Get Mystery Box with random crypto!

አጋፔ ዘ ኦርቶዶክስ

የቴሌግራም ቻናል አርማ agape_ze_orthodox — አጋፔ ዘ ኦርቶዶክስ
የቴሌግራም ቻናል አርማ agape_ze_orthodox — አጋፔ ዘ ኦርቶዶክስ
የሰርጥ አድራሻ: @agape_ze_orthodox
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.00K
የሰርጥ መግለጫ

✝️በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን✝️
በዚህ ቻናል ውስጥ ኦርቶዶክሳዊ እና መንፈሳዊ ትምህርቶች ፣ ጸሎት ፣ ምክር ፣ ተከታታይ ትምህርት ፣ ወንጌል ወዘተ የምንማማርበት መንፈሳዊ ቻናል ነው ።
Share💯share💯share💯
👇👇👇👇👇👇👇👇
@Agape_ze_orthodox
ለኃሳብ አስተያየት በዚህ ያግኙን
👉 📨 @wededen

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-29 23:47:51 “እኔ ግን እላችኋለሁ፥ በሰማያት ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፥ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፥ ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፥ ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ፤ እርሱ በክፎዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፥ በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና።” — ማቴዎስ 5፥44-45

አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ ጠላታችንን ቀርቶ የሚወዱንንም መውደድ አቅቶናልና የመውደድ ጸጋህን አብዛልን። የሚረግሙንን መመረቅ ቀርቶ ሰላም የሚሙሉንንም መመረቅ አቅቶናልና እባክህ የሚወዱንንም የሚጠሉንንም የምንወድበት አቅም ስጠን።

አቤቱ እግዚአብሔር እምነታችን ላልቷል የክርስትናችን ሕይወታችን ሰንፏን ለሚያሳድዱን መጸለይ አልቻልንም ለሚጹልዩልን እንኳ መንበርከክ አልቻልንም። ለሚጠሉን መልካም ማድረግ ቀርቶ ለምንወዳቸው እንኳ መልካም ለማድረግ ምክንያት የምናበዛ እጅና ፍቅር ያጠረብን ሆነናል። እባክህ ፍቅር አድለን።

አንተን መምሰል ይሁንልን ሃብታም ደሃ ሳትለይ ወንድ ሴት ሳትመርጥ የሚያምን የማያምን ሳትል ሁሉን በአንድ ልብ ወደኃልና እኛም ዘር ጎሳ ብሄር ሳንመርጥ ሰውን ሁሉ እንድንወድ ፍቅርህ ያግዘን። ሸካራው ልባችንን በፍቅርህ ዘይት አለስልስልን። አሜን!

@Agape_ze_orthodox
@Agape_ze_orthodox
896 viewsቀራንዮ, 20:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 23:38:14 ሰላም ለሁላችሁ፤-

ባርያቱ አጋር ከአብርሃም ቤት ከወጣች በኋላ በምድረ በዳ በውሃ ጥማት ተቅበዘበዘች፡፡ ልጄ ሲሞት ከማይ ብላ ልጇን አስቀምጣ ራቅ አለች፡፡ ቸር የሆነው እግዚአብሔር በአጠገቧ የውሃ ምንጭ አንዶለዶለላት! አጋርም ተገረመች እመቤቷን ሳራን በድላ የመጣች በመሆኗ እንደማይገባት ተረዳች፡፡ የሚያየኝን አምላክ አየሁት ስትል ዘመረች፡፡ አጋር በሥጋ እስራኤል ላልሆንን አህዛብ እናት ናት፡፡ እኛ የዓለም ህዝቦች እንደ እስራኤል ርስት የመውረስ ተስፋ አልነበረንም፡፡ ከተስፋው ህዝብ ተለይተን በምድረ በዳ ነበርን፡፡ በታላቅ ጥማትም ነበርን፡፡ ሙሴ ከቆጠረው፣ ዳዊትም ንጉስ ሆኖ ከመራው ወገን አልነበርንም፡፡ ሞት የተባለ ጥላ እያሳደደን በኩነኔ ዘመን ነበርን፡፡ እግዚአብሔር አብ ከድንግል ማሕጸን የህይወት ውሃን በቤተልሔም በረሃ አፈሰሰ፡፡ ይህን ውሃ ጠጥተን ከሞት ተረፍን፡፡ ከእድፋችንም በዚህ ንጹህ ውሃ /በኢየሱስ ክርስቶስ/ ታጠብን፡፡ በርሱ በረሃው ለመለመ፡፡ እኛም እንደ አጋር የሚያየንን አምላክ በእኛ ምሳሌ አየነው፡፡ ነጻ ስጦታው በእኛ ታየ፡፡ በጸጋ አዳነን፡፡ በዓለም ርኩሰት ተይዘን ዘመናትን ላሳፍን ለእኛ ጌታ ኢየሱስ ሳይገባን ጽድቅ ሆኖ ይቆጠርልን ዘንድ አጠገባችን ፈለቀ፡፡ደጉ አብርሃም የተቆጣባትን አጋርን እግዚአብሔር እንዴት ሊቀበላት ቻለ? እርሷን ስለተቀበለ ጌታችን ቸር፣ እኛን ስለማረ መሃሪ ተብሏል፡፡ እኛን ሃጥአንን ስትምረን ያን ጊዜ መሃሪ ትባላለህና አንዳለ ቅዳሴአችን፡፡

@Agape_ze_orthodox
@Agape_ze_orthodox
396 viewsእግዚአብሔር ፍቅር ነው, 20:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 00:05:56 ወዳጆቼ ሰው አለባበሳችሁን ተመልክቶ ተመችቷቸዋል ይላችኋል ማንም የማያይላችሁን የተሸከማችሁትን ሸክም ግን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያውቀዋል።

ገጻችሁን ተመልክተው ውበቱን ደፍቶባችኋል ይላችኋል። በጓዳ የምታፈሱትን እንባ ግን መድኃኔዓለም ያውቅላችኋል።

ማንም ደርሶ የማይነካላችሁን የችግራችሁን ስምጥ ሸለቆ ጠልቆ የሚነካላችሁ፤ ሸክማችሁን የሚያንከባልላችሁ፤ እንባችሁን የሚያብስላችሁ አማኑኤል አለ።

እርሱ የተሰበረ ልብን፣ የተሰበረ ህልምን፣ የተሰበረ ሕይወትን ይፈውሳል። እመኑት መቼም አይጥላችሁም።

@Agape_ze_orthodox
@Agape_ze_orthodox
650 viewsቀራንዮ, 21:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 18:47:48 ሰላም ለሁላችሁ፦ የሰማይ አባታችሁን እስቲ አስቡት። ምን ያህል እንደሚገነዘባችሁ ምን ያህን ለስሜታችሁ ቅርብ እንደሆነ ልትገምቱ አትችሉም። ድሮ ሳይሰራችሁ ብርታታችሁንና ድካማችሁን ያውቅ ነበር። በጎ ፍጻሜእችሁን ስላየ ወደዚህ አለም አመጣችሁ። ሳትጸልዩ ይሰማችኃል። የሞታችሁን ጦስ መስቀል ላይ ከፍሎላችኃል። ደሙ የተከፈለላችሁ እንደሆነ ይናገራል። በድንብ ትገቡታላችሁ። ስለእናንተ አልገባኝም ብሎ አይልም። ስለራሱ የሚያስረዳው ማነው? በጸሎቱ ችግሩን ለማብራራት የሚሞክርስ? ለእርሱ የመፍትሄ መንገድ የሚያሳየው፣ እንዲህ አርገህ ብትረዳኝ እያለ ሊመክረው የሚችል ከመሃላችሁ ማን ነው? ጸጉራችሁን የቆጠረ የአሻራችሁን ማህተም የቀረጸ እርሱ ሆኖ ሳለ አታውቀኝም የሚለው ማነው? እርሱ የእናንተ ብቻ ነው።እናንተም የእርሱ።
እባካችሁ ለሌሎች አካፍሉት

@Agape_ze_orthodox
@Agape_ze_orthodox
915 viewsቀራንዮ, 15:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 23:46:58
919 viewsእግዚአብሔር ፍቅር ነው, 20:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 11:11:25 ኢየሱስ ጌታ ነው ሮሜ 10፡9
ቤተክርስቲያን ከምታከብራቸው አበይት በዓላት አንዱ ደብረ ታቦርን ነው፡፡ ደብር ተራራ ማለት ሲሆን፤ የታቦር ተራራ ማለት ነው ሲተረጎም፡፡ ቀኑ በዓለ ኢየሱስ ነው፡፡ በእርግጥም ጌትነቱ የሚነገርበት ቀን ነው፡፡ጎልጎታ መድኃኒትነቱና ሰው በመሆን ቤዛ መሆኑን ያሳየበት ተራራ ሲሆን፣ ታቦር ጌትነቱ የታየበት ተራራ ነው፡፡ ሦስቱን ደቀ መዛሙርት ይዞ ተራራ መውጣቱ ጌትነቱን ያሳያል፡፡ የእግዚአብሔር ክብር በተራራ ሲገለጥ ኖሯል፡፡ በብሉይ ኪዳን በኮሬብ፣ በቀርሜሎስ፣ በሞርያ እንዲሁ በአዲስ ኪዳን በቆሮንቶስ፣ በደብረ ዘይት፣ በጽዮን፣ በታቦር ተራራ ከፍ ያለ ጌትነቱን ሲያሳይ ኖሯል፡፡ ዛሬም እጃቸውን ይዞ እንዲኖር ለሚፈቅዱ ወደ ከፍታ ተራራ ህይወታቸውን ይዞ ይወጣል፡፡ ፊቱ እንደ ጸሐይ ማንጸባረቁ ማንም በማይቀርበው ብርሃን የሚኖር ጌታ መሆኑን ያሳየበት መገለጥ ነበር፡፡ ልብሱ እንደ መብረቅ በሆነ ጊዜ ብርሃን የለበሰ የብርሃናት አዛዥ፣ የመላእክት አዛዥ እርሱ እንደሆነ ታወቀ፡፡ ከሙታን መሃል ሙሴን፣ ሳይሞቱ ከተነጠቁ ቅዱሳን ኤልያስ አጠገቡ ቆመው በታዩ ጌዜ፤ በእርግጥም ኢየሱስ የጠራቢው የዮሴፍ ልጅ ሳይሆን የህያዋንና የሙታን ጌታ እንደሆነ ታወቀ፡፡ እነ ቅዱስ ጴጥሮስ በድንጋጤ እንደ ሞተ ሰው በሆኑ ጊዜ ዳስሶ ተነሱ ማለቱ ወደ ፊት ከሙታን የሚጠራን ትሳኤያችን እንደሆነ ታየ፡፡ በክብር ደመና ውስጥ አብ የምወደው ልጄ በማለቱ የዮሴፍ ልጅ ሳይሆን ጌታ የሆነው የአብ ልጅ እርሱም ጌታ እንደሆነ ሰማን፡፡ ደመና ወርዶ የሚከበው፣ በደመና መሃል የሚራመድ የልዑል ልጅ ኢየሱስ በታቦር ተራራ ጫፍ ቆሞ ታየ፡፡ የዛሬ በዓል ለዓለም ሁሉ ኢየሱስ ጌታ እንደሆነ ሲናገር ይውላል፡፡ በዓመታት መካከልም ይህን ሲመሰክር ይኖራል፡፡ እንኳን አደረሳችሁ፡፡
ዘማሪ ቀሲስ አሸናፊ ገ/ማርያም

@Agape_ze_orthodox
@Agape_ze_orthodox
1.2K viewsእግዚአብሔር ፍቅር ነው, 08:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-17 12:08:40 የደብረ ታቦር መዝሙር ለመትፈልጉ ይህን የመዝሙር ቻናል ይቀላቀሉ

https://t.me/ortohodox_new_mezmur
1.2K viewsⒷaⒷa, 09:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-15 00:11:10 ጫፉን ልቀቁት

       ተንበርክከን ጌታ ሆይ ያስጨነቀኝን ችግር ከኔ ውሰድ ብለን ለእግዚአብሔር ጫፉን እናሲዘዋለን፤ የችግሩን ጫፍ ግን እኛም አንለቀውም።

      ለእግዚአብሔር የሰጣችሁት የተበላሸባችሁ ነገር ቢኖር ልቀቁት ጫፍ ይዛችሁ አትጓተቱ፤ የሞተብሽ ነገር ቢኖር ለእግዚአብሔር ልቀቂለት ጫፍ ይዘሽ አትጓተቺ እንደ አልዓዛር ያስነሳዋል፤ የታመመብህን ነገር ለእግዚአብሔር ተውለት እርሱ ይፈውሰዋል።

@Agape_ze_orthodox
@Agape_ze_orthodox
1.3K viewsእግዚአብሔር ፍቅር ነው, 21:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-09 23:49:42 መልካምነት !

አንዳንድ ሰዎች መልካም የሚሆኑት መልካም ለሆነላቸው ሰው ብቻ ነው። እንደ ክርስቲያን መልካምነት ሰዎች እንደምንፈልገው ስለሆኑልን የምንሰጣቸው ሽልማት ሳይሆን እኛ በዳግም ልደት የሆነው ማንነታችን ነው። ኢየሱስን ወደ መምሰል ስናደግ ጸባያችን በሰዎች ጸባይ መወሰኑ ይቀራል። ይሄ ማለት ለደጎች ብቻ ደግ ለክፉዎች ክፉ መሆን እናቆማለን። ይልቁኑ ማንነታችን በመንፈስ ቅዱስ ቁጥጥር ውስጥ ይገባና መልካችን የሰዎችን መልክ ሳይሆን የልጁን የኢየሱስ ክርስቶስን መልክ ይመስላል። ያኔ ለማያስቡልን ማሰብ የሚጠሉንን መውደድ ለሚያሳድዱን መጸለይ እንጀምራለን።

የልጁ መልክ በመልካችን ላይ ይድመቅ።

@Agape_ze_orthodox
@Agape_ze_orthodox
1.8K viewsእግዚአብሔር ፍቅር ነው, 20:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-08 00:04:11 እንኳን ለፍልሰታ ጾም / በሰላም አደረሳችሁ !!

ጾም ለመንፈሳዊው ዓለም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ነው ። በእግዚአብሔር ፊት ቊርጥ ልመናን ለማቅረብ ፣ እውነተኛ ንሰሐን ለመፈጸም ፣ የዕንባ መሥዋዕትን ለማቅረብ ፣ በትሕትና ጸጋን ለመቀበል ጾም አስፈላጊና ግዴታ ነው ። 

ጾም አዋጅና በአዋጅ ሊደረግ የሚገባው ነው ። በስውር የሚደረግ ጾም አለ ። ግለሰቡ ጉዳዩን ለእግዚአብሔር የሚያቀርብበት ፣ መጾሙንም የማያሳውቅበት ነው ። የማኅበር ጾም ግን በአዋጅ የሚደረግ ፣ ስለ አገርና ስለ ወገን የእግዚአብሔር ማዳን የምንጠባበቅበት ነው ። ጾምን ሰው ለራሱ ያውጃል ፣ ቤተ ክርስቲያንም ታውጃለች ።

ጾም ራሳችንን በእግዚአብሔር ፊት የምናዋርድበት ነው ። በተሰበረ ልብ የሚቀርብ ልመና ግዳጅን ይፈጽማል ። ፈጽሞም መልስ ያገኛል ። ጾም ለትሑት ጸሎት እጅግ ይረዳል ። ሥጋን በማድከም ወደ ነፍስ ልዕልና የምናቀርብበት ምሥጢር ነው ። ጾም የርኅራኄ መገኛ ፣ የዕንባ ምንጭ ፣ የትሕትና መፍለቂያ ናት ። ራሳችንን በጾም ስናዋርድ እግዚአብሔር ከፍ ያደርገናል ፣ ምሪትን ይሰጠናል ። (ዕዝ. 8÷21) ።

ጾም አዋጅን የሚሽር አዋጅ ነው ። በመጽሐፈ አስቴር ላይ እንደምናነበው በአይሁድ ላይ የታወጀው የሞት አዋጅ ወደ ሹመትና ክብር የተለወጠው በጾምና በጸሎት ነው ። (አስቴ. 4÷3) ። የተዘጉ ደጆች እንዲከፈቱ ፣ በአገር በወገን ላይ የመጣ የክፉ አዋጅ ማለት ሞት ፣ መከራ ፣ በሽታ እንዲወገድ ጾም ጸሎት ትልቅ መሣሪያ ነው ። የጾምና የጸሎት ትጥቅ አይታይም ፣ የሚታየውን ጠላት ግን ያሸንፋል ።

ጾም ይቅር ብለን ይቅርታ የምንለምንበት ነው ። እግዚአብሔር ከመሥዋዕት ይልቅ ምሕረትን (ይቅርታን) ይወዳል ። በጾም በጸሎት የእግዚአብሐር ይቅርታ ስንለምን ይቅር እያልን ፣ በረከቱን ስንለምን ለተራቡት እያበላን ሊሆን ይገባዋል ። አማኝ ከጫጫታ ስፍራ ገለል ብሎ ፣ ከዘፈን ይልቅ ዝማሬን መርጦ ፣ ከወሬ ይልቅ በጸሎት ተጠምዶ እንዲባረክ ጾም ቀስቃሽ ደወል ነው ።

ዘፈንና ዝሙት እንዲሁም ስካር በአገር ሲበዛ ቀጥሎ ትልቅ ጥፋትና ልቅሶ ይኖራል ።  "የዘፈን ቤት ሳይፈርስ አይቀርም" እንዲሉ ዘፈን ሲበዛ መጾምና ማልቀስ ይገባል ። እግዚአብሔር የሚፈልገው ጾሞ የበሬ ሥጋን ብቻ ሳይሆን ከሰው ሥጋም እንድንርቅ ነው፡፡ ያለ ቢላዋ በሐሜት የሰውን ሥጋ መብላት ጾምን እንደ መግደፍ ነው ። ሠራተኞቻችንን እያስለቀስን ፣ ደመወዛቸውን እየበላን ፣ ቂምን በልባችን ሞልተን የምንጾመው ጾም የረሃብ አድማ እንጂ ጾም አይባልም (ኢሳ. 58 ÷ 5-6) ። የጾም መሰናዶው ነጠላን ማጽዳት ሳይሆን ልብን ማጽዳት ፣ በልኳንዳ ቤት ደጆች መሰለፍ ሳይሆን ንስሐ መግባት ፣ ዕቃን ማጣጠብ ሳይሆን ከቂም መጽዳት ነው ። የጾምን መረቁን እንጂ ሥጋውን አልበላንምና ከንቱ ልፋተኞች ሆነናል ። ምክንያቱም ለጾማችን የምናደርገው ዝግጅት ሜዳዊ እንጂ ውስጣዊ አይደለምና ። ትልቁ ጾም ከኃጢአት መከልከል ነው ። ቅበላና ፍቺ የሌለው ጾም ኃጢአት ነው ። በአገራችን በጾም መግቢያ መውጫ ስካርና ዝሙት ይደራል ። ቅበላውና ፍቺውም በኃጢአት በመሆኑ ከጾም የሚገኘውን በረከት ማግኘት አልቻልንም ።

ጾም ለእግዚአብሔር እንጂ ለታይታ አይደለም ። (ዘካ. 7÷5) ። ከማኅበረሰቡ ላለ መለየት ፣ ሆዳም ላለ መባል ፣ ዶሮ ለመባረክ መጾም ከንቱ ጾም ነው ። የምንጾመው ከእግዚአብሔር ዋጋ ለማግኘት እንጂ ጾመኛ ለመባል መሆን የለበትም ። የጾምና የጸሎት ዋጋ ያለው ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው ። በጾም አፌ ክፉ አታናግሩኝ ለማለት መጾም አይገባንም ። ባንጾምም ክፉ መናገር አይገባንም ። በጾማችን የሚታየን እግዚአብሔር ነው? ራሳችንን መጠየቅ ይገባናል ።


ጾም እውነትና ሰላም ያለበት ነው ። በጾማችን ወራት ከድሆች ጋር ማሳለፍ ብድር መመለስ ለማይችሉ ቸርነት ማድረግ ይገባል ። እኩዮችን ሲጠሩ መኖር እውነተኛነት አይደለም ። ከእኛ ባነሰ ኑሮ ለሚኖሩት እጅን መዘርጋት ግን የጾም መገለጫው ነው ። ጾም ሁለት እጆች አሏት ። አንደኛው የጾም እጅ ጸሎት ፣ ሁለተኛው የጾም እጅ ምጽዋት ነው ። ጾም ሁለት አንደበት አሏት፡፡ አንደኛው ቃላችን ሲሆን ሁለተኛው ዕንባችን ነው ። ጾም እውነትን ትፈልጋለችና ለተጨቆኑ ምስኪኖች ፣ ፍርድ ለተጓደለባቸው እስረኞች ፣ በግፍ ከገዛ አገራቸው ለሚሰደዱ አቤት የምንልበት ፣ ግፍ አድራጊዎችን በቃችሁ ብለን የምንገስጽበት የእውነት ሰይፍ ነው ። ጾም ሰላም ስለሆነ ግለሰብ ከግለሰብ ፣ ማኅበራትን ከማኅበራት ፣ አገር ከአገር ጋር የሚታረቁበት ፣ እንዲታረቁም ጥረት የምናደርግበት ሊሆን ይገባዋል ። እርቅን የጠሉና የገፉ ጾምን የማወጅ አቅም የላቸውም ። ስለዚህ ታርቀው የሚያስታርቁበት እንዲሆን ሊያስቡ ይገባቸዋል ። የጾም የመጨረሻው ውጤት ወይም በዓሉ እግዚአብሔር በሚሰጠን መልስ ሆታና ደስታ ነው ። መልስ እንዲመጣ ግን እውነትና ሰላም መርጋት አለባቸው ። ግፈኞች ፣ የሌላውን ድርሻ እየነጠቁ የሚበሉ ፣ ለሀብታም እያደሉ ለድሃ የሚፈርዱ ሊገሰጹ ፣ ንስሐ ሊገቡ ይገባል ። ያ ሲሆን የጾም ዳርቻው ተድላና ደስታ ይሆናል ። (ዘካ. 8÷19) ።

የነነዌ ሰዎች ምሕረትን የተቀበሉት በሦስት ቀን ጾምና ጸሎት ነው ። የመጣው መዓት የተመለሰው ፣ የራቀው ምሕረት የቀረበው በአንድ ልብ ሆነው አቤት በማለታቸው ነው ። እኛ ግን ዓመት ሙሉ እየጾምን ለምን በረከት ራቀን ብለን ጠይቀን አናውቅም ። ስለዚህ የፍስለታ ጾም ስንጾም፡-

1.  ርዕስ ልንይዝ

2.  ይቅር ልንባባል

3.  ንስሐ ልንገባ ይገባናል ።

ብዙ አንገብጋቢ ርዕሶች አሉን ። የቤተ ክርስቲያን ለሁለት መክፈል ፣ እርቅን የማይወዱ ሰዎች መሙላታቸው ፣ በአገር ያለው የኑሮ ውድነት ፣ ድሆች በደንብ እየደኸዩ መሆናቸው ፣ ፍትሕና ፍቅር መጥፋቱ ፣ የገንዘብ ጣኦት በምድራችን መቆሙ ፣ የዝናብ መታጣት ፣ የበሽታ መበርከት ፣ የአንድነት መጥፋት ፣ የትዳር መናጋት ፣ የልጆች ዋልጌነት ፣ የሐሰት መምህራን መብዛት ፣ እግዚአብሔርን መርሳት……. ይህ ሁሉ የጾምና የጸሎት ርዕሳችን ነው ። ክርስቲያን መንፈሳዊ ኃይልን አጥቷል ። በየደረሰበት ውጊያ አሸናፊ ሳይሆን ተሸናፊ ሆኗል ። ይኸውም፡-

·   ቃሉን ስለማያጠና

·   የጸሎት ሰዓቱ ስላልተከበረ

·   ጾምና ጸሎትን ስለተወ

·   ምጽዋትን ስላስቀረ

·   የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሔር መስጠት ስላልቻለ …. ነው ።

በእውነት ጾመን በዓሉ ተድላ እንዲሆን ፣ በጾም ዘርተን በፈውስ እንድናጭድ እግዚአብሔር ይርዳን ። 
ምንጭ:—

እባካችሁ ለሌሎች አጋሩ

ይቀላቀሉ ➙ @hiyaw_qal
ይቀላቀሉ ➙ @hiyaw_qal
1.7K viewsእግዚአብሔር ፍቅር ነው, 21:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ