Get Mystery Box with random crypto!

አሐዱ መድረክ ፕሮግራም ጊዜው ፈቅዶ ከሬዲዮ እና ቴሌቪዝን ተሻግሮ ታሪካዊ ሰነድ ሆኖ ያገለግል ዘ | AHADU RADIO FM 94.3

አሐዱ መድረክ ፕሮግራም ጊዜው ፈቅዶ ከሬዲዮ እና ቴሌቪዝን ተሻግሮ ታሪካዊ ሰነድ ሆኖ ያገለግል ዘንድ በመጽሀፍ መልክ ቀርቧል ፡፡ በተቃራኒ ሀሳቦች ክርክርና ምክክር የዳበረ ውይይት ፤በሳል አተያዮች የመነጩበት፤ የአመለካከት ልዩነትን አቻችሎ ለሀገር መስራት ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ ፖለቲካዊ ምክረ ሀሳቦች የቀረቡበት :ለሀገራችን ፖለቲካ ህመም ፈውስ የሚሰጡ ያለፍንበትን ሒደት ወደ ኃላ የሚያሳይ፤ የአሁኑን የፖለቲካ ጉዟችንን የሚገመግም ፤ የወደፊቱን የሚገምት እና የቢሆን ምልከታ የተቀመጠበት; የፖለቲካ ፈውስ እና መድሐኒቶችም ከነ መፍትሔያቸው የተጠቆሙበት መጽሐፍ የፊታችን መስከረም 20/2015 ለአንባቢያን ይቀርባል።