Get Mystery Box with random crypto!

ጎዶልያስ

የቴሌግራም ቻናል አርማ aklesyazetewahdo — ጎዶልያስ
የቴሌግራም ቻናል አርማ aklesyazetewahdo — ጎዶልያስ
የሰርጥ አድራሻ: @aklesyazetewahdo
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 178

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2023-02-05 20:25:28
ዛሬ በኮምቦልቻ
89 viewsታኦሎጎሥ, edited  17:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-05 10:29:56
ደሴ
ጥር 28/05/2015
ታላቅ ሰላማዊ ሠልፍ እየተደረገ ይገኛል
41 viewsታኦሎጎሥ, 07:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-04 22:58:01 የካቲት 5 ሰልፍ የጠራው ቅዱስ ሲኖዶስ ብቻ አይደለም:: ሰልፉን የጠራው ዛሬ ጠዋት ለቅድስት ቤተክርስቲያን ክብር በግፍ የተሠዋው ሰማዕት ደም ድምፅ ነው::

ዛሬ ቤታቸው ሳይገቡ እህል ሳይቀምሱ ቤተክርስቲያናቸው ውስጥ ውለው በስናይፐር የተመቱ ምእመናን ደም እኔና አንተ ክርስትና ለተነሣንባት ኃጢአታችንን በንስሓ ለምናራግፍባት የምንቆርብባት የምንዳርባት ስንታመም የምንጠመቅባትና ስንሞት የምንቀበርባትን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንዳናጣ ብለው ነው::

ቤተ ክርስቲያን ለኢትዮጵያ ያልሆነችው የለም:: ትምህርት ሚኒስቴር ሆና ከድንቁርና ጤና ሚኒስቴር ሆና ከበሽታ መከላከያ ሚኒስቴር ሆና ከቅኝ ግዛት የቱሪዝም ሚኒስቴር ሆና ከተራነት ኢትዮጵያን የታደገች ቤተ ክርስቲያን ናት::

ውለታዋ ተረስቶ የተሳዳቢዎች አፍ መፍቻ የሐሰተኞች ትንቢት መለማመጃ ሆና በንዋየ ቅድሳትዋ ተቀልዶ በከበሮዋ ተጨፍሮ ዕረፍት እንድታጣ ሆና መቆየትዋ ሳያንስ አሁን ደግሞ በግልፅ ተዘምቶባታል::

ቅዱስ ሲኖዶስ ያወጀው የጾም አዋጅና የካቲት 5 የጠራው ሰልፍ አባቶቻችን አባት ሆነው የተገኙበት ነው:: ልጆች ሆነን መገኘት የእኔና አንተ ፋንታ ነው:: ሕጋዊነትዋን ይዛ በሰላማዊ መንገድ የጠራችው ተቃውሞ ነውና የተሻለው መንገድም ይኼ ነው:: ከዚህ ቀደም ተጀምሮ የቀረ ሰልፍ ምን ዋጋ እንዳስከፈለን እናውቀዋለን:: አሁን በምንም ወደ ኋላ ማለት የለብንም:: በጎበዝ አለቃ መመራት በተባራሪ ወሬ መነዳት ትተን ከቤተ ክርስቲያናችን ጎን እንቁም:: ጉዳዩ የሐዋርያዊው ቅዱስ ሲኖዶስ ልዕልና ጉዳይ ሆኖ ሳለ የዘርና የቋንቋ ጉዳይ ለማድረግ የሚጥሩ ሰዎችን ጆሮ ባለ መስጠት በማያምኑባት ቤተ ክርስቲያን ውድቀትዋን ተመኝተው የሚሳደቡ እነ "ብጥብጥ አማረኝ"ን በቻልነው ሁሉ ብሎክ በማድረግ ጆሮአችንን ለቤተ ክርስቲያን ብቻ እንሥጥ::

ድርድር ሽምግልና ወዘተ የሚሉ የማዘናጊያ ሃሳቦች ፈጽሞ ተቀባይነት የላቸውም:: ተጽእኖ ፈጣሪ ሰዎች እጃችሁን አስገቡ ብትባሉም እንኳን ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን አክብራችሁ እጃችሁን ሰብስቡ:: መነጋገር ካለበት አካል ጋር ሊነጋገር መብት ያለው ቅዱስ ሲኖዶስ ብቻ ሲሆን ከሰልፉ በኋላ የሚለንን እንሰማለን:: የእኛ ድርሻ ቤተ ክርስቲያን ያለችንን ብቻ ማድረግ ነው::

ዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ

#yekatit5
#one_patriarch
#አንድ_ሲኖዶስ
#eotc_one_holy_synod
#OrientalOrthodox

@aklesyazetewahdo
@aklesyazetewahdo
@aklesyazetewahdo
24 viewsታኦሎጎሥ, 19:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-04 22:47:44
14 viewsታኦሎጎሥ, 19:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-04 21:29:55
"አንድ ሀገርን እመራለሁ የሚል መንግሥት የሕዝቡን በሕይወት የመኖር ሰብዓዊ መብት ማክበር እና ማስከበር ካልተቻለው መንግሥትነቱ ምኑ ላይ ነው?" -ብፁዕ አቡነ ሄኖክ

ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በዛሬው ዕለት በሻሸመኔ ኦርቶዶክሳውያን ላይ በመንግሥት አካላት የተፈጸመውን ግድያና ማዋከብን አስመልክቶ ጥሪ አቅርበዋል።

ብፁዕነታቸው በማኅበራዊ የትሥሥር ገጻቸው ባሠፈሩት መልእክት የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በቤተ ክርስቲያን እና በክርስቲያኖችን ላይ እያደረሰ የሚገኘውን የማሳደድ ተግባር በአስቸኳይ እንዲያቆም ጥሪያችንን እናቀርባለን ብለዋል::

በሰሜን ኢትዮጵያ ሕግ እናስከብራለን በሚል በትግራይ እንቅስቃሴ ሲያደርግ የነበረው የኢትዮጵያ መንግስት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ለማፍረስ ከተሰበሰበ ወራሪ ቡድን ጋር በማበር በጠራራ ፀሐይ ሕግ ሲጥስና የሕግ አፍራሾች ተባባሪ ሆኖ ማየት እጅግ አሳፋሪ እና አንገት የሚያስደፋ ድርጊት ነው በማለት ገልጸዋል።

በሻሸመኔ ከተማ በኦርቶዶክሳውያን ልጆቻችን ላይ እየተፈፀመ የሚገኘው ግፍ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖትን ለማጥፋት ከሚደረግ የዘር ጭፍጨፋ ተለይቶ የሚታይ አይደለም።

አንድ ሀገርን እመራለሁ የሚል መንግሥት የሕዝቡን በሕይወት የመኖር ሰብዓዊ መብት ማክበር እና ማስከበር ካልተቻለው መንግሥትነቱ ምኑ ላይ ነው?
14 viewsታኦሎጎሥ, 18:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-04 19:57:42
ከቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ
19 viewsታኦሎጎሥ, 16:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-04 19:44:54
"ምዕመናን ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ለመጠበቅ በሚያደርጉት ጥረት ለሚፈጠረው ችግር መንግሥት ኃላፊነቱን ይወስዳል"
ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ

በምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት ሻሸመኔ ከተማ በሕገ ወጥ የተሾመው ቡድን መንበረ ጵጵስና እና ቤተ ክርስቲያን ሰብረን እንገባለን በማለት በምእመናን ላይ ስጋት መፍጠሩን ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የሲዳማ፣ ጌዲዮ፣ አማሮ፣ ቡርጂና ምዕራብ አርሲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ማምሻውን ለማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን አሳወቁ።

ከሰሞኑን የሀገረ ስብከቱ አገልጋዮች ያለምክንያት እየታሰሩ ነው ያሉት ብፁዕነታቸው ይህንንም ለሚመለከተው የዞን ፀጥታ አካል ለማሳወቅና ጥበቃ እንዲያደርጉ ብንደውልም፣ መልእክት ብንጽፍም ሊመልሱልን አልቻሉም ብለዋል።

በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ መሠረት ለኦሮምያ ክልል የሚመለከታቸው አካላት በተለይም ጥበቃና ከለላን በተመለከተ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ አስቀድሞ ደብዳቤ ቢጻፍም ምንም አይነት የቃልም ሆነ የተግባር መልስ እንዳልተሰጣቸውም ተናግረዋል።

ብፁዕነታቸው አክለውም መንግሥት በሕገ ወጡ ቡድን የሚደረገውን ድርጊት ማስቆም ካልቻለ ምእመናን ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ለመጠበቅ በሚያደርጉት ጥረት ለሚፈጠረው ችግር ኃላፊነቱን ይወስዳል ብለዋል።

በመጨረሻም ምእመናን ቤተ ክርስቲያናቸውን እንዲጠብቁ መልእክት አስተላልፈዋል።

ምንጭ:- የኢ/ኦ/ተ/ቤ መገናኛ ብዙኅን አግልግሎት ሥርጭት ድርጅት
53 viewsታኦሎጎሥ, 16:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-04 19:39:16 መንግሥትም ሰላም እና ደህንነትን ከማስጠበቅ ባለፈ የሕይወት እና የአካል ደህንነት መብትን እንዲሁም የመንቀሳቀስ መብትን በመገደብ ያለአግባብ ታግተው መቆየታቸውን ከሊቃነ ጳጳሳት ውስጥ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስን ከዚህ ቀደም መግለጻችን የሚታወቅ ሲሆን ከዚህ ድርጊታቸውም ሳይታቀቡ በጥር 26 ቀን 2015 ዓ.ም ከምሽቱ 3፡30 አካባቢ የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የሆኑትን ብጹዕ አቡነ ያሬድን በሕገ ወጥ መልኩ የዜግነት መብታቸው ተጥሶ በደረቅ ሌሊት በማሰር እና በማዋከብ ከሀገረ ስብከታቸው ለቀው እንዲወጡ የተደረጉ ሲሆን እንዲሁም የተለያዩ አህጉረ ስብከት ሊቃነ ጳጳሳትን ወደየ አህጉረ ስብከታቸው እንዳይሄዱ ማስፈራሪያ በመላክ የቤተ ክርስቲያችንን ክብር እና ልዕልና እጅጉን የሚጎዳ እና አሳዛኝ ድርጊት እየተፈጸመባት ይገኛል፡፡ በተጨማሪም የየሀገረ ስብከት ሥራ አኪያጆችንና ሠራተኞችን፤ አገልጋይ ካህናትንና ምእመናን በሕገ ወጥ መልኩ በማሰር እንደ መንግሥት የሚጠበቅበትን ኃላፊነት ባለመወጣቱ ቤተ ክርስቲያናችን እጅጉን አዝናለች፡፡

ከዚህም አልፎ መንግሥትም በቤተ ክርስቲያችን በኩል በተደጋጋሚ የተሰጠውን ማሳሰቢያ ችላ በማለቱ ምክንያት በምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት በሻሸመኔ ከተማ ሕገ ወጦቹ መንግሥትን ተገን በማድረግ የቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን በሕገ ወጥ መልኩ ወረራ ለመፈጸም ባደረጉት እንቅስቃሴ ቤተ ክርስቲያንችንን ለመጠበቅ በወጡ ምእመናን ላይ ፖሊስ በወሰደው እርምጃ ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ የአደባባይ የግድያ ወንጀል ተፈጽሟል፡፡ ሌሎች በቁጥር ያልታወቁ ምእመናንም ላይ ከፍተኛ እና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ 

ይህንንም ሕገ ወጥ ተግባር በተመለከተ ተገቢውን ሕጋዊ የሰላም እና የደህንነት ከለላ እንዲያደርጉ ለሚመለከታቸው የፌዴራል እና የክልል መንግሥታት በተደጋጋሚ ማሳሰቢያ ቤተ ክርስቲያናችን ብትሰጥም ይህንን ማሳሰቢያ ወደጎን በመተው መንግሥት ሕገ ወጡን ቡድን በመደገፍ እና በማስፈጸም ከላይ የተገለጹትን አሳዛኝ ድርጊቶች በይፋ በአደባባይ ፈጽሟል፡፡

ስለሆነም የኢትዮጵያ ኦርቶደክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በጠራው አስቸኳይ ጉባዔ የሚከተሉትን ውሳኔዎች አስተላልፏል፡፡

1. በብፁዐን ሊቃነ ጳጳሳት እና የአህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጆች፤ የክፍል ኃላፊዎች፤ ካህናት፤ አገልጋዮች እና ምእመናን ላይ የተፈጸመውንና እና እየተፈጸመ ያለውን ሕገ ወጥ እስር እና ወከባ ቅዱስ ሲኖዶስ በፅኑ አውግዟል፤
2. በጥር 27 ቀን 2015 ዓ.ም በምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት በሻሸመኔ ከተማ በደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን፤ ቤተ ክርስቲያንን ለመጠበቅ የወጡት ምዕመናን ላይ ጭካኔ በተሞላ ሁኔታ የተፈጸመው ሕገ ወጥ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እና የተፈጸመው አሰቃቂ የሞት ድርጊትን ፍጹም ታወግዛለች፤ ተገቢውን ሲኖዶሳዊ እና ሃይማኖታዊ ጸሎት በማድረግ በሁሉም አጥቢያ ሥርዓተ ፍትሐት እንዲፈጸም ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፤
3. ቅዱስ ሲኖዶስ በጥር 26 ቀን 2015 ዓ.ም ባስተላለፈው ውሳኔ እና በሰጠው መግለጫ መላው የቤተ ክርስቲያኒቱ ተከታዮች ጾመ ነነዌን ሙሉ የሱባዔ ጊዜ በማድረግ ጥቁር ልብስ ያለውን ትርጓሜ በመግለጥ እንድንሰነብት መግለጫ መሰጠቱ ይታወሳል፡፡
3.1. ለዚህም ዝርዝር አፈጻጸም መመሪያ ማውጣት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ከጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 3 ቀናት በመላው ዓለም የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ የምትገኙ ማናቸውም ካህናት እና ምዕመናን ሙሉ ጥቁር ልብስ በመልበስ በየአብያተ ክርስቲያናት እና በገዳማት ያለውን ሥርዓተ ጸሎት እንድትመሩ እና እንድትከታተሉ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፤
3.2. በየትኛውም እንቅስቃሴ ይህንን ጥቁር ልብስ በመልበስ የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔ ንቁ በመሆን እንድትፈጽሙ፤ ሆኖም ግን ቅዱስ ሲኖዶስ ይህንን ዓለም አቀፍ የጸሎትና የምህላ መርሐ ግብር ካወጀበት ቀን በኃላ በተለያዩ ከተሞች የጥቁር ልብስን ሆነ ተብሎ ከገበያ እንዲወጣ እየተደረገ መሆኑን በመረዳታችን ምዕመናን ያላችሁን ተመሳሳይ አልባሳት በመጠቀም የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔን በእንቅስቃሴያችሁ ሁሉ እንድትፈጽሙ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፤
3.3. በነዚህ ቀናት ውስጥ አገልግሎቱ በድምጽ ማጉያ እንዲከናወን እና የሙሉ ጊዜ ሆኖ በሰባቱ የጸሎት ሰዓታት እየተጠበቀ በተመሳሳይ ሰዓታት ለአምስት ደቂቃ ያህል በማያቋርጥ ደወል በመደወል የማስተጋባት ሥራ እንዲሠራ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፤
3.4. ይህንንም የየአህጉረ ስብከት፤ የወረዳ ቤተ ክህነት እና የአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ሰበካ ጉባኤያት በመከታተል እንድታስፈጽሙ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
3.5. የአኃት አብያተ ክርስቲያናት፤ የኦርቶዶክስ ዓለም፤ እውነቱን የምታውቁና የምትደግፉ ማናቸውም ኃይማኖታዊም ሆነ ማህበራዊ ተቋማት እና ግለሰቦች የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንን ጥሪ በመደገፍ በአንድነት ትቆሙ ዘንድ ጥሪያችንን እናስተላፋለን፡፡
4. በነዚህ የጸሎትና የምሕላ ጊዜያት የደነደኑ ልቦች ወደ ልቦናቸው ተመልሰው የቤተ ክርስቲያኒቱን ጥሪ ሰምተው የማይፈጽሙ እንደሆነ
4.1. በየካቲት 5 ቀን 2015 ዓ.ም በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ካህናት እና ምእመናን ከጠዋቱ 11፡00 ጀምሮ በየአጥብያቸው በሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት እስከ ጠዋቱ 1፡30 ድረስ ሥርዓተ ቅዳሴው ከተፈጸመ በኃላ ከጠዋቱ 2፡00 ላይ ሁሉም ገዳማት፣ አድባራት እና አብያተ ክርስቲያናት በተመሳሳይ ሰዓት ደወል በመደወል ምእመናን በሙሉ እስከ ጠዋቱ 2፡30 ድረስ እንዲሰባሰቡ በማድረግ ከየአጥቢያው በመነሳት የጥምቀተ ባህር ወይም የመስቀል አደባባይ ላይ ታቦተ ሕጉን በማክበር፤ በማጀብ በዝማሬ እና በእልልታ በአንድ ቦታ በመሰባሰብ ሰላማዊ ሰልፍ እንዲደረግ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
4.2. የዚህ ሰላማዊ ሰልፍ ዝርዝር አፈጻጸም መመሪያን በተመለከተ በአጭር ጊዜ ውስጥ የምናሳውቃችሁ መሆኑን አውቃችሁ ዝግጅት እንድታደርጉ ቅዱስ ሲኖዶስ ያሳስባል፡፡ 
5. ማንኛውም የመንግሥት የጸጥታ ኃይል ቤተ ክርስቲያን ያዘዘችውን ሰላማዊ ጥያቄ በሚከወንበት ማንኛውም የአገልግሎት ጊዜ ተግባራቱ ሰላማዊ መሆናቸውን በመገንዘብ ተገቢውን ጥበቃ የማድረግ ግዴታ እንዳለበት አውቆ እንዲያስፈጽም ቅዱስ ሲኖዶስ ያሳስባል፤

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ
ጥር 27 ቀን 2015 ዓ.ም
አዲስ አበባ
ኢትዮጵያ
@aklesyazetewahdo
@aklesyazetewahdo
@aklesyazetewahdo
24 viewsታኦሎጎሥ, 16:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-04 19:39:16
ሰበር ዜና

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

ከኢትዮጵያ ኦርቶደክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ አዋጅ

በመንፈስ ቅዱስ የሚመራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በጥር 18 ቀን 2015 ዓ.ም ባደረው አስቸኳይ ምልዐተ ጉባኤ በኢትዮጵያ የኦሮሚያ እና የብሔር ብሔረሰቦች ቅዱስ ሲኖዶስ በሚል በሕገ ወጥነት በቀድሞ ስማቸው አባ ሳዊሮስ የተባሉ ግለሰብ መሪነት ይህ መግለጫ እስከተሰጠበት ቀን ድረስ በተለያዩ ክልሎች እና የፌዴራል መንግሥት በሚመራቸው ቦታዎች ውስጥ በሚገኙ የቤተ ክርስቲያኗ አህጉረ ስብከት የሆኑትን ሥርዓተ አምልኮዋን የምትፈጽምባቸው በየመዋቅሩ የሚገኙ አስተዳደር ቢሮዎችን  ከሕግ አግባብ ውጭ የቤተ ክርስቲያኗ እምነት ተከታይ ያልሆኑ ግለሰቦችን በማካተት በመንግሥት ልዩ ኃይል ድጋፍ በመውረር እና በመስበር የሕግ አግባብነት በሌላቸው  እንዲሁም መብት እና ጥቅም ሳይኖራቸው በማሸግ ቤተ ክርስቲያን ላይ ወረራ እየተፈጸመባት የሚገኝ መሆኑን ቅዱስ ሲኖዶስ ለመረዳት ችሏል፡፡
25 viewsታኦሎጎሥ, 16:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-04 19:37:36
በአሰበ ተፈሪ/ጭሮ/ ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን የጸጥታ ኃይሎች አስለቃሽ ጭስ ወደ ምእመናን እየወረወሩና ተኩስ መጀመራቸውን ምእመናን ለማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ገለጹ።
ምእመናን ከጠዋት ጀምረው ቤተ ክርስቲያኗን ሲጠብቁ የነበረ ሲሆን የዞኑ የጸጥታ ኃይል "በሁለታችሁ አንገባም" በማለት ገለልተኛ ለመሆን ሞክሮ ውሏል።
ነገር ግን ከመሼ ከክልል የመጣ ትእዛዝ ነው በሚል የክልሉ ልዩ ኃይልን ጨምሮ ተኩስ በመክፈት አስለቃሽ ጭስ ወደ ምእምናን እየወረወረ መሆኑን ምእምናን በስልክ ገልጸውልናል።
መረጃውን ያደረሱን ምእመናን አክለውም የጸጥታ ኃይሉ ቤተ ክርስቲያኑ ከቦ እየተኮሰና እያወከበ ቢሆንም ምእመኑ ግን ከግቢ አልወጣም ብሏል።

@aklesyazetewahdo
@aklesyazetewahdo
@aklesyazetewahdo
26 viewsታኦሎጎሥ, 16:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ