Get Mystery Box with random crypto!

'የጠላህ ይጠላ ፣ ብድሩ ይድረሰው ያጎደፈህ ይጉደፍ ፣ ጭቅቅት ያልብሰው' ብዬ አልራገምም!!! የ | Aki Man Z Menz

"የጠላህ ይጠላ ፣ ብድሩ ይድረሰው
ያጎደፈህ ይጉደፍ ፣ ጭቅቅት ያልብሰው"
ብዬ አልራገምም!!!
የሚጠላህ ጠልቶኝ ፣ ነፍሴን ሲያስጨንቃት
የ'ውነት አንገትህን
የተረት ሸምቀቆ ፣ አስገብቶ ሲያንቃት
አንተን ለሚረግሙ
አንተ እንዳስተማርከኝ ፣ እነሆ ምርቃት።
።።።
"የጠላህ ይወደድ ፣ ይራቀው አመፃ
ያጨቀየህ ይጥራ ፣ ያጎደፈህ ይንፃ!!!
።።።
ባንተ የሚጠላኝ
ቂም በቀል ጥላቻን ፣ ፈፅም አይቅመሰው
አንተ እንዳስተማርከኝ ፣ ነፃነት ላውርሰው
እነሆ ነፃነት
ሞቶም ድል አድራጊ ፣ ምኒልክ ህያው ሰው!