Get Mystery Box with random crypto!

… በመንገዳችን ላይ በኃጢአት ሥራዋ በሁሉ ዘንድ የምትታወቅ የአንዲት ሴት ቤት ነበር፡፡ በዚያ ስና | #አሐዱ_መንፈሳዊ_መዝሙር_ቤት

… በመንገዳችን ላይ በኃጢአት ሥራዋ በሁሉ ዘንድ የምትታወቅ የአንዲት ሴት ቤት ነበር፡፡ በዚያ ስናልፍ በሁኔታው የተከበረ ሰው የሚመስል በደጃፏ ተቀምጦ አምርሮ ሲያዝን ቅዱሱ ተመለከተ፡፡ በሁለት እጆቹ ፊቱን ሸፍኖ ያለቅሳል፡፡ ትንሽ ቆይቶ ደግሞ ዓይኖቹን ወደ ሰማይ አቅንቶ ይጸልይና መልሶ ደግሞ አምርሮ ያለቅሳል፡፡

ኒፎን ሁኔታው ልቡን ነክቶት ማልቀስ ጀመረ፡፡ ወደ ተከበረው ሰውም ቀርቦ “ወንድሜ ሆይ! በዚህ ውርደት በተሞላ ሥፍራ ተቀምጠህ በምሬት የምታለቅስ ስለ ምን ነው? ኀዘንህ ልቤን ሰብሮታል፤ እባክህ ስለ እግዚአብሔር ብለህ የሆንከውን ንገረኝ?” ሲል ለመነው፡፡

“የተወደድከው ኒፎን! ከአንተ እንደማይሠወረው እኔ የእግዚአብሔር መልአክ ነኝ፡፡ ክርስቲያን ሁሉ ጥምቀተ ክርስትናን በተቀበለበት ዕለት አንድ ጠባቂ መልአክ ይሰጠዋል፡፡ እኔም አንድ ሰውን እንድጠብቅ ኃላፊነት ተሰጥቶኛል፡፡ ነገር ግን ኃጢአትን አዘውትሮ በመሥራት አስመርሮኛል፡፡ አሁንም እንኳ በዚህ በረከሰ ቤት ከአንዲት ሴት ጋር በዝሙት ራሱን ያጎሰቁላል፡፡ በእግዚአብሔር አርአያና አምሳል የተፈጠረ እንዲህ ያለርኵሰትና የጨለማ ሥራ ተውጦ እየተመለከትሁ አለማልቀስ እንዴት ይቻለኛል?”

“ለምን ከኃጢአት ሥራ እንዲርቅ አታስጠነቅቀውም?” ሲል ኒፎን ጠየቀው፡፡

“እንዳለመታደል ሆኖ አሁን…
____
ከራእየ ኒፎን መጽሐፍ የተቆነጠረ፣
------------------
መጽሐፋ ዋጋ፡ 130 ብር

መጽሐፉን፡ #በአሐዱ_መንፈሳዊ_መዝሙር ቤት ያገኙታል፡፡