Get Mystery Box with random crypto!

እዚህ ሀገር ለምን አብዛኛዎቹ Programmer or Hacker አይሆኑም??? 1 Material | AHADU ፩ TECH®™

እዚህ ሀገር ለምን አብዛኛዎቹ Programmer or Hacker አይሆኑም???

1 Material

ስለ ሃኪንግ ሆነ ስለ ሳይበር ሴኩሪቲ ሲነሳ ቀድሞ ሚጠቀሰው Computer ነው .

Computer ከሌለ ሃኪንግ የለም
የሰው ልጆች በምድር ለመኖር ምግብ ልብስ መጠለያ የመሳሰሉት መሰረታዊ የሆኑ ነገሮች እንደ ሚያስፈልጋቸው ሁሉ
ለ ሃኪንግም Computer መሰረታዊና ቁልፍ የሚባል ቁስ ነው.

ኢትዮጵያ ውስጥ Computer የሚሞክሩ ፍላጎቱ ያላቸው ጎበዝ የሆኑ ብዙ ልጆች አሉ ችግሩ Material ላይ ነው እነዚህ ልጆች ሀሳባቸውን ወደተግባር የሚቀይሩበት Computer የላቸውም.

ከ Computer ቀጥሎ በጣም ወሳኝ የሚባል (Internet Connection) ነው

ኢትዮጵያ ውስጥ ለሃኪንግ ነቀርሳ የሆነው አንዱ Internet ነው  ኢትዮጵያ ውስጥ እንደሚታወቀው Internet በጣም ውድና ቀርፋፋ ነው ሃኪንግ ደግሞ በጣም ፈጣን Internet ይፈልጋል

እውነቱን ተናግሮ የመሸበት ማደር ነው

2G ራሱ የት በስትክክል ይሰራል አሁን አሁን እንጂ 3G ራሱ ማታ ማታ በተአምር አይሰራም Ethio ገበታ ብንል ራሱ 75MB በ 5ብር እየተሸጠ ያውም ለ24 Hours
Ethioele.com ካቀደው በላይ አስመዘገበ ተብሎ 3GB ለ 3ቀን ብለው ሰተው በስትክክል ሚሰራው ከ ለሊቱ 6 ሰአት በዛ ላይ ቀርፋፋ ካልተቀላጠፍ አንደኛውን ቢቀረስ ባይሰጥ Wifi ተብሎ 1MB 499 ገዝተን ሚደርሰው 200 250 k/b  200kb/per/S ማለት 1ድ Laptop Connecte ካደረክ
ቻው በቃ ሌላ (Device) Connect ማድረግ አይታሰብም
እና እንዴት ሃኪንግ ይታሰባል?

ለ ሃኪንግ የሚመረጠው OS Kali Linux ነው 1MB Wifi ቢኖራቹና Linux ለማውረድ ብትፈልጉ
ምን አለፋችሁ ማታ ልትተኙ ስትሉ ማዘዝ ነው ጠዋት ይገባላቹሀል አልፈጠነም

Downloadዱን ተውት እሺ 
Online መማር ብንፈልግ Like Udemy YouTube የመሳሰሉ ላይ የምታዩትን Video  በስትክክል ለመመልከት ብላቹ 480 ላይ ብናደርግ Qualityውን አበቃ Videoው 10ሬ ይቆራረጣል.

በቅርብ ደግሞ የ 4G አገልግሎት ኢትዮጵያ ውስጥ ተደመረ ተብሎ ሲቀወጥ ነበር እኔ በግሌ ፍሬሂወትን ምጠይቀው የተጀመረው የ4G አገልግሎት ሁሉን ያማከለ ነዉ እንዴ ነው መልሱ Clear ነው አይደለም ኢትዮጵያ ውስጥ 4G ስለገባ ሁሉም ይጠቀማል ማለት አይደለም ዝም ብለህ አትፈንጥዝ

በመጀመሪያ 4G ለመጠቀም ስልክህ 4G Network ይቀበላል (Support) ያደርጋል በል አብዛኞቹ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ስልኮች 4G አይቀበሉም ለምን ስልካችን Smart ስላልሆነ አብዛኞቹ ስልኮች 2G GSM ና 3G ነው ሚቀበሉት በርግጠኝነት ከ100% 80 በ መቶ የሚሆኑ ስልኮች 4G አይቀበሉም.

ስለዚህ ስልክህ 4G ማይቀበል ከሆነ 4G አትጠቀምም ለዚህም ነው ሁሉንም ያካተተ ያማከለ አይደለም ያልኩት

4G ለመጠቀም ስልክ መቀየር ያስፈልጋል በዚህ Time ደግሞ ስልክ መግዛት ቀላል አይደለም
በርግጥ ስልክ ሳንቀይር ወደ 4G  መቀየር የምንችልበት መንገድ YouTube በስፋት አለ ነገር ግን
Risk አለው ስልካቹ ሊበላሽ ይችላል እሱ ብቻ አይደለም 4G ሆኖላቹ የሆነ ግዜ ተመልሶ ሊቆም ይችላል በበኩሌ እሱን አልመክርም የሚፈልግ ግን መሞከር ይችላል በራሱ ሀላፊነት.

2 Capabilitie(አቅም)
በሁለተኛ ደረጃ ያስቀመጥኩት አቅም ነው ማለትም
Computer ና Internet መሰረታዊ ነገሮች ናቸው ካልን
Computer ለመግዛትም ሆነ Wifi ለማስገባት ገንዘብ ያስፈልገናል ኢትዮጵያ ላይ በአጠቃላይ ስናይ የያንዳንዱ ሰው የነብስወከብ ገቢ በጣም ትንሽ ጥሩ ነው ለማለት አያስደፍርም አይደለም ጥሩ Computer ና ጥሩ Wifi ለማስገባት ይቅርና ወሩን በሙሉ ዳቦ በሻይ ካልበላህ የምታገኘው ገንዝብ ወር አያደርስም + ኢትዮጵያ ላይ ብር ማጥፋት እንጂ ማግኘት ቀላል አይደለም.
ሰዉ ለመኖር በተቸገረበት በዚህ ግዜ Computer ና Wifi ቤሰብህን ብጠየቅ ትመታለህ ሚመታህም ጥሩ  ቤተሰብ ነው አንዳንድ ከቤት ያባራል. 

በርግጥ የሚጠይቁ ነገር የሚሟላቸው ልጆች አሉ  የሚያሟላም ቤተሰብ አለ ግን ሚዛን ሚደፋው የጠየቁት ነገር የማይሟላላቸውና የማያገኙ ልጆች ናቸው

ሁሉም የራሱን ቤት ያውቃል አይደል

3 Economic
ኢትዮጵያ ውስጥ አብዛኛው አይደለም Computer ና Smart Phone ጫማ ልብስ All ማለት ይቻላል Qualityያቸው የወረደ ነው ለምን ምክንያቱም High Quality ያለውን እቃ ለመግዛት አቅሙ ስለሌለን በማደግ ላይ ስላለን ምርጥና ጠንካራ የሆኑ Product ለመግዛት ለመሸጥ ትንሽ ይከብዳል እሱን ለማድረግ ኢትዮጵያ መበልጸግ አለባት iPhone 40K 50K መግዛት ትችላለህ ?

ኢትዮጵያ በየቦታው የበዛው የ China ምርት ነው  ለምን በዋጋ ዝቅ ያለ ስለሆነና ኪስ ብዙ ስለማይጎዳ እንደምሳሌ ራሱ ብኖስድ Tecno itel infinix የቻይና ምርትቶ ናቸው ገበያ ላይ ኪስ በማይጎዳ እናገኛቸዋለን

የቻይና ምርት አቅም ያማከለ በመሆኑ ቢመሰገንም በጥራት ደረጃ የወረደ ነው የገዛችሁት ስልክ ሆነ Computer አንድ አመት ሳያስጠቅማችሁ ሊበላሽ ይችላል አስተማማኝ ዋስትና የለውም የቻይና ምርቶች ለመበላሸት በጣም ፈጣን ናቸው

ለ ሃኪንግ Purpose እስከሆነ ድረስ የምንገዛው Computer ና Phone አሪፍ Original ና Strong
ቢሆን ተመራጭ ነው

እሱን ለማድረግ Economyያችን ማደግ አለበት Economyያችን እንዲያድግ ሁሉም በየስራ ድርሻው ጠንክሮ መስራት አለበት

ጠንክሮ መስራት የት እንደሚያደርስ ማወቅ ከፈለጋችሁ Japaንን መመልከት በቂ ነው

4 Weak Thinking

Computer ሆነ ስልክ ስትጠቀም ቤት ውስጥ ስልክ ምን ያደርግልሀል ይህን ነገር ተው አንብብ የሁልጊዜው አሰልቺ ጭቅጭቅ ነው ከ ቤተሰቦቻችን ግን አትፍረድባቸው ምክያቱም የዚህ Generation ሰው ሳልሆኑ ትንሽ ይከብዳቸዋል ለመቀበል
ሰይጣን ነው ሁሉ ይላሉ አንዳዶቹ


ወደ ዋናው ቁምነገር ስንገባ ስልክ እጅግ ጠቃሚ ነው
እኔ አላውቅም በዚህ በኔ ቻናል ውስጥ የልጆች ወላጆች ልትኖሩ ትችላላችሁ ልጆቻቹሁን ስልክ በሚጠቀሙ ግዜ አስቀምጥ ተው አትንካ አትበሉ ሰዎች አንድ ነገር ላይ ሙጭጭ ሚሉት አለምክንያት አይደለም ፍላጎቱ ስላላቸው ነው ልጆችን ከልጅነታቸው ነዉ መኮትኮት ያለባቸው ዛሬ ስልክ ሚነካካ ልጅ ነገ ለ ሀገሩ አልፎም አለም ይተርፋል በማስረጃ ለማስደገፍ ያህል በ Computer Hacking በጣም ጎበዝ የሚባለውና በ አለም ሁሉ የሚታወቀው አብዛኞቻቹም የምታውቁት Adward Snowdon የሚባለው አሜሪካዊ መጣት Computer መነካካት የጀመረው ገና በ13 አመቱ ነበር BillGateም በተመሳሳይ በ13 አመቱ ነበር  Computer መነካካት የጀመረው አሁን የት ነው ያሉት ? ትልቅ ቦታ ላይ. ትልቅ የሚለው ቃል ራሱ አይገልፃቸዉም. እነዚህ ሰወች ለዚህ ትልቅ ደረጃ የበቁት በራሳቸው ብቻ ሳይሆን በልጅነታቸው ተው አትንካ አቁም ከማለት ይልቅ በርታ ሞክር እያለ የሚያበረታታ ቤተሰብ ስለነበራቸው ጭምር ነው
በልጅነታቸው ስልክና Computer ሲነኩ ቢመቱ ቢነጠቁ አትንካ ቢባሉ ዛሬ ለዚህ ክብር ችሎታ ባልበቁ ነበር


@Ahadu_Tech