Get Mystery Box with random crypto!

መውሊዱን ናፋቂ… 12 አቡ ሁረይራ ረዲየላሁ አንሁ ባወሩት ሀዲስ « በይተል መቅዲስ አ | አል_በሳዕ

መውሊዱን ናፋቂ… 12

አቡ ሁረይራ ረዲየላሁ አንሁ ባወሩት ሀዲስ « በይተል መቅዲስ አምቢያዑን በሙሉ ካሠገዱ በሆላ ሚንበሩ ላይ ወጥው በሹክር መስጊዱን አንቀጠቀጡት ። ያኔ ካረጉት ኹጥባ የተወሠነው ይህ ነው ።« ምስጋና ለአሏህ ይገባው። ሁላቹሁም ይህን ፈድል ስለተገጠማቹሁ አሏህን አመስግኑ። እኔ ዛሬ የተነባባረ ምስጋናየን ማደርስበት ቀን ነው። ለአለማት በሙሉ እዝነት አርጎ ስለላከኝ አመሠግነዋለሁ። ለሠው ዘር በሙሉ አብሳሪና አስጠንቃቂ አርጎ ስለላከኝ አመሠግነዋለሁ። ሁሉንም አጀንዳ የሚያብራራውን « ፉርቃንን » ስለሠጠኝ አመሠግነዋለሁ። ዑመቴን ምርጡ ኡማ ስላደረገልኝ አመሠግነዋለሁ። ዑመቴን ሚዛናዊ ኡማ ስላደረገልኝ አመሠግነዋለሁ። ልቤን ለኢማንና ለጥበብ ስለከፈተልኝ አመሠግነዋለሁ። አይኔን ንፁሁ ነገር ብቻ እንዳይ አድርጎ ስለፈጠረኝ አመሠግነዋለሁ። መወሳቴን ከፍ ስላረገልኝ አመሠግነዋለሁ። የድልና የስኬት ባለቤት አርጎ ስለላከኝ አመሠግነዋለሁ………»
ከዚያም ወደ ሠማይ በረሩ። ሁሉም ነብያቶች ሷሊሁ ወንድማችን እንኳን ደህና መጣህ እያሉ ተቀበሎቸው። አደምና ኢብራሂም ዐለይሂ ወሰለም ግን ሷሊሁ ልጃችን እንኳን ደህና መጣህ ሚለውን ተጠቀሙ። ሙሳን ዐለይሂ ሰላም አልፈውት ሲሄዱ ሙሳ ዐለይሂ ሰላም እንዲህ አሉ « እስከዝች ሠአት ድረስ ከሁሉም ነብያት እኔ እበልጣለሁ የሚል ጥርጣሬ ነበረኝ ግን አልሆነም አሉ።

#ምርጥ ቂሳ

#ትንሹ ነቢል ሙከረም

شريف نبيل مكرم
❀በቴሌግራም
❀ይ ላ ሉን!


@al_besaa
@al_besaa
@al_besaa