Get Mystery Box with random crypto!

قناة الحق

የቴሌግራም ቻናል አርማ afterkhair — قناة الحق ق
የቴሌግራም ቻናል አርማ afterkhair — قناة الحق
የሰርጥ አድራሻ: @afterkhair
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 541
የሰርጥ መግለጫ

العلم:-هو معرفة الحق بدليل وضده الجهل ።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ننصح بسماعها ونشرها وبارك الله فيكم 📲

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-05 17:59:38 «የዐሹራእን ፆም የተመለከቱ የተወሰኑ ማስታዎሻዎች

የዐሹራእ ፆም የሚባለው እንደ ሒጅራ አቆጣጣር የመጀመሪያው የሙሐረም ወር በገባ በአስረኛው ቀን የሚፆም ፆም ነው።
ይህ ፆም እጅግ ከተጠኑ የሱና ፆሞች መካከል ከዋናዎቹ ነው።

وعن أبي قتادة -رضي الله عنه-، أنّ النّبي -صلّى الله عليه وسلّم- قال:
( صيامُ يومِ عاشوراء، أحتسب على اللَّه أنْ يُكَفِّرَ السّنة التي قبله ).
[أخرجه مسلم]

ከአቡ ቀታዳ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዙ ነብዩ (ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም)
"የዓሹራእ ቀን ፆም ከሱ በፊት የነበረውን ዓመት ወንጀል ያስምራል ብዬ በአላህ ላይ ተስፋ አደርጋለሁ" አሉ።

【ሙስሊም ዘግበውታል】

ዐብዱላህ ኢብኑ ዐባስ (ረዲየላሁ ዐንሁማ)
ሰለ ዐሹራእ ፆም ተጠይቀው እንዲህ አሉ :-
" ነብዩን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ከሌሎች ቀኖች አሰበልጠው የሚፆሙበትን ቀን ሲጠባበቁ ከዚህ ቀን ውጪ አላውቅም (የዐሹራእን ቀን ማለቱ ነው።) ወርን ሲጠባበቁ አላየሁም የዚህን ወር ያክል (የረመዳን ወር ማለቱ ነው።)
【ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል】

የዐሹራእ ቀን የሚባለው የሙሐረም 10 ኛው ቀን ነው።
የሙሐረምን 10 ኛውን ቀን በፆም ማሳለፍ ከላይ በሐዲሡ ላይ እንዳየነው ያለፈውን የአንድ አመት ወንጅል ያስምራል

ለሙስሊሞች እሄን ቀን በመፆም እራሳቸውን፣ልጆቻቸውን፣ቤተሰቦቻቸውንና ማሀበረሰባቸውን ሊያነሳሱ ይገባቸዋል።

ማሳሰቢያ:- ያለፈውን የአመት ወንጀል ያስምራል ማለት ትንንሹን ወንጀል ነው እንጅ ትልልቁን ሀጢአት አይደለም ትልቅ ወንጀል ዝሙት፣ህሜት፣ነገረኝነት፣ሪባ እና መሰል ትልልቅ ወንጀሎች መስፈርቱን ያሟላ እራሱን የቻለ ተውበት ያስፈልጋቸዋል።

በዚህ ቀን ወደአላህ ልንመለስ ካለፈው ወንጀላችን በአጠቃላይ ከትልቁም ከትንሹም በመፀፀት እውንተኛ ተውበትን ልንቶብት ይገባል። ተውበትን አላህ በማንኛውም ጊዜ ቢቀበልም በእንደዚህ ብልጫ ባላቸው ጊዜዎች ከሌላው በተለዬ ጊዜ ይቀበላል። በተለይ እኛ እንደሂጅራ አቆጣጠር አድስ አመትን እየጀመርን ስለሆነ ካለፈው ጥፋታችን በመመለስ በተረፈው በመስተካከል ወደአላህ ልንመለስ ይገባናል።

የዐሹራእ ፆም ምክኒያት:-

የዐሹራእን ቀን መፆም ሱና ሁኖ የተደነገገው አሏህ ሙሳንና ህዝቦቾዎን ከፊርዐውን ሰላም ያወጣበት ቀን እንዲሁም ፊርዐውንና ሰራዊቱን ያጠፋበት ቀን ስለሆነ አላህን ለማመስገን ነው።
ለዚህም ተብሉ ሙሳ(ዐለይሂ ሰላም) ይህን ቀን ፁመውታል አይሁዶችም ሙሳን ተከትለው ፁመውታል።እኛ ሙስሊሞች ሙሳን በመከተልና በሙሳ ሰላም መውጣት በጠላታቸው መጥፋት በመደሰት ከአይሁዶች የበለጠ የተገባን ነን

ከላይ የጠቀስኩት የዐሹራእ ፆም ምክንያት በዚህ ሐዲሥ ተገልፇል:-

عن ابن عباس ((قَدِمَ النَّبِيُّ -صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ- المَدِينَةَ فَرَأَى الْيَهُودَ تَصُومُ يَوْمَ عَاشُورَاءَ فَقَالَ مَا هَذَا؟ قَالُوا: هَذَا يَوْمٌ صَالِحٌ، هَذَا يَوْمٌ نَجَّى اللَّهُ بَنِي إِسْرَائِيلَ مِنْ عَدُوِّهِمْ فَصَامَهُ مُوسَى، قَالَ فَأَنَا أَحَقُّ بِمُوسَى مِنْكُمْ فَصَامَهُ وَأَمَرَ بِصِيَامِهِ)). 【صحيح البخاري】

ከኢብኑ ዐባስ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ:–
"ነቢዩ (ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) ወደ መዲና በገቡ ጊዜ አይሁዶች የዐሹራእን ቀን ሲፆሙ አዩዋቸው ነቢዩም (ለአይሁዶች) "ይህ (የምትፆሙት) ምንድነው?" አሉዋቸው ይህ ምርጥ ቀን ነው ይህ ቀን አላህ በኒ ኢስራኢሎችን ከጠላታቸው ሰላም ያወጣበት ቀን ነው። ስለዚህ ሙሳ ፆሞታል። አሉ ነቢዩም "እኔ ለሙሳ ከናንተ የበለጠ የቀረብኩኝ(የተገባሁኝ) ነኝ ብለው ፆሙት እንዲፆምም አዘዙ።"
【ቡኻሪ ዘግበውታል】

ከአስረኛው ቀን በስተፊት ያለውን ማለት የዘጠነኛውን ቀን አብሮ መፆም ይወደዳል

ኢብኑ ዐባስ(ረዲየሏሁ ዐንሁ) እንዲህ ይላሉ:-
"ነቢዩ (ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) ዐሹራእን በፆሞና እንዲፆምም ባዘዙ ጊዜ (ሱሐቦች) የአላህ መልእክተኛ ሆይ እርሱኮ አይሆዶችና ነሷራዎች የሚያከብሮት ቀን ነው አሏቸው። ነቢዩም (ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) «አሏህ ካለ በቀጣይ አመት የዘጠነኛውን ቀን እንፆማለን» አሉ (ኢብኑ ዐባስ) "የቀጣዩ አመት አልመጣም ነቢዩ(አለሂሶላቱ ወሰላም) የሞቱ ቢሆን እንጅ" አለ
【ሙስሊም ዘግበውታል】
ስለዚህ ለዚህ ሐዲሥ ሲባል ዘጠነኛውን ቀን ከአስረኛው ጋር አብሮ መፆም ይወደዳል

« አስረኛውን ብቻ በፆም መለየት ከአይሁድ ጋር እንዳይመሳሰል ከሙሐረም ዘጠኝና አስርን አብሮ መፆምን ብዙ ዐሊሞች ይወደዳል ብለዋል (ከነርሱም መካከል) ኢማሙ ማሊክ፣ኢማሙ ሻፊዒይና ኢማሙ አሕመድ»

ምንጭ【ሶሒሁ ፊቂሂ ሱናህ (2/121)】

ከላይ ያሳለፍነው ሐዲሥ ከከሀዲዎች ጋር መመሳሰል በሸሪዓችን ክልክል እንደሆነ መረጃ ነው።ሸሪዓ እንድህ በዒባዳቸው እንኳ እንዳንመሳሰል ይከለክለናል ዛሬ የሚያሳዝነው ብዙው ወጣት በሚሰሩት ሀራም እና ፀያፍ ተግባራቸው ሳይቀር ይከተላቸዋል ውርደት ማለት እሄነው። አላህ ከውርደት ይጠብቀን

ቀደምቶቻችን የዐሹራእን ፆም በአስቸጋሪ ሆኔታ እንኳ ቢሆኑም ይፆሙት ነበር

ኢማም ዙህርይ ሙሳፊር(መንገደኛ) ሁነው ሳለ የዓሹራን ፆም ፆሙ
ለርሳቸውም "አንቱ በመንገድ ላይ ስትሆኑ ከረመዳን ፆም እያፈጠርኩ ለምን (በመንገድ ላይ ስትሆኑ) ዓሹራን ትፆማለሁ" ተባላቸው

"ረመዷን በሌላ ቀን (የቀዷ ማውጫ) ግዜ አለው ዓሹራእ ግን ያልፋል (የማካካሻ ቀን የለውም)
በማለት መለሱ

【ሲየሩ አዕላሚ ኑበላእ (5/342)】

በዚህ የዐሹራ ቀን ሁለት ቡድኖች ተሳስተው ጠመዋል

የመጀመሪያዎቹ:-
ዓሹራእን ልክ እንደ ዒድ ወን አድርጎ በመያዝ በዚህ ቀን አድስ ልብስ ይልብሳሉ የተለየ ምግብ ያዘጋጃሉ እንድሁም በመኳኳልና በመቀባባት ይበጃጃሉ አንዳንዶቹም መውሊድ በማድረግ ይደግሳሉ ይህ ሁሉ ረሱል(ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንድንሰራው ያላዘዙን ጥመትና ቢድዓ ነው። ከእንድህ አይነት ጥፋት እኛም ቤተሰቦቻችንም ልንርቅ ይገባናል።

ሁለተኞቹ:-
አንጃዎች ደግሞ እሄን ቀን ሑሰይን ኢብኑ ዐሊይ(ረዲዬሏሁ ዐንሁ) የተገደለበት ቀን ነው በማለት የአዘን እና የለቅሶ ቀን አደረጉት በዚህቀን አዝነው ተግዘው ሲያለቅሱ ሌሎችም የጃሂልያ ተግባር ሲያደርጉ ይውላሉ ይህም በሸሪዓ ያልተደነገገ ጥመት ነው።

አሏህ በእነዚህ ሁለት የጠፉ አንጃዎች መካከል አህሉሱኖችን ለቀጥተኛው መንገድ መራቸው እሄንቀን ረሱል (ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዳዘዟቸው በመፆም እና ሌሎችንም የተደነገጉ ዒባዳዎች በማድረግ ያሳልፉታል

የዐሹራእ ፆም ትሩፋቱና ምክኒያቱ እሄን ይመስላል ወሏሁ አዕለም


ዋናዉ ፃሙ የሚጀምረው ሰኞ ሲሆን
ዘጠነኛዉ ደግሞ እሁድ ነዉ።»

ኢብኑ ሙሐመድዘይን
30 views14:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-03 19:57:54
73 views16:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-03 19:56:53 ዒልም ፈላጊ ከተበላሸ …


ነገራችንን እናስተካክል

https://t.me/Muhammedsirage
72 views16:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-29 16:36:59
1ኛ, አንዳዴ የሚሰግድ አንዴት የሚተዉ የተላለፈ መልዕክት
2ኛ, ሲመቸዉ የሚሰግድ ሳይመቸዉ የሚተዉ ሰዉ የተላለፈ መልዕክት
3ኛ, ጁሙዓ ጁሙዓ ብቻ እየጠበቀ ለሚሰግድ ሰዉ የተላለፈ መልዕክት
4ኛ, ረመዷን ብቻ እየጠበቀ ለሚሰግድ ሰዉ የተላለፈ መልዕክት
5ኛ, ሶላት መስገድ ፈፅሞ የተወ ያቆመ ሰዉ የተላለፈ መልዕክት

https://t.me/HuzeyfaAhmed
177 views13:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-22 19:22:19
260 views16:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-22 19:21:56
225 views16:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-22 19:21:39
206 views16:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-22 19:20:57
170 views16:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-22 19:20:26 አብሽሪ/ አብሽር


ተጨንቀሻል? ተጨንቀሃል?
150 views16:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-18 21:16:48 ማን ሊሆን ፈለገ...።

ሙስሊም ውድ እህቴ እስኪ አሏህን ፍሪ
እወቂው እሱኑ ድንሽን ተማሪ
በሰለፎች መንሐጅ በፅናት ዘውትሪ
ይህ ነው የኔ ምክር በጨርቅሽ ጫፍ ቋጥሪ
ከጀግኖቹ መንደር በሱናው እደሪ
ከደጋጎቹ ጋር ውሎን አሳምሪ
ወደ ጥመት ጥሪ ልብ እንዳታዞሪ
መርዛቸውን ጠንቀቅ ብለሽ እህት ኑሪ፤
ሒሳብ አለመማር ወይም ኬሚስትሪ
ከወንዶች ጋር አብረሽ ስፖርትን በሱሪ
ባትሮጭ ከሜዳ ባትሽከረከሪ
ዶክተር ጋር ብቻሽን ነርስነት ባትሰሪ
የአድዋን ጦርነት ተምረሽ ሂስትሪ
እንቶ ፈንቶ ነገር ለሰው ባታወሪ
የእንግሊዝኛን ወግ አንብበሽ ባትኖሪ፤
ይበቃሽ የለም ወይ ቁርአን ብትቀሪ
ተውሒድን ተምረሽ ቤተሰብ ብትመክሪ
የሸሪዓዊ እውቀት የድን አስተማሪ
መሆንሽ በቂ ነው በፍፁም አትፍሪ
ጠላት ዞር በል በይው እንዳትበገሪ።
ማን አለሽ "ያ ጋሊያህ" አንችን ኋላ ቀሪ?
እሱ ነው የኔ ውድ አውቀሽው እደሪ
አቅሉ የዞረበት በእውር ተመሪ
ልቡ የታመመ ከንቱ ቀባጣሪ
አንችን ያስከፋብኝ የጥመቱ መሪ።
ሴት ሶሓቢያትን መከተል በይፋ
ነውር ከተባለ ተግባሩ ሲስፋፋ
የኋላ ቀርነት ሰበብ ሆኖ አስከፋ
ከሆነ ሙግቱ የነ ሸይኽ ቀርፋፋ
እህት ጆሮ አትስጭ ለኢኽዋን ልፈፋ
ጠመው አጥማሚዎች ይዘዋል ወረፋ
ቅጣት ሊያቋድሱሽ ዐዛብ ስትደነፋ
ሐፈዘኪላሁ ያን ቀን ሳይከፋ።
ሐያእ መላበስሽ ይህ ጥብቅነቱ
በነሱ ኋላ ቀር ካስባለሽ እህቱ
አዎ ነኝ በያቸው በቁጭት ይሙቱ
ቅናቻ የላቸው በሴት ሲያጫውቱ
ከአጅነቢይ ጋር ባንድ እየዶለቱ
ጀባ በይ ከቡናው ይቃም እስኪ
ጫቱ
እግሯ ከባት ድረስ ግልፅ ሆና ከፊቱ
ከሚያቃቅመው ጋር አፍ ላፍ መካፈቱ
ስልጣኔ ሆኖ ለሱ መታየቱ
የልቡ መሰለብ የአዕምሮ ቅዠቱ
ተጠናውቶት እንጅ ፀንቶ በጥመቱ
ታዳ ምን አስከፋሽ በነዚህ አይነቱ
ኋላ ቀር በጊዜው አንች ነሽ ማለቱ
ተቃርኖ እየኖረ ከራስ ማንነቱ
ንቀሽ ተራመጅ አይበግርሽ ከንቱ
ይህ የሱና ጠላት ባሪያ የስሜቱ።
ኋላ ቀር ካስባለ ድን መያዝ አጥብቆ
የሴት ሶሓቢያት ፈለግንም ንቆ
የአስተማሪያቸውን ማንነት አፅድቆ
ክብር አለመስጠት ይገልፀዋል ዘልቆ
ተማሪን ሲያንቋሽሽ ሞራልን አድቅቆ
ቀጥታ ተዋጋ ከአሏህ ጋር አውቆ
የነብዩን ሱና ከትውልድ አርቆ
ጥመትን ሊያስፋፋ እራሱን ደብቆ
ኢኽዋነልሙፍሊሲን ያሕባሽ ካባ አጥልቆ
ሲፈልግ የተብሊግ የሺአንም ሰርቆ
ስፕሪስ ድን ይዞ ቀለም አሸብርቆ
ካንች እንዳይጠጋ ሹብሐት ሰንቆ
ሊያጠምሽ በሲሕሩ ከዑማው አርቆ።
ሐሜት ሳይበግራት በትእግስት ቆማ
"አዒሽ" ብርቋ እናቴ በእውቀቷ ቀድማ
ስንቱን አስተማረች ይዛ የሐቅ አርማ
ሒጃብ ተጠንቅቃ "ኒቃብ" አስቀድማ
ሞደል ሆነቻቸው ለላቀው አላማ
ለአሏህ በመስራት ለጀነት ከተማ፤
"ኡመሃቱልሙእሚን" ቀልጠው እንደ ሻማ
ብርሃን የሰጡት በድቅድቅ ጨለማ
ቤታቸው ረግተው በ"ኢኽቲላጡ"ማ
መውጣት መች ፈለጉ በሱ ቀልብ ታማ
ከአሏህ መጣላት ተገቢ አይደለማ፤
ይህ የነሱ ምርጫ ለዛሬ አይስማማ
ከጠሞ አጥማሚዎች መባሉ ተሰማ
ሴት መውጣት አለባት ድምጿን ልታሰማ
ወንዱን እየገፋች ሰልፍ ተሽቀዳድማ
አርቃኗንም ትማር በሳይንስም ትልማ
የምን በቤት መርጋት ባሏንም ትጥቀማ
ማእረግ ይኑራት ድግሪም ድፕሎማ
ይህ ካልሆነ ፍፁም ጆሯቸው አይሰማ
ለሐቅ ተጣሪ ነፍስ ስታቅማማ
መደመር ከበዳት በሱናው አውድማ
አሳዛኙን ነገር ከነሱው ስትሰማ
በድን ትኩረት መስጠት ልባቸው ከደማ
ለኋላ ቀርነት ሰበብ ነው ካለማ
በ"ሊሳነልሐሉ" ረሱልን ሲያማ
ማን ሊሆን ፈለገ እሱ እንጅ ጠማማ።

አቡ ሐኒፋ ዐብዱልከሪም (ከገጠር)
236 views18:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ