Get Mystery Box with random crypto!

ፍቅር እንደ ዝናብ ከሰማይ አይወርድም ያበባ መደብ ነው በሰው የሚታነፅ : በሰው የሚወድም ተዘርቶብ | Aki Man Z Menz

ፍቅር እንደ ዝናብ ከሰማይ አይወርድም
ያበባ መደብ ነው
በሰው የሚታነፅ : በሰው የሚወድም
ተዘርቶብን እንጂ :ተሰብከን አንወድም::
"ወዳጄ ወዳጄ " የሚያቀነቅኑ
አገር ያቀኑ ለት መች ልብን አቀኑ
ሳይወጡ ሳይወርዱ
ውብ ስራን ከውብ ቃል :ሳያስተባብሩ
ከድሜ እና ከምቾት ቆርሰው ሳይገብሩ
ፍቅር መች ይፈልቃል?
በስብከት በምልጃ በየዋህ ሰዎች ህልም
ያልጣዱት አይበስልም
ያልዘሩት አይበቅልም::