Get Mystery Box with random crypto!

በደቡብ ከልል Human Africa Trypanosomiasis (sleeping sickness) የተባ | Affini Media and Communication

በደቡብ ከልል Human Africa Trypanosomiasis (sleeping sickness) የተባለ አዲስ በሽታ መከሰቱ ተገልጿል፤
========================
አፊኒ ነሐሴ 25፣2014
ሀዋሳ

አፋጣኝ የህክምና እርዳታ ካልተገኘ የሰው ልጆችን በህይወት የመቀጠል ጉዳይ እጅግ ፈታኝ ያርገዋል ወይም ገዳይ ነው የተባለለት በሽታ Human Africa Trypanosomiasis (sleeping sickness) መከሰቱን የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት ጤና ቢሮ የሕብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ባካሄደው የሳምንታዊ ውይይት አስታውቋል።

በአሁኑ ወቅት Human Africa Trypanosomiasis (sleeping sickness) ክስተት በጋሞ ዞን በቁጫ አልፋ ወረዳ የኦሞ ወንዝ ሸጥ ከሆኑ ቀበሌያት ወደ ሰላምበር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በወባ በሽታ ተጠርጥረው ለህክምና በመጡ ታካሚዎች ላይ በተወሰደ ናሙና ውጤቱን ለማወቅ ተችሏል ብሏል።

በመሆኑም በክልሉ በየትኛውም አካባቢዎች መሰል የህመም ምልክቶች ክስተት ዙሪያ በህረተሰቡ ዘንድ ግንዛቤ እየተፈጠረ መሄድ ስላለበት እና በተለይ አሁን ክስተቱ በተፈጠረባቸው አከባቢዎች ጋር አጎራባች የሆኑና አና በማህበራዊ ትስስር የሚገናኙ ሁሉም ቀበሌዎች ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ በየአከባቢው ባሉ የጤና መዋቅር በአስቸኳይ ሪፖርት እንዲደረግ ጥሪውን ኢኒስቲትዩቱ አቅርቧል።

በአገራችን ትኩረት የሚሹ አሩራማ በሽታዎች ከመከላከልና ከመቆጣጠር አንፃር ከዓለም ጤና ድርጅት እና ከተለያዩ አጋር ድርጅቶች ድጋፍ የፌዴራል ጤና ሚኒስቴር ከኢትዮጲያ ህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት እና ከጤና ቢሮ ጋር በመተባበር በተለያዩ የጤና ፕሮግራሞች በተቋማትና በማህበረሰብ አቀፍ እየተከናወኑ ይገኛሉ ፡፡

@via ደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት ጤና ቢሮ
አፊኒ_ሚዲያና_ኮሙኒኬሽን
#Affini_Media_Communication
ትኩስ እና እውነተኛ መረጃዎችን ለማግኘት ይከታተላሉ
ዩቲዩብ:https://youtube.com/channel/UCzxVCZUtW-XmosukNkCXZEA
telegram:https://t.me/affinimedia
https://t.me/affinihasaaw