Get Mystery Box with random crypto!

ዛሬ ስታፈጥሩ የነበረው ድባብ እንዴት ነበር? ተብሎ ቢጠየቅ የአብዛኛው ሰው መልስ 'እጅግ አሪፍ ነ | Ahmedin Jebel - አሕመዲን ጀበል

ዛሬ ስታፈጥሩ የነበረው ድባብ እንዴት ነበር? ተብሎ ቢጠየቅ የአብዛኛው ሰው መልስ "እጅግ አሪፍ ነበር" ምግቡ፣ መጠጡ፣ ብስኩቱ፣ ሳንቡሳው፣ሀብሀቡ...ለጉድ ነው የሚል ይሆናል።ይሄን ሁሉ አተራምሰን ነው ለዒሻእና ተራዊህ ሰላት የምንሄደው፤ ግና ወንድሞቻችስ? ጎረቤቶቻችንስ? እንዴት እንደሆኑ አስበን እናውቃለን?!

“እናቴ ሰዎች ሰሑር እየተመገቡ ነው፣ ግና እኛ አላፈጠርንም” እያለ እናቱን የሚነዘንዝ ጨቅላ በርካታ ነው። “አባዬ መቼ ነው በስጋ የምናፈጥረው” እያለ አባቱን የሚያስጨንቅ ልጅ የት የለሌ ነው። ስሁር የሚመገቡት አጥተው በቦዶ ሆድ ፆም የሚይዙ ይኖራሉ። እና በዚህ የተባረከ ወር እኚህ ወገኖቻችን ሊታሰቡ አይገባም? ሊታዘንላቸው አይገባምን?

በዚህ በተከበረ ወር ሚስኪኖችን እናስባቸው። ጎረቤቶቻችን እንጠይቃቸው። ድሆችን እንደግፋቸው። ማፍጠሪያ የሌላቸው ብዙዎች ይኖራሉና እናስፈጥራቸው። እኛ የምንሰጣቸው ባይኖር የሚሰጡ ሰዎች ጋር እናገናኛቸው። ይሄን ሁሉ ማድረግ ባንችል እንኳ"አብሽሩ" እንበላቸው።

T.me/ahmedin99