Get Mystery Box with random crypto!

የምርጫ ህግ ጥሰቶች እንደነበሩ በምርጫ ታዛቢዎች ሪፖርት በመቅረቡ ውጤት የማረጋገጥ ስራን በታቀደበ | AHADU RADIO FM 94.3

የምርጫ ህግ ጥሰቶች እንደነበሩ በምርጫ ታዛቢዎች ሪፖርት በመቅረቡ ውጤት የማረጋገጥ ስራን በታቀደበት ጊዜ ለማጠናቀቅ እንዳልተቻለ ተገለጸ፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም. በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልላዊ መንግሥት ሥር በሚገኙ ስድስት ዞኖች ማለትም በኮንሶ፣ በደቡብ ኦሞ፣ በወላይታ፣ በጋሞ፣ በጌዴኦ፣ በጎፋ እና በአምስት ልዩ ወረዳዎች በቡርጂ፣ በባስኬቶ፣ በአሌ፣ በአማሮ፣ በደራሼ ላይ የህዝበ ዉሳኔ ማካሄዱ ይታወቃል፡፡

ያካሄደውን የሕዝበ ውሣኔ ጊዜያዊ ውጤት የማዳመር ሥራ በሁሉም ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች ላይ አጠናቆ በዞንና በልዩ ወረዳ ደረጃ ጊዜያዊ ውጤቶች ይፋ ማድረጉን በማስታወስ ቦርዱ የመጨረሻውን ውጤት የማጣራትና የማረጋገጥ ሥራ ከየካቲት 6 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ አርባ ምንጭ ከተማ በሚገኘው የሕዝበ ውሣኔው ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት እየሰራ እንደሚገኝ ከቦርዱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ሆኖም ግን ቀደም ሲል ቦርዱ የመጨረሻውን በቦርድ የተረጋገጠ ውጤት የካቲት 8 ቀን 2015 ዓ.ም ይፋ እንደሚያደርግ የገለፀ ቢሆንም በርከት ያሉ ግድፈቶችና የምርጫ ህግ ጥሰቶች በቦርዱ የምርጫ ክትትል ቡድን እንዲሁም በምርጫ ታዛቢዎች ሪፖርት በመቅረቡ የማጣራት እና ውጤት የማረጋገጥ ስራን በታቀደለት ጊዜ ለማጠናቀቅ አልተቻለም፡፡

በዚህም የውጤት ማጣራትና ማረጋገጥ ስራ የደራሼ፣ አሌ፣ ደቡብ ኦሞ፣ባስኬቶ፣ ኮንሶ እና ቡርጂ ውጤቶችን የማጣራትና የማረጋገጥ ስራ ተጠናቆ ውጤታቸው በቦርዱ የጸደቀ ሲሆን በቀጣይም በቀሪዎቹ ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች ማለትም በአማሮ፣ በወላይታ፣ በጋሞ፣ በጌዴኦ እና የጎፋ ጊዜያዊ ውጤቶች የማጣራትና የማረጋገጥ ሂደት እንደተጠናቀቀ ቦርዱ ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግ አሀዱ ከምርጫ ቦርድ ባገኘው መረጃ ማረጋገጥ ችሏል፡፡