Get Mystery Box with random crypto!

|ኢብኑ ባዝ ቁርአን መኽሉቅ ነው የሚል በግለሰብ ካፊር ነው። ሙስሊም ነኝ እያለ ቀብር የሚያመል | አህሉል ሐዲስ የደርስ ቻናል قناة أهل الحديث

|ኢብኑ ባዝ ቁርአን መኽሉቅ ነው የሚል በግለሰብ ካፊር ነው።

ሙስሊም ነኝ እያለ ቀብር የሚያመልክን፣ ቁርአን መኽሉቅ ነው የሚልን፣የአላህን ከዐርሽ በላይ መሆን የማይቀበልን አሽዐርይ #ዐሊምም ይሁን #ጃሂል በግለሰብ ካፊር ነው እንላለን ለዚህም ማስረጃችን የሰለፎች ስምምነት ነው።ነገር ግን ዛሬ ላይ ወደ ሰለፍያ የሚጠጉ ግን ከሰለፎች ኩቱብ የራቁ ዐዋቂ ነን ባዮች ሰለፎችም ይሁን ኸለፎች በግለሰብ አላከፈሩም ብለው ይሞግታሉ።እስኪ ቢቀበሉ ይህንን የኢማም ኢብኑ ባዝን ፈትዋና ውይይት ይመልከቱ…አላህ ይመራቸው ይምራን

قال الإمام ابن باز : هذا معروف ، أهل السنة يكفرون من قال بخلق القرآن، لان معناه الله ما يتكلم، معناه أن القرءان ليس كلام الله، معناه وصف الله بأنه لا يتكلم ، ساكت
ኢማም ኢብኑ ባዝ እንዲህ አሉ «ይህ የታወቀ ነው።አህሉሱንናህ ቁርአን መኽሉቅ ነው የሚልን ያከፍሩ ነበር ፤ምክኒያቱም ትርጉሙ አላህ አይናገርም እንደማለት ነው።ቁርአንም የአላህ ንግግር አይደለም እንደማለት ነው።አላህን ባለ መናገር ዝም ያለ በማለት መግለፅ ነው።»
فقال أحد الحضور: ما لهم شبهة يل شيخ؟
አንድ ታዳሚ እንዲህ ብሎ ጠየቀ "ሹብሃ የላቸውም
فقال الإمام ابن باز رحمه الله: كفر ... لا، نخرجه من الملة. الله عز و جل له كلامه، وصفوه بأنه أبكم ما يتكلم ( يريدون أن يبدلوا كلام الله)، (و إن أحدمن المشركين استجارك فأجره حتى يسمع كلام الله) و الرسول يقول
(إن قريشا منعوني أن أبلغ كلام ربي).
ኢብኑ ባዝ ረሂመሁሏህ እንዲህ አሉ «ኩፍር ነው። የላቸውም፤ ከእስልምና ይወጣሉ።አላህ ንግግር አለው።እነርሱኮ አላህን በማይናገር ዲዳ ገልፀውታል።{አላህ እንዲህ ብሏል} "የአላህን #ንግግር ሊቀይሩት ይፈልጋሉ።" "ከአጋሪዎች አንዱ ጥገኝነትን ቢጠይቅህ የአላህን #ንግግር እስከሚሰማ አስጠጋው" የአላህ መልክተኛም ﷺ እንዲህ ብለዋል "ቁረይሾች የጌታየን #ንግግር እንዳላደርስ ከለከሉኝ"
قال أحد الحضور:هل يكفر المعتزلة؟
ከታዳሚዎች አንዱ እንዲህ አለ "ሙዕተዚላዎች ይከፍራሉን?"
قال الإمام بن باز: ما في شك، من قال بخلق القرآن فهو كافر
ኢማም ኢብኑ ባዝ እንዲህ አሉ "ምንም ጥርጥር የለውም።ቁርአን መኽሉቅ ነው ያለ እርሱ ካፊር ነው።"
قال أحد الحضور: أحمد بن أبي دؤاد يكفر؟
ከታዳሚዎች አንዱ እንዲህ አለ "አህመድ ኢብኑ አቢ ዱአድ ይከፈራል?"
فقال الإمام بن باز: كل من قال بخلق القرآن فهو كافر.
ኢማም ኢብኑ ባዝ እንዲህ አሉ "ቁርአን መኽሉቅ ነው የሚል ሁሉ ካፊር ነው።"
فقال أحد الحضور: عينا يا شيخ؟
ከታዳሚዎች አንዲ እንዲህ አለ "ያ ሸይኽ በግለሰብ?(ይከፈራሉ)
فقال الإمام بن باز: عينا إذا ثبت عليه ذلك.
ኢማም ኢብኑ ባዝ እንዲህ አሉ "ግለሰቡ ላይ ይህን ማለቱ ከተረጋገጠበት አዎ"
فقال عائض القرني: الذهبي في السير يا شيخ ذكر أحمد بن دؤاد قال: هذا و ليس الرجل بكافر، فهو يشهد أن لا إله إلا الله، و يومن بالله.
አዒድ አል-ቀረኒ እንዲህ አለ «አዝ-ዘሃብይ በሲራህ "ይህ ሰውየ ካፊር አይደለም።ከአላህ መስተቀር በሀቅ የሚመለክ የለም ብሎ መስክሯል፤በአላህም ያምናል" ብሏል»
فقال الإمام بن باز : الذهبي ليس من أهل الفقه و البصيرة ، الذهبي عالم من الوسط، يعتني بمصطلح الحديث
ኢማም ኢብኑ ባዝ እንዲህ አለ "አዝ-ዘሃብይ (በዚህ ጉዳይ) የእውቀትና የፊቅህ ባለቤት አይደለም።እርሱ ሙስጠለሃል ሃዲስ ላይ ትኩረት የሚያደርግ መካከለኛ ዐሊም ነው።"
فقال أحد الحضور: حمل المأمون الناس على القول بذلك أليس كفرا؟
አንድ ታዳሚ እንዲህ አለ "መእሙን ሰዎችን በዚህ ላይ ሰዎችን ያስገድድ ነበር ካፊር አይደለምን?"
فقال الإمام بن باز: كفر، المأمون و غير المأمون .
[من شريط الدمعة البازية]
ኢማም ኢብኑ ባዝ እንዲህ አሉ "ይከፍራል።መእሙንም ይሁን ከእርሱ ውጭ ሌላ ይከፍራል።
ደምዐቱል ባዝያ በተባለ ካሴት

ከዘመናችን ዑለሞች ካልመጣላችሁ የማትረኩ ሰዎች ይህንን የዘመናችን ዐሊም ፈትዋ በደንብ ተመልከቱ።የምትቀበሉት የሙዐሲር ስለሆነ ነው እንጅ ከሰለፎችማ በመቶዎች የሚቆጠሩ ደሊሎች አሉ…

وصل الله وسلم علي نبينا وحببينا وقدوتنا محمد ابن عبد الله وعلى آله وصحبه وسلم