Get Mystery Box with random crypto!

AFZAN MEDIA / አፍዛን ሚዲያ

የቴሌግራም ቻናል አርማ afzanmedia — AFZAN MEDIA / አፍዛን ሚዲያ A
የቴሌግራም ቻናል አርማ afzanmedia — AFZAN MEDIA / አፍዛን ሚዲያ
የሰርጥ አድራሻ: @afzanmedia
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 506
የሰርጥ መግለጫ

አላህን በደስታህ ጊዜ ተዋወቅ በችግር ጊዜ ያውቅሀልና!!!

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-10 10:17:26 ዒድ ሙባረክ ስትባሉ መልሱ ግራ ለሚገባቹ :-

1 مبارك علينا وعليك
2 يبارك فيك ربي
3 علينا وعليك يتبارك
4 الله يبارك فيك
5 الله يطرح البركة في اعيادنا
6 الله يعديه علينا بالبركات
7 عقبال مليون عيد
8 كل عام وأنت بخير
9 كل عام وأنت طيب
……
በስኩን/ሳኪን ሲያልቅ ለወንድ በከስራ ሲያልቅ ለሴት ይሆናል።

1 ሙባረክ አለይና ወአለይክ/ወአለይኪ
2 ዪባሪክ ፊክ/ፊኪ ረቢ
3 አለይና ወአለይክ/ወአለይኪ የተባረክ
4 አሏህ ዪባሪክ ፊክ/ፊኪ
5 አሏህ የጥረሁ አልበረከተ ፊ አዕያዲና
6 አሏህ ዩዓዲይሂ አለይና ቢል በረካ
7 ዒቅባል ሚሊዩን ዒድ
8 ኩሉ አመ ወአንተ/ወአንቲ ቢኸይር
9 ኩሉ አም ወአንተ/ወአንቲ ጠይብ

@afzabmedia
367 views07:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 07:36:40 የዒድ ትዝብት
=
================

በቅድሚያ ሰላቱን ጨምሮ ሙሉ ስርአቱ እንዲያምርና እንዲሰምር የበኩላቸውን ያደረጉና የሚያደርጉ ሁሉ ሊመሰገኑ እንደሚገባ ግልፅ ነው፤ በተለይ በአንዳንድ ቦታዎች ካለፉት አመታት የተሻሉ መስተንግዶዎችና ቅንጅቶች መኖራቸው አስደሳች ነው። ይህ በእንዲህ እንዳለ፦

1/ ሰዎች ኹጥባውን እንዲሰሙ ለማድረግ በመጓጓት ኹጥባውን ማድመጥ ግዴታ እነደሆነ አድርጎ ማቅረብ ትክክል አይደለም፤ "ዋጂብ" የሚለው ቃል ከአፍ ባይወጣ እንኳ ከመጠን ያለፈ ግፊትና ጫና ማሳደር ከረሱላችን ፈቃድ ጋር አይገጥምም።
عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ السَّائِبِ، قَالَ: شَهِدْتُ مَعَ رَسُولِ اللَّهِ - صلى الله عليه وسلم - الْعِيدَ، فَلَمَّا قَضَى الصَّلَاةَ، قَالَ: " إِنَّا نَخْطُبُ، فَمَنْ أَحَبَّ أَنْ يَجْلِسَ لِلْخُطْبَةِ فَلْيَجْلِسْ، وَمَنْ أَحَبَّ أَنْ يَذْهَبَ فَلْيَذْهَبْ " أخرجه أبو داود والنسائي وابن ماجه.
«ዐብዱላህ ኢብኑ አስ-ሳኢብ እንዲህ አሉ፦ ከአላህ መልእክተኛ ጋር በዒድ ተገኝቻለሁ፤ ሰላታቸውን እንደጨረሱ እንዲህ አሉ፦ "እኛ ኹጥባ እናደርጋለን፤ ለኹጥባው መቀመጥ የፈለገ ይቀመጥ፤ መሄድ የፈለገም ይሂድ።"»
[አቡ ዳዉድ (ቁ 1155)፣ አን-ነሳኢይ (ቁ 1571)፣ ኢብኑ ማጀህ (ቁ 1290)]

ሰዎች ግዴታ ያልሆነባቸውን ተግባር እንዲሰሩ ለማድረግ የሚቀየር ህግ ሊኖር አይችልም። መርዋን ኢብኑ'ል-ሐከም የተባለው ኸሊፋ የዒድን ኹጥባ ከሰላቱ በፊት ያስቀደመው "ሰዎች እንደ ቀድሞው ( ኹጥባውን ለማድመጥ) አይቀመጡልንም!" በሚል መነሻ ቢሆንም ከአቡ ሲዒድ አል-ኹድሪይ እና ከሌሎች ተቃውሞ ገጥሞት ነበር። (አል-ቡኻሪ ቁ 956 እና ሙስሊም ቁ 889)
ኢብኑ ተይሚያ ለዚህ የመርዋንና የመሰሎቹ ተግባር ምላሽ ሲሰጡ ያለማድመጣቸው መንስኤ የራሱ ማጓደል እንደሆነና መልእክተኛው ያደርጉ እንደነበረው ለህዝቡ መድህን የሚጠቅም ምክር በማስተላለፍ ፈንታ ስልጣኑን የሚያስጠብቅበትን ንግግር በመደስኮሩ ወይም ለዲናቸው አስቦ ቢሆን እንኳ የሚጠቅማቸውን ቁም ነገር ባለማስተማሩ እንደሆነ ጠቅሰው ከዚያ ባሻገር ደግሞ አላህ ስለስራው እንጂ ስለሌሎች ስራ እንደማይጠይቀው አወስተዋል።
[ኢቅቲዷኡ'ስ-ሲራጢ'ል-ሙስተቂም (2/104)]

2/ ኹጥባውን ማዳመጥ "ግዴታ አይደለም" ማለት እንደፈለጉ በማውራትና ግርግር በመፍጠር የሚያደምጡትን "ማወክ ይቻላል" ማለት አይደለም። ስለዚህ ወይ ማዳመጥ፤ ወይ ደግሞ ሳይረብሹ ውልቅ ማለት!

3/ ኹጥባው ብዙሃኑ በሚረዱት ቋንቋ ቢሆን ምናልባት ብዙ ሰው ለማድመጥ የተሻለ ፍላጎት ያድርበት ነበር።
በአቡ ሐኒፋ መዝሀብ ኹጥባ በዐረብኛ መሆኑ በጥቅሉ ግዴታ አይደለም∷ አንዳንድ የሻፊዒያ መዝሀብ ሊቃውንትና ሌሎች ታዋቂ ምሁራን ይህንን አቋም ይጋራሉ∷ ሁሉም ታዳሚ ዐረብኛ የማይረዳ ከሆነ ደግሞ በሻፊዒያህና በሐናቢላህ መዝሀብም ጭምር በሚያውቁት ቋንቋ መኾጠቡ ይፈቀዳል∷
የኹጥባ አላማ መልእክትን ማስተላለፍ ነውና የዐረብኛ ቋንቋ ተናጋሪ ባልሆኑ አገራት በአገርኛው ልሳን ኹጥባውን ማስተላለፍ መፈቀዱ አለም አቀፉ የፊቅህ ጉባዔ፣ የሳውዲው ቋሚ የፈትዋ ኮሚቴና ሌሎች የዘመናችን የዒልም ተቋማትና በርካታ ምሁራን የመረጡት አቋም ሆኗል∷

4/ ሰዎች ኹጥባውን እንዳይሰሙ ተፅእኖ የሚያደርጉ ምክንያቶች አሉ፤ ለምሳሌ፦
- የድምፅ ማጉያ ሲስተም በአንዳንድ ቦታዎች አለመስተካከሉ
- የኹጥባው መርዘም
- ከኹጥባው በፊት ሌሎች ንግግሮች መኖራቸው (መልእክተኛው ከሰላት በፊት የሚያደርጉት ወይም የሚያስደርጉት ንግግር አልነበርምና!)

5/ የዒድ ሰላት በየቦታው የሚሰገድበትን ሰዓትና ደቂቃ አስቀድሞ በሚዲያ ማሳወቅ ብዙ አገሮች ላይ የሚሰራበት ጥሩ ልምድ ነው። ሰዎች አስቀድመው እንዲዘጋጁና ሰላቱ እንዳያመልጣቸው ያግዛል።

6/ ህዝቡ አስተናጋጆችን ቢታዘዝ ብዙ የሰልፍና የቦታ ችግሮች ባልኖሩ ወይም ቢኖሩም ባልተወሳሰቡ ነበር።

7/ አስተናጋጆች በተቻላቸው መጠን ትእግስትንና መልካም ባህሪን የተላበሱ ሊሆን ይገባል፤ ንግግራችውም በትህትና ቢሞላ መልካም ነው - በተለይ በድምፅ ማጉያ መልእክት የሚያስተላልፉ ወንድሞች!

መልካም ዒድ

تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال ustazilyas

@afzanmedia
72 views04:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 11:15:33 "ጥቁር_ኮት_አልብሱኝ" ===============
(በእለተ አረፋ የተፈፀመ አሳዛኝ ታሪክ)

ወደ ሞት አደባባይ እየተነዱ ነው። ሊገደሉ። ከኃላቸው ሆኖ ወደ ሞት አደባባይ ለሚነዳቸው ሰው እንዲህ አሉት "ጥቁር ኮት አልብሱኝ"። አመጡላቸውና እየለበሱ ለምን ጥቁር ኮት መልበስ ፈለጉ? ተብለው ስጠየቁ "እንደምታዩት አከባቢው እጅግ ብርዳማ ነው። ይሄ በኔ ሞት ሊደሰት የተሰበሰበ ህዝብ ብርዱ ስያንቀጠቅጠኝ አይቶ ሞት ፈርቶ ነው የሚንቀጠቀጠው እንዳይለኝ ሰውነቴን ማሞቅ ስለፈኩ ነው" ብለው መለሱላቸው።

April 28, 1937 ተወለዱ። በ1979 የሀገሪቱ 5ኛው ፕሬዝዳንት ሆነው በመመረጥ ለ24 ዓመታት ሀገራቸውን በፕሬዝዳንትነት አገልግለዋል።

በ24 ዓመታት የስልጣን ቆይታቸው ወቅት ሀገራቸው በጦር ሃይል እና በኢኮኖሚ ምዕራባዊያን ሀገራትን የምትገዳደር ሀገር ወደ መሆን አሸጋገሯት።

እሳቸው የገነቧት አገር ምዕራባዊያንን ከመገዳደር ባሻገር ምዕራባዊያን በመካከለኛው ምስራቅ ለሚከተሉት የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ እና ብሔራዊ ጥቅማቸው ጋሬጣ ልትንባቸው እንደምችል እርግጠኛ ሆነዋል።

ስለሆነም እሳቸው መወገድ ነበረባቸው። የሚያስወግዱበትን ሰበብ ፈለጉ። ቀላል ነበር ይህ ሰው "#ኒውክሌር_ቦንብ_ታጥቋል" በሚል ተራ ክስ እ.አ. አ 2003 ከስልጣን እስወገዷቸው።

በኢኮኖሚ የምዕራባዊያን ተገዳዳሪ የነበረች ሀገር በምዕራባዊያን ወረራ ተዘርፋ እንዳልነበረች ሆነች። ሞኙ ያገሬው ሕዝብም በሳቸውን ከስልጣን መውረድ ሀገራቸው ምድረ ገነት የሆነች ያልህ ጨፈሩ።

ያገረውን ህዝብ በዚህ ያህል መጨፈርና መደሰት የተገነዘቡት ምዕራባዊያን "ለምን የዚህን ህዝብ ደስታ ላይ ደስታ አንደርብላቸውም" በማለት Decmber 30, 2006 #በእለተ_አረፋ በአደባባይ በስቅላት ገደሏቸው።

እሳቸው በህዝባቸው ፊት ያውም በእለተ አረፋ በአደባባይ እንደተሰቀሉት ሁሉ ዛሬ ላይ ሀገራቸውና ህዝባቸው በዓለም ፊት የደሃ ደሃ ተብለው ከተመዘገቡት ሀገራት ተርታ ሆነዋል። በየእለቱም በአገሪቱ በተፈለፈሉ አሸባሪ አካላት በዓለም አደባባይ ይሰቀላሉ።መሪህን በስሜት አሳልፈህ አትስጥ።

እኚህ ሰው ማናቸው!?!?!?
( ሁሴን አብደላ ሁሴን)

ለመላው የእስልምና ተከታዮች መልካም የአረፋ በዓል በድጋሜ ኢድ ሙባረክ እንኳን አደረሳችሁ

@afzanmedia
90 views08:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 11:15:27
"ጥቁር_ኮት_አልብሱኝ" ===============
(በእለተ አረፋ የተፈፀመ አሳዛኝ ታሪክ)

ወደ ሞት አደባባይ እየተነዱ ነው። ሊገደሉ። ከኃላቸው ሆኖ ወደ ሞት አደባባይ ለሚነዳቸው ሰው እንዲህ አሉት "ጥቁር ኮት አልብሱኝ"። አመጡላቸውና እየለበሱ ለምን ጥቁር ኮት መልበስ ፈለጉ? ተብለው ስጠየቁ "እንደምታዩት አከባቢው እጅግ ብርዳማ ነው። ይሄ በኔ ሞት ሊደሰት የተሰበሰበ ህዝብ ብርዱ ስያንቀጠቅጠኝ አይቶ ሞት ፈርቶ ነው የሚንቀጠቀጠው እንዳይለኝ ሰውነቴን ማሞቅ ስለፈኩ ነው" ብለው መለሱላቸው።

@afzanmedia

72 viewsedited  08:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 22:49:52
እንኳን ለ1443ኛው የኢድ አል አደሃ አረፋ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን። ኢዱን ሰዒድ ተቀበለላሁ ሚና ወሚንኩም ሷሊሁል አዕማል! ኢድ ሙባረክ!

@afzanmedia
80 viewsedited  19:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 22:10:15
. 人 ★* 。 • ˚* ˚
. (__) *ዒድ ሙባረክ* ★
. ┃口┃ *Éid Al Adha *
. ┃口┃★ *መልካም በዐል *˛•
. ┃口┃★ 。* •★ 。•˛˚˛*
. ┃口┃ •˛˚˛* 人 •˛˚ *
. ┃口┃ .- :'''"''''"''.-.
. ┃口┃ (_(_(_()_)_)_)
┃口┃_┃∩∩∩∩∩∩┃
. ┃. ┃_┃∩∩∩∩∩∩┃
. 三_||三三三三三三 三|
... U and ur family....
4all

...Eid Mubarek..

كل عام وانتم بخير
هلا اى يوم العيد
#ለመላው ቤተሰብዎ ለወዳጅ ዘመድዎ መልካም በዐል ይሁንላቹ ዘንድ ተመኘሁላቹ


#1443 ዓ.ሂ
@afzanmedia
77 views19:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 22:08:59
የአዲስ አበባ ፖሊስ ለዒድ አል አድሃ በዓል ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን ይፋ አደረገ

ሐምሌ 1/2014 (ዋልታ) የአዲስ አበባ ፖሊስ በነገው ዕለት ለሚከበረው 1 ሺሕ 443ኛው የዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን ይፋ አደረገ፡፡

1 ሺሕ 443ኛው የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ የፀጥታና የደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል አፈስላጊውን ዝግጀት አጠናቆ ወደ ሥራ መግባቱን አስታውቋል፡፡

የኢድ ሶላት ተጀምሮ እስከሚጠናቀቀ የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑም ነው የገለጹት፡፡

ለበዓሉ አከባበር ሀገራችን ካለችበት ወቅታዊ ሁኔታ አንፃር ልዩ ዝግጅት ከመደረጉም ባሻገር ከእምነቱ አባቶችና ከፈቃደኛ ወጣቶች ጋር በበዓሉ አከባበር ዙሪያ አስቀድሞ ተገቢውን ውይይት በማድረግ ዝግጅት መደረጉ ተገልጿል፡፡

የበዓሉ ታዳሚዎች በየአካባቢያቸው በዓሉን ሲያከብሩም ሆነ ወደ ሶላቱ ሲመጡ እንደወትሮው ሁሉ የፀጥታ ኃይሉን መስተንግዶና ትዕዛዝ በማክበር ተባባሪ እንዲሆኑ የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

ህብረተሰቡ ለፀጥታው ስራ ስኬታማነት እያደረገ ላለው ቀና ትብብር ግብረሃይሉ ምስጋናውን እያቀረበ ትብብሩ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪውን አስተላልፏል፡፡

ከፀጥታ ጋር ተያያዥ መረጃ ወይም ጥቆማ ለመስጠት በ991 ወይም 816 ነፃ የስልክ መስመሮችን እና 01- 11 -11- 01 -11፣ 01- 11- 26- 43- 59፣ 01- 11- 01- 02- 97፣ መጠቀም እንሚቻል ገልጿል።

በዓሉን አስመልክቶ የሚካሄደው የሶላት ፕሮግራም ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር ፡-

ከቦሌ አየር መንገድ ፣ በሚሊኒዬም አዳራሽ ወደ ለገሃር የሚወስደው መንገድ ደንበል ሲቲ ሴንተር ወይም ኦሎምፒያ

@afzanmedia
78 views19:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 22:11:10
ነገ አረፋ ነዉ።

[የነገዋን ቀን የፆመ ያለፈዉንም
የሚመጣውንም አመት ወንጀል ያስምራል።]ብለዋል
ነብዩ ሙሐመድ ﷺ

ነገ አረፋ 9ኛው የዙልሂጃ ቀን በፆም በዱዓ በተውበት ልናሳልፈው ይገባል ሊያልፈን አይገባም ።

@afzanmedia
96 views19:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 22:08:25
"ምርጥ ዱዐ የአረፋ ቀን ዱዓ ነው"
"ከአረፋ ቀን ይበልጥ አላህ በርካቶችን ከእሳት ነፃ የሚያደርግበት ቀን የለም"
ረሱል ﷺ ﷺ ﷺ

@afzanmedia
80 views19:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 22:07:31 اللهم صلي وسلم وبارك على نبينا وحبيبنا محمد وعلى آله وصحبه أجمعين


@afzanmedia
73 views19:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ