Get Mystery Box with random crypto!

እዚህ ሀገር ለምን አብዛኛዎቹ Programmer or Hacker አይሆኑም??? PART-2 የኢትዮጵ | AHADU ፩ TECH®™

እዚህ ሀገር ለምን አብዛኛዎቹ Programmer or Hacker አይሆኑም??? PART-2

የኢትዮጵያ ቤተሰብ አብዛኛው (Medicine) ካልተማርክ ይሉሀል ቤተሰብ ለልጆቻቸው የሚጠቅመውን ትምህርት እንደ አማራጭ ማቅረብና ጥሩ የትምህርት ክፍል እንዲመርጡ ማገዝ እንጂ የግድ ይህን ተማር ብሎ ማስገደድ ተገቢ አይመስለኝም እንደኔ
 
የልጆች ፍላጎት ይከበር ባይ ነኝ አንድ ልጅ በቤተሰቡ Medicine ተማር ብለውት አልፈልግም ካለ በርግጠኝነት ያ ልጅ የሆነ የተለየ መማር ሚፈለገው ትምህርት አለ ማለት ነው ባይገርማችሁ በትምህርትም የሚከብደው በገንዘብ ማለትም በደሞዝ ከፍተኛ ብር ሚስገኘው Computer ነው በአለም ደረጃም Computer የተማረ ነው More የሚፈልገው ከDoctor ይልቅ እንደ አለመታደል ሆኖ Computer Science,IT,Software- Engineering ኢትዮጵያ ውስጥ ተራ የማይፈልግ ሆነዋል እስክታድግ ነው አይዞን

ዛሬ Game መጫወት የሚወድ  ልጅ ነገ Game Developer ቢሆንስ?

ዛሬ ስልክና Computer መጎርጎር የሚወድ ልጅ ነገ አለ የተባለ የ Cyber Security ባለሞያ ቢሆንስ

ዛሬ ስዎችን በስልክ Photo ማንሳት የሚወድ ልጅ ነገ ተፈላጊ Photographerና Graphics Designer ቢሆንስ

ዛሬ ፊልም ማየት የሚወድ የሚወድ ልጅ ነገ ጎበዝ Movie Editor ቢሆንስ ማን ያውቃል ?

ስለዚህ ሁሉም ቤተሰብ ነገ ምን እንደሚፈጠር በማይታወቅ ነገር  ላይ ባንወስን ጥሩ ነው ከዛ ይልቅ በትርፍ ግዜያቸው ያላቸውን ችሎታ ፍላጎት እንዲያወጡ በር ክፈቱ አበረታቱ

ስልክና Computer ቀኑን ሙሉ ይጠቀሙ እያሉኩ ሳይሆን የትምህርት ና የጥናት ግዜያቸውን በማይሻማ መልኩ እንዲጠቀሙ ፍቀዱ + የሚጠቀሙትን ነገር ትምህርታዊ ነው አይደለም የሚለውን ተከታሉ እንዲሁም የሚጠቀሙበትን Time አውጡላቸዉ ዝም ብሎ መከልከል ተገቢ አይደለም

አይ ካላቹ እናታድያ የነዚህ ልጆች ተስፋ ምንድነው ?

አንዳንዶቹ ልጅ ነህ ቀስ ብለህ University ስትገባ ትማራለህ ይሉሀል የአስተሳሰብ መቀጨጭ እንጂ እንደዛ ሚያሳስበን ቅድምም እንደገለፅኩት   የአለማችን ቁጥር አንዱ ሀብታም Bill Gate በ13 አመቱ ነበር Computer መማር የጀመረው ልጅ እያለ

ኢትዮጵያ ላይ University የምትገባው ለማወቅ ሳይሆን ለመመረቅ ነው አስተማሪው ሀላፊነቱ ማስተማር ትውልድን መቅረፅ ሆኖ ሳለ ተማሪዎችን እንዴት ልጣላቸው ውጤታቸውን እንዴት ላበላሽ በማለት ግዜውን የሚያጠፍበት ተማሪዎች ሲያልፉ ከማየት ይልቅ ሲወድቁ ማየት ሚስደስታቸው ቦታ ነው  ትማራለህ የምትለኝ ያየ ይፍረደው አይደል ይህን ጉዳይ

የሰው ልጆችን ችሎታ አስተሳሰብ ብቃት ከፍ ከሚያደርጉት ነገሮች መካከል አንዱ ማበረታታት (Motivation) ነዉ  

University ላይ አንድ የፈተና ጥያቄ በስትክክል አብራርተህ መልሰህ ነገርግን አንድ (Spelling) ብረሳ ያ ጥያቄን በሙሉ 0 ይደረግብሃል የትም ሀገር የሌለ ነገር በዚህ ሁኔታ ነው ተማሪዎች ነገ ስራ ሚፈጥሩት ? ይሄ አስተማሪ እንደኔ ትውልድ ቀራጭ አይመሰለኝም

በጣት የሚቆጠሩ ጥሩ አስተማሪዎች ግን አለ

አንዳንዱ University ገብቼ Hacking እማራለሁ ብሎ የሚያስብ ሰዉ አይጠፋም ጀለስ Hacking ኮ illegal ነው እንዴት University ገብተህ ለመማር ታስባለህ

አብዛኞቹ ሃከሮች በራሳቸው internet ላይ ተፍ ተፍ ብለው ተምረው ሃከር እንደሆኑ ይናገራሉ

ለማንኛውም የኢትዮጵያ Universityን እንተወው ነገርግን እዚህ ጋር የማሰምረው ነገር ሚኖር አለማችን ላይ  የተሳካላቸው(Successful) የሚባሉ ሰዎች ሙሉ በ ሙሉ ማለት ባልችልም አብዛኞቹ University አልተማሩም.

የኔ ሀሳብ በመጨረሻ

ከላይ የገለፁኩት በሙሉ እውነት ነው ያም ሆነ ይህ ጉዞዋችሁን አታቁሙ መሰናክል እንዲያጠነክራችሁ እንጂ እስከመጨረሻው እንዲጥላቹ አትፍቀዱ ደግሞ ተስፋ የቆረጥክ ቀን መሞትህን እወቀው የ Alibaba Owner Jack-Ma ለ 40 አመት ያህል Computer አልነበረውም Computer የለኝም ብሎ ህልሙን አላቆመም ጠንክሮ ከሰራ የችግሩ ግዜ አልፎ ጥሩ ቀን እንደሚጣ ያውቅ ነበር አልቀረም ያቀን አልፎ አሁን ትልቅ ደረጃ ላይ ደርስዋል ትልቅ የሚለው ይገልፀው ይሆን

ዛሬ ከባድ ነው ነገ ከዛሬ  ይብሳል ከነገወዲያ ግን ነገሮች ቀላል ይሆናሉ ( Jack'Ma)


@Ahadu_Tech ...የእናንተው