Get Mystery Box with random crypto!

ቀን 13/12/2014 ዓ.ም ከ2ሺ 900 በላይ ለሚሆኑ የ9ኛ ክፍል ተማሪዎች ልዩ የክረምት ማጠና | Addis Ketema Education Office

ቀን 13/12/2014 ዓ.ም

ከ2ሺ 900 በላይ ለሚሆኑ የ9ኛ ክፍል ተማሪዎች ልዩ የክረምት ማጠናከሪያ ትምህርት እየሰጠ መሆኑን የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡

በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ውስጥ በሚገኙ ስምንት 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ውስጥ በ2014 የትምህርት ዘመን የ9ኛ ክፍል ተማሪዎችን ስነ-ምግባርና ውጤት ለማሻሻል እንደ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ጥናት መጠናቱን የገለፁት የጽ/ቤት ሃላፊዋ ወ/ሪት ሳምራዊት ቅባቱ በጥናቱ ግኝት መነሻ የተሰጠው የመፍትሄ ሀሳብ ተማሪዎችን በተጠናከረ መልኩ የማጠናከሪያ ትምህርት በመስጠት ውጤታቸውን ማሻሻል እንደሚቻል ያመላከተ በመሆኑ በመደበኛ ትምህርት ወቅት የሚሰጠው ማጠናከሪያ ትምህርት እንደተጠበቀ ሆኖ ወደ 10ኛ ክፍል መግባት ያልቻሉትን ተማሪዎች እና ከ8ኛ ወደ 9ኛ ክፍል የተዛወሩትን በተመደቡበት 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች በክረምት መርሀ ግብር ማጠናከሪያ ትምህርት መስጠት አስፈላጎ ሆኗል ብለዋል፡፡

በዚህ መነሻነትም በአስኮ፣ በሚሊንየም፣ በኮልፌ፣ በድላችን፣ በአዲስ ከተማ፣ በየካቲት 23 እና በአቢሲንያ 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች በአጠቃላይ ለ2,908 ተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርቱን በጥብቅ ዲሲፕሊን እየተከታተሉ እንደሚገኙ ወ/ሪት ሳምራዊት ገልጸዋል፡፡

ሃላፊዋ አክለውም በተለይ የ9ኛ ክፍል ተማሪዎች በክረምት ማጠናከሪያ መማራቸው የሚማሩበትን ት/ቤት አካባቢ በደንብ እንዲያውቁትና ከወዲሁ የሚጠበቅባቸውን ሁሉ ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ የሚያግዛቸው ከመሆኑም በተጨማሪ ትምህርታቸው ላይ ብቻ ትኩረት እንዲያደርጉ ማንቂያ በመሆኑ ያልመጡ ተማሪዎችም ከላይ በተዘረዘሩት ት/ቤቶች በመገኘት ትምህርታቸውን መከታተል እንደሚችሉ ጥሪ እናስተላልፋለን ብለዋል፡፡