትን ይውደድ። ጀነት ያለ ሂሳብ መግባት የፈለገ አህለል በይትን ይውደድ። ነፍሴ በእጁ በሆነች ጌታየ እምላለሁ አህለል ቤትን የወደደ በዱንያም በአኺራም ትርፋማ ነው ሚሆነው። »
በሌላ ሀዲስ «እኔን የወደደኝና እነዚህ በእጃቸው ( ወደ ሀሠንና ሁሴን እንዲሁም አልይና ፋጡማ ) እያመላከቱ የወደደ በጀነት በደረጃ ከእኔ ጋ ነው የሚሆነው » ብለዋል።
አህለልበይትን፣ ሡሃቦችን በአጠቃላይና ዑሳማ ብን ዘይድን በተለየ መልኩ መውደድ (ዑሳማን እወደዋለሁ እናንተም ውደዱት ብለው አፅንኦት ሠጠው አስተምረውናል __ ሀቢቢ) ረሡሉን የመውደድ አንዱ አካል ነው።

#ምርጥ ቂሳ

#ትንሹ ነቢል ሙከረም

شريف نبيل شيخ مكرم
❀በቴሌግራም
❀ይ ላ ሉን!


@al_besaa
@al_besaa
@al_besaa
8 viewsشريف نبيل مكرم, 02:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-29 05:51:58 መውሊዱን ናፋቂ… 12

አቡ ሁረይራ ረዲየላሁ አንሁ ባወሩት ሀዲስ « በይተል መቅዲስ አምቢያዑን በሙሉ ካሠገዱ በሆላ ሚንበሩ ላይ ወጥው በሹክር መስጊዱን አንቀጠቀጡት ። ያኔ ካረጉት ኹጥባ የተወሠነው ይህ ነው ።« ምስጋና ለአሏህ ይገባው። ሁላቹሁም ይህን ፈድል ስለተገጠማቹሁ አሏህን አመስግኑ። እኔ ዛሬ የተነባባረ ምስጋናየን ማደርስበት ቀን ነው። ለአለማት በሙሉ እዝነት አርጎ ስለላከኝ አመሠግነዋለሁ። ለሠው ዘር በሙሉ አብሳሪና አስጠንቃቂ አርጎ ስለላከኝ አመሠግነዋለሁ። ሁሉንም አጀንዳ የሚያብራራውን « ፉርቃንን » ስለሠጠኝ አመሠግነዋለሁ። ዑመቴን ምርጡ ኡማ ስላደረገልኝ አመሠግነዋለሁ። ዑመቴን ሚዛናዊ ኡማ ስላደረገልኝ አመሠግነዋለሁ። ልቤን ለኢማንና ለጥበብ ስለከፈተልኝ አመሠግነዋለሁ። አይኔን ንፁሁ ነገር ብቻ እንዳይ አድርጎ ስለፈጠረኝ አመሠግነዋለሁ። መወሳቴን ከፍ ስላረገልኝ አመሠግነዋለሁ። የድልና የስኬት ባለቤት አርጎ ስለላከኝ አመሠግነዋለሁ………»
ከዚያም ወደ ሠማይ በረሩ። ሁሉም ነብያቶች ሷሊሁ ወንድማችን እንኳን ደህና መጣህ እያሉ ተቀበሎቸው። አደምና ኢብራሂም ዐለይሂ ወሰለም ግን ሷሊሁ ልጃችን እንኳን ደህና መጣህ ሚለውን ተጠቀሙ። ሙሳን ዐለይሂ ሰላም አልፈውት ሲሄዱ ሙሳ ዐለይሂ ሰላም እንዲህ አሉ « እስከዝች ሠአት ድረስ ከሁሉም ነብያት እኔ እበልጣለሁ የሚል ጥርጣሬ ነበረኝ ግን አልሆነም አሉ።

#ምርጥ ቂሳ

#ትንሹ ነቢል ሙከረም

شريف نبيل مكرم
❀በቴሌግራም
❀ይ ላ ሉን!


@al_besaa
@al_besaa
@al_besaa
5 viewsشريف نبيل مكرم, 02:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ