Get Mystery Box with random crypto!

በተለያየ ምክንያት ሀገር አቀፍ ምርጫ ባልተደረገባቸዉ አከባቢዎች ምርጫ ለማካሄድ አስፈላጊዉን ዝግጅ | AHADU RADIO FM 94.3

በተለያየ ምክንያት ሀገር አቀፍ ምርጫ ባልተደረገባቸዉ አከባቢዎች ምርጫ ለማካሄድ አስፈላጊዉን ዝግጅት እያደረገ መሆኑን የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ፡፡
ሀገር አቀፍ ምርጫ ሳይደረግባቸዉ የቀሩ ቦታዎች ምርጫዉን ለማካሄድ አስፈላጊዉን ዝግጅት እና ማጣራት እየተደረገ መሆኑን የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሳቢ ብርቱካን ሚዴቅሳ ተናግረዋል፡፡
በፀጥታ ምክንያት ምርጫ ያልተደረገባቸዉ አከባቢዎችን የፀጥታ ሁኔታዎች የማጣራት ስራ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡
በተጨማሪ የምርጫዉ ሂደት ስህተት ያለዉ በመሆኑ ምክንያት እንዲደገሙ የተወሰነባቸዉ አከባቢዎች ምርጫዉን ለማድረግ አስፈፃሚዎችን የመመልመል ስራ እየተሰራ እንደሆም ገልፀዋል፡፡
በቀጣይም የማሟያ ምርጫ በፍጥነት የሚደረግበትን እቅድ በማዉጣት ይፋ እንደሚደረግ ገልፀዉ ምርጫ ቦርድ ብዙ ምርጫ ሂደቶችን በመፈጸም ረገድ ክህሎቱን እና አቅሙን እያሳደገ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡
በቅርቡ ከተደረገዉ የደቡብ ክልል ህዝበ ዉሳኔ ቁጥጥር እና ክትትል ማድረግ የሚያስችሉ ቀልጣፋ አሰራሮችን በመተግበር አቅሙንና ክህሎቱን እያዳበረ መምጣቱን አስታዉቀዋል፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/ahadutelevision
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቴሌግራም፡- https://t.me/ahadutelevision
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦ https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24