Get Mystery Box with random crypto!

ዛሬ ብንሞት ምን የማይቋረጥ መልካም ስራ አለን? ነብዩ ሶለላሁ ዐለይዊ ወሰለም እንዲህ ይላሉ:– | Ahmedin Jebel - አሕመዲን ጀበል

ዛሬ ብንሞት ምን የማይቋረጥ መልካም ስራ አለን?

ነብዩ ሶለላሁ ዐለይዊ ወሰለም እንዲህ ይላሉ:–

"የሰው ልጅ ሲሞት ስራው ይቋረጣል። ከሶስት ሲቀር።

① ቀጣይነት ያለው ሶደቃ፣

② ወይም ሰዎች የሚጠቀሙበት እውቀት፣

③ ወይ ደግሞ ዱዓ የሚያደርግለት ጥሩ ልጅ።" [ሙስሊም]

የቱ ጋር አለህ? የቱ ጋር አለሽ?

① ከቻልን ህዝብ የሚጠቅም ሶደቃ ጥለን እንለፍ።

② ወይ ደግሞ ወይ አውቀን እናሳውቅ። ወይ የዑለማዎችን እውቀት እናስራጭ።

③ ልጆቻችንን ደግሞ በጥሩ ሁኔታ ኮትኩተን እናሳድግ። ከሁሉም አለመኖር ግን አሳዛኝ ብክነት ነው።

T.me/ahmedin99